አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሀና ልጅ)
ሪያል ማድሪድ በአዲሱ አመት ካለው ዕቅድ አንዱ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ማስፈረም ነው።ዋነኛው ውጥኑ ደግሞ ሴኔጋላዊው የሊቨርፑል አጥቂ ሳዲዮ ማኔ ሲሆን ከተጨዋቹ ወኪሎች ጋርም መነጋገር ጀምሯል።
(Le10Sport)
የአታላንታው አማካይ ዲያን ኩሉሴቭስኪ ጁቬንትስን ለመቀላቀል በዚህ ሳምንት የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ ይጠበቃል።ስዊድናዊው የ19 አመት አማካይ ከዚህ በፊት ስሙ በስፋት ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ሲያያዝ ቢሰናበትም በስተመጨረሻ ማረፊያው ቱሪን ይሆናል።ዲያን ያሳለፍነውን አመት በውሰት ፓርማ ነው የነበረው።
(Calciomercato)
ኢንተር ሚላን በቼልሲ የቋሚ ተሰላፊነት ዕድል የተነፈገውን ፈረንሳዊውን አጥቂ ኦሊቪየ ዢሩ በቀጣዮቹ ቀናት እንደሚያስፈርም ይጠበቃል።በ2020 በሚደረገው የአውሮፓ ዋንጫ ሀገሩን መወከል የሚፈልገው ዢሩ በቂ የመሰለፍ ዕድልን በመሻት ወደ አንቶኒዮ ኮንቴው ክለብ የመሄድ ዕድሉ ሰፊ ነው።
(Calciomercato)
ሁለቱ የስፔን ሐያላን ክለቦች ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ የኤስፓኞሉን አማካይ ማርክ ሮካ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።በዘንድሮው አመት 18 የላሊጋ ጨዋታዎች ላይ የተሰለፈውን አማካይ ባርሴሎና የማስፈረም ዕድሉ ግን ሰፊ ይመስላል።
(Don Balon)
ቼልሲ ለሲኤስኬ ሞስኮው አጥቂ ፊዮዶር ቻሎቭ £20ሚ. አቅርቧል።ከሩሲያ ክለቦች ጋር ጥሩ ግንኙነት ያለው የሚመስለው ቼልሲ በዘንድሮው አመት በራሺያ ሊግ አምስት ግብ ያስቆጠረውን የ21 አመት አጥቂ ለማስፈረም ጥረቱን አጠናክሯል።
(Express)
ማንቸስተር ዩናይትድ የሊሉን አማካይ ቡባከሪ ሳውማሬ ለማዘዋወር እየሞከረ ነው።ሊል ለተጨዋቹ ዝውውር £50ሚ. የሚፈልግ ሲሆን ቶተንሃም እና ዎልቭስም የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።
(France Football News)
ሊቨርፑል የሲቪያውን ተከላካይ ዲዬጎ ካርሎስ ለማዘዋወር ይፈልጋል።ቀያዮቹ ብራዚላዊውን ተከላካይ የሚፈልጉት በአመቱ መጨረሻ ሲሆን የውል ማፍረሻውን £65ሚ. ለመክፈልም ፈቃደኛ ናቸው።በዘንድሮው አመት 18 ጊዜ በላሊጋው የተሰለፈው ካርሎስ ሪያል ማድሪድም ይፈልገዋል።
(Eldesmarque)
የፓሪሰን ዤርመኑ አማካይ ጁሊያን ድራክሰለር ዛሬ በተከፈተው የዝውውር መስኮት ክለባቸውን ከሚለቁ ተጨዋቾች መሀከል እንደሚሆን ይጠበቃል።ሊቨርፑል ፣ አርሰናል እና ሲቪያ ደግሞ የክለቡ ዋነኛ ፈላጊዎች ናቸው።
(Sun)
ጆዜ ሞሪንሆ ክለባቸው ቶተንሃም በዝውውር መስኮት እምብዛም እንደማይሳተፍ ፍንጭ ሰጥተዋል።ክርስቲያን ኤሪክሰን ከቶተንሃም በዚህ የዝውውር መስኮት ከሚለቁ ተጨዋቾች ውስጥ እንደሚሆን ይጠበቃል።
(Goal)
No comments:
Post a Comment