አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ኢንተር ሚላን የ30 አመቱን ጋቦናዊ ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ ከአርሰናል ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።አንቶኒዮ ኮንቴ በተጨማሪም ጣሊያናዊውን የቼልሲ የግራ መስመር ተከላካይ ኤመርሰን ወደ ሳንሲሮ እንዲመጣለት ይፈልጋል።
(Mirror)
ቼልሲ እና ማንቸስተር ሲቲ እንግሊዛዊውን የሌስተር ሲቲ ተከላካይ ቤን ቺልዌል ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።በተለይ ማንቸስተር ሲቲ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ያስፈልገዋል።
(The i)
ምንም እንኳን በማንቸስተር ዩናይትድ በጥብቅ ቢፈለግም የ21 አመቱ እንግሊዛዊ ዶሚኒክ ካልቨርት ሊውን በኤቨርተን አዲስ የአምስት አመት ኮንትራት ሊፈርም ነው።
(Telegraph)
ጁቬንትስ ለአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ አዲስ ኮንትራት ሊያቀርብለት ነው።አሮጊቷ ለፖርቱጋላዊው ኮከብ እስከ 2023 የሚያቆይ ኮንትራት ያቀረበለት ሲሆን ሮናልዶ ውሉን ከተቀበለ ዕድሜው 38 እስኪሆን በቱሪን ይቆያል ማለት ነው።
(Corriere dello Sport, via Mail)
ሀርታ በርሊን ስዊዘርላንዳዊውን የ27 አማካይ ግራኒት ዣካ ከአርሰናል በውሰት ለመውሰድ ከስምምነት ላይ ደርሷል።ክረምት ላይ ደግሞ በቋሚነት የማስፈረም ስምምነት በውሉ ላይ ይኖራል።
(Independent)
ሰርቢያዊው የማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ ኒማኒያ ማቲች በክለቡ ያለህን ኮንትራት ታራዝማለህ ወይ ተብሎ ተጠይቆ "እስካሁን የወሰንኩት ነገር የለም" ሲል መልሷል።
(Telegraf - in Serbian)
ሪያል ማድሪድ በአዲሱ አመት ካለው ዕቅድ አንዱ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ማስፈረም ነው።ዋነኛው ውጥኑ ደግሞ ሴኔጋላዊው የሊቨርፑል አጥቂ ሳዲዮ ማኔ ሲሆን ከተጨዋቹ ወኪሎች ጋርም መነጋገር ጀምሯል።
(Le10Sport)
ቶተንሃም የሌስተር ሲቲውን የቀኝ መስመር ተከላካይ ሪካርዶ ፔሬራ ለማዘዋወር £40ሚ. አቅርቧል።የ26 አመቱ ተከላካይ በኪንግ ፓወር ድንቅ ጊዜን እያሳለፈ ሲሆን ማንቸስተር ዩናይትድ እና ፓሪሰን ዤርመንም ይፈልጉታል።
(Express)
ቼልሲ ከአጥቂው ታሚ ኤብራሀም ጋር በአዲስ ኮንትራት ጉዳይ ከስምምነት ላይ አለመድረሱን ተከትሎ ማንቸስተር ሲቲ እንግሊዛዊውን አጥቂ ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ኤብራሀም በአሁኑ ወቅት እስከ 2021-22 በስታንፎርድ ብሪጅ የሚያቆይ ኮንትራት አለው።
(Le10Sport)


No comments:
Post a Comment