አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ኦሊ ጉናር ሶልሻየር ፖል ፖግባ በጥር ወር የዝውውር መስኮት እንደማይሸጥ ተናገረ።ፈረንሳዊው አማካይ በተለይ ከሪያል ማድሪድ እና ጁቬንትስ ጋር ስሙ በስፋት እየተያያዘ ቢገኝም የቀያይ ሰይጣኖቹ አለቃ ሶልሻየር ግን ተጨዋቹ በኦልድ ትራፎርድ እንደሚቆይ ተናግሯል።
(Goal)
አርሰናል የአያክሱን አማካይ ሀኪም ሲያች ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ሞሮኮዋዊው አማካይ የሽያጭ ገንዘቡ £43ሚ. እንደሚሆን የተገመተ ሲሆን መድፈኞቹም ይህንን ገንዘብ ለመክፈል ፍቃደኝነቱን አሳይተዋል።ዚያች በዘንድሮው አመት በኤርዴቪዜው ለአያክስ 6ግብ ያስቆጠረ ሲሆን 12 አሲስትም አድርጓል።
(Calcio Mercato)
የአስቶን ቪላው አሰልጣኝ ዲን ስሚዝ ክለባቸው ኦሊቪየር ዢሩን ማዘዋወር ዋነኛው ዕቅዱ መሆኑን ይፋ አድርጓል።ፈረንሳዊው አጥቂ በዘንድሮው ሲዝን በስታንፎርድ ብሪጅ በቂ የመሰለፍ ዕድል ያልተሰጠው ሲሆን በተከፈተው የዝውውር መስኮትም የመልቀቅ ዕድሉ ሰፊ ይመስላል።
(The Athletic)
ቶተንሃም የኖርዊች ሲቲውን ተከላካይ ማክስ አሮንስ ለማዘዋወር £15ሚ. አሰናድቷል።ጆዜ ሞሪንሆ የተከላካይ መስመራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ከአሮንስ በተጨማሪ ሌሎች ተጨዋቾችም የዳኒ ሌቪ አስተዳደር እንዲያመጣለቸው ይሻሉ።
(The Sun)
ማንቸስተር ዩናይትድ ከዎልቭስ ራውል ሂሜኔስን እና ሩበን ኔቬስን ለማዘዋወር በመስራት ላይ ይገኛል።ቀያይ ሰይጣኖቹ በተጨዋቾቹ ዙሪያ ከክለባቸው ጋር መነጋገር የጀመሩ ሲሆን የአቋሚ መዋዠቅ በየጊዜው የሚታይበትን ቡድኑን ለማጠናከር ሶልሻየር አዳዲስ ተጨዋቾችን ይፈልጋል።
(Goal)
አዲሱ የኤቨርተን አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በሪያል ማድሪድ አብረውት የሰሩትን ኮሎምቢያዊውን የጨዋታ ቀማሪ ሀሜስ ሮድሪጌዝ በውሰት ወደ ጉዲሰን ፓርክ ለማዘዋወር እየሰሩ ነው።
(Sunday Mirror)
ዌስት ሀም በቀጣዩ ሳምንት ከቤኔፊካ ጋር ይወያያል።ውይይቱ የሚያተኩረው ፖርቱጋላዊውን አማካይ ጌዲሰን ፈርናንዴዝ በውሰት ስለመውሰድ ላይ ይሆናል።
(Record, via Star on Sunday)
ቶተንሃም በውሰት ከሪያል ቤቲስ አምጥቶት የነበረውን አርጀንቲናዊውን አማካይ ጂዮቫኒ ሌ ሶልሶ በቋሚነት ለማዘዋወር ለስፔኑ ክለቡ £27ሚ. አቅርቧል።ጆዜ ሞሪንሆ አማካዩን በጥብቅ ይፈልጉታል።
(Sun)
No comments:
Post a Comment