Sunday, January 5, 2020

የዕለተ ሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

                   አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ማንቸስተር ዩናይትድ ፖርቱጋላዊውን የስፖርቲንግ ሊዝበን  የጨዋታ ቀማሪ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለማዘዋወር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው።ኦሊ ጉናር ሶልሻየር ቡድኑ ውስጥ ፈጣሪ አማካዮችን ማከል ይፈልጋል።
(Goal.com)





አርሰናል ጀርመናዊው የ31 አመት የባየርን ሙኒክ ተከላካይ ጄሮሚ ቦዋቲንግ ለማዘዋወር ከባቫሪያው ክለብ ጋር ንግግር ጀምሯል።
(Footmercato - in French)





ባርሴሎና ስፔናዊውን የዳይናሞ ዛግሬቭ አጥቂ ዳኒ ኦልሞ ለማዘዋወር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ነው።የ21 አመቱን ተስፈኛ አጥቂ የእንግሊዞቹ ቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድም ይፈልጉታል።
(Goal.com)





ከማንቸስተር ዩናይትድ ሊወጣ እንደሚችል የሚነገርለት እንግሊዛዊው ሄሴ ሊንጋርድ አወዛጋቢውን እና ታዋቂውን ወኪል ሚኖ ራዮላ ወኪሉ ሊያደርገው ንግግር ላይ ናቸው።
(Mail)





የአያክሱ ድንቅ ሞሮካዊያዊ አማካይ ሀኪም ዚያች በዚህ የዝውውር መስኮት ከክለቡ እንደሚለቅ ማረጋገጫ ተስጥቶታል።የ26 አመቱን አማካይ ለማዘዋወር ሁለቱ የሰሜን ለንደን ክለቦች አርሰናል እና ቶተንሃም የሚፎካከሩ ይሆናል።
(Football.London)





የአጥቂ መስመር ስፍራውን ለማጠናከር የሚፈልገው ፍራንክ ላምፓርድ አይኑን ወደ ጣሊያን በማማተር ብራዚላዊውን የኢንተር ሚላን አጥቂ ጋብሬል ባርቦሳ ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ ለማምጣት እየሰራ ነው።ባርባሶ በዚህ አመት በውሰት ለሀገሩ ክለብ ፍላሚንጎ ተሰጥቶ ድንቅ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
(Express)





ፈረንሳዊው አጥቂ ኦስማን ዴምቤሌ በኢንስታግራም ገጹ የሊቨርፑልን ማሊያ ለብሶ የለቀቀውን ፎቶ ተከትሎ ስሙ በስፋት ከቀያዮቹ ጋር ተያይዟል።የሊቨርፑል ደጋፊዎችም በማህበራዊ ድህረ ገጽ ዝውውሩ ቢሳካ እንደሚደሰቱ በመግለጽ ላይ ናቸው።
 (Daily Express)





ዎንቼክ ሼዝኒ በጁቬንትስ አዲስ ኮንትራት ሊፈርም ነው።ፖላንዳዊው ግብ ጠባቂ የ18 ወራት ኮንትራት በቱሪን ያለው ሲሆን አሮጊቷ እስከ 2024 የሚያቆየውን ኮንትራት ነው ያቀረበችለት።
(Calciomercato)



ፍራንክ ላምፓርድ የአጥቂ ስፍራ መስመሩን ለማጠናከር ሶስት ተጨዋቾች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነው።እነሱም የሊሉ ኦስማን ዴምቤሌ ፣ የቦሩሲያ ዶርትሙንዱ ጄደን ሳንቾ እና የክሪስታል ፓላሱ ዊልፍሬድ ዛሃ ናቸው።
(Footmercato)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...