አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ማንቸስተር ዩናይትድ የባርሴሎናውን አማካይ አርቶሮ ቪዳል የማዘዋወር ፍላጎት አለው።የ32 አመቱ ቺሊያዊ ከካታላኑ ክለብ በዚህ አመት እንደሚለቅ የሚጠበቅ ሲሆን በኢንተር ሚላንም በጥብቅ ይፈለጋል።
(DirectTV Chile)
ኤቨርተን ፣ ኢንተር ሚላን ፣ ብራይተን እና ናፖሊ ጄሮሚ ቦጋን ከሳሱሎ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።ቼልሲ ተጨዋቹን ለሳሱሎ ሲሸጥ በፈለገበት ጊዜ መመለስ እንደሚችል ውል የነበረው ቢሆንም ሰማያዊዎቹ ግን ተጨዋቹን አይፈልጉትም።
(Goal)
ዌስት ሀም የስቶክ ሲቲውን አማካይ አለን ለማዘዋወር ያደረገው የመጀመሪያ ሙከራ አልተሳካለትም።አዲሱ የመዶሻዎቹ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ዌልሳዊውን ኢንተርናሽናል ይፈልጉታል።
(Football Insider)
ቶተንሃም ቶማስ ሌማርን ከአትሌቲኮ ማድሪድ ከተቻለ በቋሚነት ካልሆነ በውሰት ለመውሰድ ጥያቄ አቅርቧል።ፈረንሳዊው የቀድሞው የናፖሊ ተጨዋች በዋንዳ ሜትራ ፖሊታኖ ስኬታማ ያልሆነ ጊዜን እያሳለፈ ሲሆን አርሰናልም ይፈልገዋል።
(Independent)
ጋሬዝ ቤል ወደ ሜጀር ሊግ ሶከር ሊጓዝ እንደሆነ ተነግሯል።ፈላጊው ደግሞ በዴቪድ ቤካም ባለቤትነት የሚተዳደረው ኢንተር ሚያሚ ነው ተብሏል።
(El Desmarque)
የጁቬንትሱ ዳይሬክተር ፋቢዮ ፓራቲቺ በተከፈተው የዝውውር መስኮት ኤምሪ ቻን እና አድናን ራቢዮ ከክለቡ ሊለቁ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥተዋል።
(Goal)
የፓሪሰን ዤርመኑ አጥቂ ኤድንሰን ካቫኒ ወደ ስፔኑ ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ ሊዘዋወር እንደሆነ ተነግሯል።ኡራጋዊያዊው በተለይ ከማውሮ ኢካርዲ መምጣት በኋላ የቋሚ ተሰላፊነት ዕድልን ያጣ ሲሆን በክለቡ ያለው ኮንትራትም በአመቱ መጨረሻ ያበቃል።
(L'Equipe)
ካሉም ቼምበርስ ጉዳት በማስተናገዱ ወደ መሰለፍ እንደሚመጣ ቢገመትም ሽኾድራን ሙስጣፊ ግን አሁንም አርሰናልን መልቀቅ ይፈልጋል።ጀርመናዊው ተከላካይ በዚህ አመት ብዙ ትችትን በማስተናገድ ላይ ይገኛል።
(The Mirror)
No comments:
Post a Comment