Monday, January 6, 2020

የዕለተ ማክሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ትናንት በፈረንጆቹ አዲስ አመት የጣሊያን ሴሪ ኤ ሲጀመር ጁቬንትስ ካጊሊያሪን አስተናግዶ 4ለ0 ያሸነፈ ሲሆን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሀትሪክ ሰርቷል።ኢንተር ሚላንም ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ናፖሊን 3ለ1 አሸንፏል።ጁቬንትስ እና ኢንተር ሚላን በእኩል 45ነጥብ በግብ ልዩነት ተለያይተው ሊጉን እየመሩ ይገኛሉ።






ቶተንሃም ፈረንሳዊውን የአትሌቲኮ ማድሪድ አማካይ ቶማስ ሌማር በውሰት ለመውሰድ ጥያቄ አቅርቧል።ስፐርስ በውሉ ላይ ከፈለገች በ£60ሚ. ማስፈረም የምትችልበትን መንገድም እንዲሰፍር ትፈልጋለች።
(Independent)





ማንቸስተር ሲቲ ስሎቫኪያዊውን የኢንተር ሚላን ተከላካይ ሚላን ስክሪኒያር ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።የስፔኖቹ ሐያላን ክለቦች ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድም የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።
(Mirror)





ኢንተር ሚላን ዴንማርካዊውን የቶተንሃም አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ለማዘዋወር £20ሚ. አቅርቧል።አንቶኒዮ ኮንቴ ግን የሚሳካለት ከሆነ በዋናነት የሚፈልገው የባርሴሎናውን ቺሊያዊ አማካይ አርቱሮ ቪዳል ነው።
(Mirror)





ማንቸስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የሌስተር ሲቲ አማካይ ጄምስ ማዲሰን የማዘዋወር ፍላጎት ቢኖረም በተከፈተው የዝውውር መስኮት ግን ተጨዋቹን ወደ ኦልድ ትራፎርድ ማምጣት አዳጋች መሆኑን ይረዳል።
(Sky Sports)




የሪያል ማድሪዱ ክሮኤሽያዊ አማካይ ሉካ ሞድሪች ወደ ሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ ዲሲ ዩናይትድ ለመዘዋወር እየተነጋገረ ነው።ዲሲ ዩናይትድ የቀድሞው የዌይን ሩኒ ክለብ ነው።
(The Athletic - subscription required)





ማንቸስተር ዩናይትድ ሲን ሎንግ ስታፍን በጥብቅ እየፈለገ መሆኑን ተከትሎ ስለ ተጨዋቹ የተጠየቁት የኒውካስትል ዩናይትዱ አሰልጣኝ ስቲቭ ብሩስ ክለባቸው ተስፈኛ ታዳጊ  ተጨዋቾችን ወደ ገበያ እንደማያወጣ ገልጸዋል።
(Manchester Evening News)





ምንም እንኳን ከማንቸስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተን ፍላጎት ቢኖርም ኤምሪ ቻንን እና አድሪያን ራቢዮን በተከፈተው የዝውውር መስኮት እንደማይሸጡ የጁቬንትሱ ዳይሬክተር ፋቢዮ ፓራቲቺ ተናግረዋል።
(Mail)





ኤቨርተን ፣ ኢንተር ሚላን ፣ ብራይተን እና ናፖሊ ጄሮሚ ቦጋን ከሳሱሎ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።ቼልሲ ተጨዋቹን ለሳሱሎ ሲሸጥ በፈለገበት ጊዜ መመለስ እንደሚችል ውል የነበረው ቢሆንም ሰማያዊዎቹ ግን ተጨዋቹን አይፈልጉትም።
(Goal)





ዌስት ሀም የስቶክ ሲቲውን አማካይ አለን ለማዘዋወር ያደረገው የመጀመሪያ ሙከራ አልተሳካለትም።አዲሱ የመዶሻዎቹ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ዌልሳዊውን ኢንተርናሽናል ይፈልጉታል።
(Football Insider)





ቶተንሃም ቶማስ ሌማርን ከአትሌቲኮ ማድሪድ ከተቻለ በቋሚነት ካልሆነ በውሰት ለመውሰድ ጥያቄ አቅርቧል።ፈረንሳዊው የቀድሞው የናፖሊ ተጨዋች በዋንዳ ሜትራ ፖሊታኖ ስኬታማ ያልሆነ ጊዜን እያሳለፈ ሲሆን አርሰናልም ይፈልገዋል።
(Independent)


No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...