Tuesday, January 7, 2020

የዕለተ ማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

                 አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)





ስሙ በስፋት ከቀድሞው ክለቡ ባርሴሎና ጋር ሲያያዝ የሰነበተው ብራዚላዊው የወቅቱ ውድ ተጨዋች ኔይማር በፓሪሰን ዤርመን ለተጨማሪ አመታት ለመቆየት አዲስ ኮንትራት ሊፈርም ነው።
( Le Parisien)





የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ ኦሊቪየር ዢሩ በቼልሲ ደስተኛ እንዳልሆነ ጠቅሰው ከክለቡ መውጣት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።የ33 አመቱ አጥቂ ስሙ በስፋት ከኢንተር ሚላን ፣ አስቶን ቪላ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ጋር እየተያያዘ ሲሆን በ2020ው የአውሮፓ ዋንጫ ሀገሩን ለመወከል በቂ የመሰለፍ ዕድል ወደ ሚያገኝበት ክለብ መሄድ እንዳለበት ዴሾ ተናግሯል።
(Goal)





ምንም እንኳን የክርስቲያን ኤሪክሰን ስም በስፋት ከኢንተር ሚላን ጋር ቢያያዝም የጣሊያኑ ክለብ ፕሬዝደንት ጁሴፔ ማሮታ ክለባቸው ከዴንማርካዊው አማካይ ጋር ምንም አይነት ንግግር እንዳላደረገ፡ተናግረዋል።የኤሪክሰን ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ የሚያበቃ ሲሆን በተከፈተው የዝውውር መስኮት ስፐርስን እንደሚለቅ ይጠበቃል።
(Goal)







አርሰናል በተከፈተው የዝውውር መስኮት ተጨዋቾችን በቋሚነት ከማዘዋወር ይልቅ በውሰት መውሰድን እንደሚጠቀም ተዘግቧል።የዚህ ምክንያት ደግሞ ባልተለመደ መልኩ ባሳለፍነው የክረምት የዝውውር መስኮት £130ሚ. ስላወጣ በዚህ የዝውውር መስኮት ወጪ ለመቆጠብ ነው።
(Goal)





የቀድሞው የቶተንሃም ተጨዋች ዳረን ቤንስ ስለ ስፐርስ ወቅታዊ ሁኔታ ተጠይቆ የሀሪ ኬንን መጎዳት ተከትሎ ጆዜ ሞሪንሆ አዲስ የአጥቂ ስፍራ መስመር ተጨዋች ማስፈረም እንዳለባቸው ፥ ያ ተጨዋችም የሳውዝሀምተኑ ዳኒ ኢንግስ መሆን እንዳለበት መክሯል።
(Goal)




ጁቬንትስ የማንቸስተር ዩናይትዱን ታዳጊ ታሂት ቾንግ ለማዘዋወር ጥረት እያደረገ ነው።ሆላንዳዊው ዊንገር በቀያይ ሰይጣኖቹ ያለው ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ የሚያልቅ ሲሆን አሮጊቷ ካዘዋወረችው ሳምንታዊ £35,000 አሰናድታለች።
(The Sun)





ማንቸስተር ሲቲ ሴኔጋላዊውን የናፖሊ ተከላካይ ለማዘዋወር £100ሚ. አሰናድቷል።ከፍተኛ የመሀል ተከላካይ ችግር ያለበት ሲቲ ድንቁን ሴኔጋላዊ ለማዘዋወር በጥብቅ ይሻል።
(90min)





የክሪስታል ፓላሱ የክንፍ አጥቂ ዊልፍሬድ ዛሃ ወደ ባየርን ሙኒክ ሊጓዝ የሚችልበት ዕድል አለ።አይቮሪኮስታዊው አጥቂ በሌሎች በርካታ ክለቦችም ይፈለጋል።
(Sky Deutschland)







No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...