Tuesday, January 7, 2020

የዕለተ ረቡዕ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

               አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ትናንት ምሽት በካራባኦ ካፕ በተደረገው ማንቹኒያን ደርቢ ማንቸስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ማንቸስተር ዩናይትድን 3-1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።





ትናንት ምሽት የካፍ የአመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጨዋች ሽልማት ሥነ-ስርዓት የተደረገ ሲሆን ሴኔጋላዊው የሊቨርፑል አጥቂ ሳዲዮ ማኔ ሽልማቱን ተቀዳጅቷል።ማኔ በዓመቱ ከክለቡ ሊቨርፑል ጋር አስደናቂ ጊዜን ያሳለፈ ሲሆን ሀገሩንም ለአፍሪካዋ ዋንጫ ፍጻሜ አብቅቶ ነበር።
(CAF)





ቼልሲ አይቮሪኮስታዊውን አጥቂ ዊልፍሬድ ዛሃ በተከፈተው የዝውውር መስኮት የማስፈረም ዕቅድ ቢኖረም ክሪስታላ ፓላስ የጠየቀውን £80ሚ. ግን ለመክፈል ፈቃደኛ አይደለም።
(Express)





ማንቸስተር ሲቲ የአጥቂ ስፍራ መስመሩን ይበልጥ ለማጠናከር ስፔናዊውን የዎልቭስ ተጨዋች አዳማ ትራዎሬ ማዘዋወርን ይሻል።ፔፕ ጋርዲዮላ ዘንድሮ ደካማ ጊዜን እያሳለፈ እንደሆነ ይታወቃል።
(Calcio Mercato, via Manchester Evening News)






የቺሊያዊው የባርሴሎና አማካይ አርቶሮ ቪዳል ወኪል በዚህ ሳምንት በጥር ወር የዝውውር መስኮት ስለመዘዋወር ጉዳይ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር እንደሚመክር ይጠበቃል።ቪዳል ኢንተር ሚላንን ጨምሮ በሌሎች ክለቦችም ይፈለጋል።
(Corriere Della Sera, via Mirror)






በጉዳት ለአምስት ወራት ከሜዳ ርቆ የቆየው ጀርመናዊው የማንቸስተር ሲቲ አጥቂ ለሮይ ሳኔ ወደ ልምምድ ሜዳ ተመልሷል።ይህም ለፔፕ ጋርዲዮላ በጎ ዜና ነው ተብሏል።
(Manchester Evening News)






ስሙ በስፋት ከቀድሞው ክለቡ ባርሴሎና ጋር ሲያያዝ የሰነበተው ብራዚላዊው የወቅቱ ውድ ተጨዋች ኔይማር በፓሪሰን ዤርመን ለተጨማሪ አመታት ለመቆየት አዲስ ኮንትራት ሊፈርም ነው።
( Le Parisien)





የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሾ ኦሊቪየር ዢሩ በቼልሲ ደስተኛ እንዳልሆነ ጠቅሰው ከክለቡ መውጣት አለበት ሲሉ ተናግረዋል።የ33 አመቱ አጥቂ ስሙ በስፋት ከኢንተር ሚላን ፣ አስቶን ቪላ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ጋር እየተያያዘ ሲሆን በ2020ው የአውሮፓ ዋንጫ ሀገሩን ለመወከል በቂ የመሰለፍ ዕድል ወደ ሚያገኝበት ክለብ መሄድ እንዳለበት ዴሾ ተናግሯል።
(Goal)





ምንም እንኳን የክርስቲያን ኤሪክሰን ስም በስፋት ከኢንተር ሚላን ጋር ቢያያዝም የጣሊያኑ ክለብ ፕሬዝደንት ጁሴፔ ማሮታ ክለባቸው ከዴንማርካዊው አማካይ ጋር ምንም አይነት ንግግር እንዳላደረገ፡ተናግረዋል።የኤሪክሰን ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ የሚያበቃ ሲሆን በተከፈተው የዝውውር መስኮት ስፐርስን እንደሚለቅ ይጠበቃል።
(Goal)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...