አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
የሀገር ውስጥ ስፖርታዊ ዜናዎች
ስምንተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች መርሃ ግብር
ቅዳሜ
ሰበታ ከተማ ከ ጅማ አባ ጅፋር - 9:00
እሁድ
ወልዋሎ ከ ሀዲያ ሆሳዕና - 9:00
ወላይታ ድቻ ከ ስሑል ሽረ - 9:00
አዳማ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ - 9:00
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ድሬደዋ ከተማ - 9:00
ሲዳማ ቡና ከ ባህር ዳር ከተማ - 9:00
ፋሲል ከነማ ከ ኢትዮጵያ ቡና - 9:00
ወልቂጤ ከተማ ከ መቐለ 70 አ. - 9:00
ማንቸስተር ዩናይትድ ሜክሲኳዊውን የዎልቭስ አጥቂ ራውል ሂሜኔስ ወይም የሊዮኑን ፈረንሳዊውን አጥቂ ኦስማን ዴምቤሌ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ማስፈረም ይፈልጋል።ዴምቤሌን ጁቬንትስ እና ቼልሲም ይፈልጉታል።
(Sky Sports)
የቼልሲው አማካይ ንጎሎ ካንቴ ወደ ሪያል ማድሪድ መሄድ ይፈልጋል።ታታሪው ፈረንሳዊ አዲስ ፈተናን ፍለጋ ወደ ስፔን መጓዝን የሚሻ ሲሆን ሎስብላንኮዎቹም ለዝውውሩ £100ሚ. አሰናድቷል።ባየርን ሙኒክ እና ጁቬንትስም የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።
(Sun)
ማንቸስተር ሲቲ የመሀል ተከላካይ በተከፈተው የዝውውር መስኮት ለማስፈረም እየሰራ ነው።ውሃ ሰማያዊዎቹ የኤምሪክ ላፖርቴን መጎዳት ተከትሎ ፈርናንዲንሆን በመሀል ተከላካይነት ለመጠቀም ተገደው እንደነበር ይታወሳል።
(Times)
ቶተንሃም የሳውዝሀምተኑን አጥቂ ዳኒ ኢንግስ ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ሀሪ ኬን ለሶስት ወራት ከሜዳ ውጪ እንደሚሆን ይፋ መደረጉን ተከትሎ ስፐርስ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ለማስፈረም ወደ ገበያ ወጥታለች።
(Daily Star)
የአርትሮ ቪዳል ቆይታ በኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ቆይታ ላይ ይወሰናል።ቫልቬርዴ ከክለቡ የሚሰናበቱ ከሆነ ቪዳል ወደ ኢንተር ሚላን እንደሚጓዝ ይጠበቃል።
(Mundo Deportivo)
ኦሌ ጉናር ሶልሻየር የስፖርቲንግ ሊዝበኑን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ አጥብቆ እንደሚፈልግ ተነግሯል።ፖርቱጋላዊው ኢንተርናሽናል ስሙ በስፋት ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር መያያዝ ከጀመረ ሰነባብቷል።
(The Athletic)
ፔፕ ጋርዲዮላ ስለ ጀርመናዊው አማካይ ለሮይ ሳኔ ቆይታ ተጠይቆ "ይሄ መጠየቅ ያለበት ለሳኔ ነው።እንዲሁም ለወኪሉ እና ለክለቡ ፥ እኔ እዚህ ላይ አልገባም" ብሏል። ሳኔ ስሙ በስፋት ከባየርን ሙኒክ ጋር በመያያዝ ላይ ይገኛል።
(Goal)
ኦሊቪየ ዢሩ ኢንተር ሚላንን ለመቀላቀል በመርህ ደረጃ ከስምምነት ላይ ደርሷል።የዓለም ዋንጫን ከሀገሩ ጋር ያሳካው ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል በአንቶኒዮ ኮንቴ ቡድን ውስጥ ከሉካኩ ጋር እንደሚጣመር ይጠበቃል።
(Sky Sports)
No comments:
Post a Comment