አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
የውጭ ስፖርታዊ ዜናዎች
ቶተንሃም የቤኔፊካውን አማካይ ጌድሰን ፈርናንዴዝ ለአስራ ስምንት ወራት በውሰት ለመውሰድ ከጫፍ ደርሷል።ዌስት ሀምም የ21 አመቱ አማካይ ፈላጊ ቢሆንም ስፐርስ ተጨዋቹን የማግኘት ከፍተኛ ዕድል አላት።
(Sunday Mirror)
ስሙ በስፋት ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ሲያያዝ የቆየው የአያክሱ ሆላንዳዊ አማካይ ዶኒ ቫን ደ ቢክ በጥር ወሩ የዝውውር መስኮት ክለቡን እንደማይለቅ ተናግሯል።
(Fox Sports Netherlands, via ESPN)
ማንቸስተር ዩናይትድ ፖርቱጋላዊውን የስፖርቲንግ ሊዝበን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለማዘዋወር አርጀንቲናዊውን ማርከስ ሮሆ እና £60ሚ. አቅርቧል።
(Talksport)
የርገን ክሎፕ የባርሴሎናውን ፈረንሳዊ አጥቂ ኦስማን ዴምቤሌ ወደ አንፊልድ ማምጣት ይሻሉ።በዘንድሮው አመት ድንቅ ጊዜን በፕሪሚየር ሊጉ እያሳለፈ የሚገኘው ሊቨርፑል ሻምፒዮን የመሆን ዕድሉን አስፍቷል።
(ElDesmarque - in Spanish)
የርገን ክሎፕ ፈርሚንሆ ይቅርታ እንደጠየቃቸው ተናገሩ።ትናንት ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ቶተንሃምን በረታበት ጨዋታ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረውን ፈርሚንሆ ከጨዋታው በኋላ ክሎፕ ሊያቅፉት ሲሄዱ "ከዚህ በላይ ግብ ማስቆጠር ነበረብኝ" በማለት ይቅርታ እንደጠየቃቸው ተናግረዋል።
(Goal)
ኢንተር ሚላን ክርስቲያን ኤሪክሰንን ለማዘዋወር ስምምነት ላይ የደረሰ ሲሆን ዴንማርካዊው አማካይም እስከ 2024 በሳንሲሮ የሚቆይ ይመስላል።ኤሪክሰን በአመት €7.5ሚ. እንደሚከፈለውም ተነግሯል።
(Gazzetta dello Sport)
ማንቸስተር ሲቲ የመሀል ተከላካይ በተከፈተው የዝውውር መስኮት ለማስፈረም እየሰራ ነው።ውሃ ሰማያዊዎቹ የኤምሪክ ላፖርቴን መጎዳት ተከትሎ ፈርናንዲንሆን በመሀል ተከላካይነት ለመጠቀም ተገደው እንደነበር ይታወሳል።
(Times)
ቶተንሃም የሳውዝሀምተኑን አጥቂ ዳኒ ኢንግስ ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ሀሪ ኬን ለሶስት ወራት ከሜዳ ውጪ እንደሚሆን ይፋ መደረጉን ተከትሎ ስፐርስ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ለማስፈረም ወደ ገበያ ወጥታለች።
(Daily Star)
የአርትሮ ቪዳል ቆይታ በኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ቆይታ ላይ ይወሰናል።ቫልቬርዴ ከክለቡ የሚሰናበቱ ከሆነ ቪዳል ወደ ኢንተር ሚላን እንደሚጓዝ ይጠበቃል።
(Mundo Deportivo)
No comments:
Post a Comment