ማንችስተር ሲቲዎች ፖርቹጋላዊውን የስፖርቲንግ ሊዝበኑን ብሩኖ ፈርናንዴዝን ለማዘዋወር ዩናይትዶች ላይ ገብተውባቸዋል ይህንን ተከትሎ የልጁ የዝውውር ሂሳብ እስከ €100m ከፍ እንደሚል ተሰምቷል
በርንማውዞች የቦሩሲያ ዶርትመንዱን የመስመር ተጨዋች ጃኮብ ብሩን ላርሰንን በውሰት ለማስፈረም ንግግር ጀምረዋል በቋሚነት ማስፈረም ከፈለጉ ከ£13m እስከ £15m ያሶጣቸዋል
አርሰናሎች በአመቱ መጨረሻ በነፃ ያገኙታል ሲባል የቆየው የፒኤስጂው የግራ መስመር ተከላካይ ላይቪን ኮርዙዋን በጥር የዝውውር መስኮት ለማምጣት ፍላጎት አሳይተዋል ፒኤስጂ ከልጁ £6m ይፈልጋል
ክርስቲያን ኤሪክሰን ወደ ኢንተር ሚላን ለማምራት ከጫፍ ደርሱዋል በዚህ ሳምንት ዝውውሩ ይጠናቀቃል በቶተንሀም እና ኢንተር መካከል የነበረው ድርድር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል
የፒኤስጂው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሊዮናርዶ ካቫኒ ፒኤስጂን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረቡን ይፋ አርገዋል አያይዘውም ከዚህ በፊት ከአትሌቲኮ ማድሪድ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ እንዳደረጉም ተናግረዋል
ኤሲሚላኖች ጀርመናዊውን የጁቬንቱስ አማካይ ኤምሪ ካንን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው ከኤሲሚላን በተጨማሪ በብዙ ክለቦች ይፈለጋል
ሮማዎች የቀድሞውን የዩናይትድ ተጨዋች አድናን ያኑዛይን ከሪያል ሶሴዳድ በውሰት ማስፈረም እንደሚፈልጉ እና አመቱ ሲጠናቀቅ £13m በመክፈል ቋሚ ማድረግ ይፈልጋሉ
ፒኤስጂዎች ሴኔጋላዊውን የናፖሊ ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊን ማስፈረም ይፈልጋሉ ለልጁም አመታዊ £12m ለመክፈል ፍቃደኛ ሆነዋል
ጁቬንቱሶች ፈርናንዶ ቤርናንዴስኪን ለባርሴሎና በመስጠት ኢቫን ራኪቲችን ለመቀያየር ንግግር ጀምረዋል
ዩናይትዶች የብሩኖ ፈርናንዴዝ ዝውውር ድርድር መቋረጡን ተከትሎ በጥር ለማዘዋወር ቢከብድም ፊታቸውን ወደ ሌስተሩ ኮከብ ማዲሰን አዙረዋል በሌላ ዘገባ ዩናይትድ እና ስፖርቲትግ ሊዝበን ለድርድር በዚህ ሳምንት ድጋሚ እንደሚቀመጡ ተነግሯል
No comments:
Post a Comment