አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
የቀድሞ የዩናይትድ ኮከብ ሀቪየር ሄርናንዴዝ ቺቻሪቶ ወደ አሜሪካኑ ኤልኤ ጋላክሲ ተዘዋውሯል
ኒውካስትል ዩናይትዶች የቀድሞውን የቶተንሀም ተጨዋች ነቢል ቤንታሌብን እስከዚ የውድድር አመት መጨረሻ በሚቆይ የውሰት ውል አስፈርመውታል
ኦልምፒክ ሊዮኖች ካርልቶኮ ኢካምቢን ከቪያሪያል £17m አስፈርመዋል
ኢንተር ሚላን ናይጄሪያዊውን ቪክተር ሞሰስን ከፊነርባቼ በውሰት ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል ከደቂቃዎች ፊት ሞሰስ በጣሊያን መታየቱን ታማኝ ሚባሉ ምንጮች በፎቶ አስደግፈው አውጥተውታ
አስቶንቪላ የጌንኩን አጥቂ ምብዋና ሳማታን በ £10m አራት አመት ከግማሽ አመት በሚቆይ ኮንትራት ማስፈረማቸውን ይፋ አርገዋል
ወልቭሶች የኦሎምፒኮሱን የመስመር ተጨዋች ዳንኤል ፖዴንስን በ£21m ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል
ሼፍልድ ዩናይትዶች ጃክ ሮቢንሰንን ከኖቲንግሀም ሁለት አመት ከግማሽ አመት በሚቆይ ኮንትራት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል
አርሰናሎች ጀርመናዊውን ተከላካይ ጄሮሜ ቡአቴንግን የዝውውር መስኮቱ ሳይዘጋ ማስፈረም ይፈልጋሉ
ዩናይትድ እና ስፖርቲንግ ሊዝበኖች በብሩኖ ፈርናንዴዝ ዝውውር ላይ ከስምምነት ደርሰዋል ዩናይትዶች ዝውውሩን በቀጣይ ሳምንት እንደሚጨርሱ ተማምነዋል
No comments:
Post a Comment