አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
የሀገር ውስጥ ዜናዎች
(Soccer Ethiopia)
የውጭ ሀገር ዜናዎች
(Sun)
ከበርካታ ተደጋጋሚ እና አሰልቺ ጥያቄዎች በኋላ ማንቸስተር ዩናይትድ ፖርቱጋላዊውን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ማስፈረሙን በሳምንቱ መጨረሻ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
(Mirror)
ስፔናዊው የሪያል ማድሪድ የቀኝ መስመር ተከላካይ አልቫሮ ኦሪዮዞላ ባየርን ሙኒክን ለመቀላቀል የህክምና ምርመራ ለማድረግ ወደ ጀርመን ተጉዟል።የ24 አመቱ ተጨዋች ቀሪውን ሲዝን በባቫሪያው ክለብ የሚያሳልፍ ይሆናል።
(AS - in Spanish)
አዲሱ የባርሴሎና አሰልጣኝ ኪዮንኬ ሲቴይን ሊውስ ሱዋሬዝ መጎዳቱን ተከትሎ የሱን ቦታ ለመተካት አዲስ አጥቂ እንደሚያስፈርሙ ተናግረዋል።ዋነኛው እቅዳቸው ደግሞ የቫሌንሲያው ስፔናዊ አጥቂ ሮድሪጎ ሞሬኖ ነው።
(Marca)
የሌስተር ሲቲውን አልጄሪያዊ አጥቂ ኢስላም ስሌማኒ ለማዘዋወር ቶተንሃም ጥረት በማድረግ ላይ ነው።ጆዜ ሞሪንሆ የሀሪ ኬንን የረዥም ጊዜ ጉዳት ለመሸፈን አዲስ አጥቂ ይፈልጋሉ።
(Leicester Mercury)
ባርሴሎና ጋቦናዊውን የአርሰናል አጥቂ ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ ለማዘዋወር እየሰራ ነው።ኦባማያንግ እስከ ቀጣዩ አመት በአርሰናል የሚቆይ ከሆነ በውሉ መሰረት £15ሚ. የታማኝነት ክፍያ የሚከፈለው ሲሆን ከዛ በፊት ክለቡን ከለቀቀ ግን ያንን ያጣል።
(Star)
አሜሪካዊው ቢሊየነር ዳን ፍሬድኪን የጣሊያኑን ክለብ ሮማ ለመግዛት ለውይይት ሚላን ገብተዋል።
(Corriere dello Sport - in Italian)
ዛሬ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚደረጉ ጨዋታዎች መርሃ ግብር
ሌስተር ሲቲ ከ ዌስት ሀም ዩናይትድ - 4:30
ቶተንሃም ሆትስፐር ከ ኖርዊች ሲቲ - 4:30
ማንቸስተር ዩናይትድ ከ በርንሌይ - 5:15
No comments:
Post a Comment