Friday, January 10, 2020

የዕለተ አርብ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ቶተንሃም ከ ሳውዝሃምተን በነበረው ጨዋታ ጉዳት አስተናግዶ የነበረው ሀሪ ኬን ለሶስት ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ይፋ ሆኗል።በዚህም ምክንያት ጆዜ ሞሪንሆ የእንግሊዛዊውን አጥቂ ቦታ ለመተካት አዲስ ተጨዋች ማስፈረም እንደሚጠበቅባቸው ብዙዎች በመናገር ላይ ናቸው።
( Goal)





የቀድሞው የባርሴሎና ሌጀንድ ዣቪ ወደ ካምፕ ኑ የሚመለስበት ዕድል እየተፈጠረ ይመስላል።በኳታሩ ክለብ አል-አሳድ የሚገኘው ዣቪ ወደ ቀድሞው ክለቡ የሚመለሰው ቀውስ ላይ የሚገኙትን ኤርኔስቶ ቫልቬርዴን በመተካት እንደሚሆን ይጠበቃል።ከባርሴሎና ባለ ስልጣኖች መሀከል የቀድሞው ተጨዋች ኤሪክ አቢዳል የሚመራው ልዑክ ዣቪን ለማነጋገር ወደ ኳታር ይጓዛልም ተብሏል።
(RAC1)





ማንቸስተር ዩናይትድ ኒማኒያ ማቲችን በተመለከተ የቀረቡለትን ሁለት የዝውውር ጥያቄዎች ውድቅ አድርጓል።በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት አስቸጋሪ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው ሰርቢያዊ አማካይ በተለይ በአትሌቲኮ ማድሪድ እና ኢንተር ሚላን በጥብቅ ይፈለጋል።
(Daily Record)





ፍራንክ ላምፓርድ ክሪስቴንሰን ቼልሲን በጥር ወሩ የዝውውር መስኮት እንደማይለቅ ተናግሯል።አንድሪያስ ክሪስቲየንሰን በኤሲ ሚላን ከሚፈለጉ ተጨዋቾች ዋነኛው ነው።
(Goal)





የቀድሞው የቶተንሃም ሌጀንድ ስሊቪ አለን የሀሪ ኬንን መጎዳት ተከትሎ ቦታውን ለመተካት ኤዲንሰን ካቫኒን ስፐርስ ማስፈረም አለበት ብሏል።በተጨማሪም ጋሬዝ ቤልን መመለስ ያስፈልጋል ሲል ተናግሯል።
(Goal)





ኦሌ ጉናር ሶልሻየር የስፖርቲንግ ሊዝበኑን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ አጥብቆ እንደሚፈልግ ተነግሯል።ፖርቱጋላዊው ኢንተርናሽናል ስሙ በስፋት ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር መያያዝ ከጀመረ ሰነባብቷል።
(The Athletic)





ፔፕ ጋርዲዮላ ስለ ጀርመናዊው አማካይ ለሮይ ሳኔ ቆይታ ተጠይቆ "ይሄ መጠየቅ ያለበት ለሳኔ ነው።እንዲሁም ለወኪሉ እና ለክለቡ ፥ እኔ እዚህ ላይ አልገባም" ብሏል። ሳኔ ስሙ በስፋት ከባየርን ሙኒክ ጋር በመያያዝ ላይ ይገኛል።
(Goal)





ኦሊቪየ ዢሩ ኢንተር ሚላንን ለመቀላቀል በመርህ ደረጃ ከስምምነት ላይ ደርሷል።የዓለም ዋንጫን ከሀገሩ ጋር ያሳካው ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል በአንቶኒዮ ኮንቴ ቡድን ውስጥ ከሉካኩ ጋር እንደሚጣመር ይጠበቃል።
(Sky Sports)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...