አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ክርስቲያን ኤሪክሰን ከኢንተር ሚላን ጋር አነጋገር ወደ ጣሊያን ሊጓዝ መሆኑን የጋርዲያኑ ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል።ኤሪክሰን በቶተንሃም ያለው ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ ይጠናቀቃል።ኢንተር ሚላን የቼልሲውን ፈረንሳዊ አጥቂ ኦሊቪየ ዢሩም ለማዘዋወር ጥረቱን ቀጥሏል።
(Guardian)
ባርሴሎና ምንም እንኳን ትናንት በስፔን ሱፐር ካፕ የ3ለ2 ሽንፈት ቢያጋጥመውም ኤርኔስቶ ቫልቬርዴን የማባረር ዕቅድ የለውም።ቫልቬርዴ ከጨዋታው በኋላ ስራውን ሊያጣ እንደሚችል ስጋት ካለው ተጠይቆ "ይሄ ምንጊዜም ያለ ነው" ሲል መልሷል።
(Cope)
በበርካታ ክለቦች እየተፈለገ የሚገኘው የሊዮኑ አጥቂ ሞሳ ዴምቤሌ በጆዜ ሞሪንሆው ቶተንሃምም ተፈልጓል።ሀሪ ኬንን በጉዳት ያጣው የ23 አመቱን አጥቂ አጥብቆ ይሻዋል።
(Goal)
የዌስት ሀሙ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ቤልጄሚያዊውን የ32 አማካይ ማርዋን ፌይላኒ ከቻይናው ክለብ ሻልዶንግ ሊዎንግ ማዘዋወር ይፈልጋል።ሞይስ ከዚህ በፊት በሁለት ክለቦች ከፌይላኒ ጋር አብሮ ሰርቷል።
(Sky Sports)
ቼልሲ እና ቶተንሃም የ24 አመቱን ፈረንሳዊ የክንፍ አጥቂ ቶማስ ሌማር እስከ አመቱ መጨረሻ በውሰት ለመውሰድ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።ሌማር በአትሌቲኮ ማድሪድ ከባድ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።
(Telegraph)
ሪያል ማድሪድ በተከፈተው የዝውውር መስኮት ዌልሳዊውን የክንፍ አጥቂ ጋሬዝ ቤል የመሸጥ ፍላጎት ያለው ሲሆን ወኪሉ ግን ዝውውሩ በአመቱ መጨረሻ እንዲፈጸም ነው የሚፈልገው።
(Telegraph)
ቶተንሃም ፖርቱጋላዊውን የ26 አመት የባርሴሎና የቀኝ መስመር ተከላካይ ኔልሰን ሴሜዶ የማዘዋወር ፍላጎት አለው።
(Mirror)
የቀድሞው የአርሰናል አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ ኤቨርተን ካርሎ አንቾሎቲን ከመሾሙ በፊት ለሶስት ሰዓት ያክል አነጋግሮት ባለመስማማት እንዳልተሳካ ተናግሯል።
(Mail)
ሌስተር ሲቲ ቱርካዊውን የጁቬንትስ ተከላካይ ሜርህ ዴሚራል ለማዘዋወር ጥረት እያደረገ ነው።ሌስተር ከዚህ በፊት ተጨዋቹን ሁለት ጊዜ ለማዘዋወር ሞክሮ ውድቅ የተደረገበት ሲሆን ማንቸስተር ሲቲም የተጨዋቹ ፈላጊ ነው።
(Mirror)
No comments:
Post a Comment