Monday, January 27, 2020

የዕለተ ሰኞ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

           አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ

ዩናይትዶች አሁን እንግሊዛዊውን ጀምስ ማዲሰንን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው በጥር የዝውውር መስኮት ዝውውሩ የመሳካት እድል ባይኖረውም ከክረምት በፊት ለሌስተር ይፋዊ ጥያቄ በማቅረብ ለድርድር ለመቀመጥ ዝግጁ ናቸው።




ጨራሽ አጥቂ እየፈለጉ የሚገኙት ባርሴሎናዎች ፊታቸውን ወደ ሞናኮ ዌሳም ቤንያደር አዙረው ነበር ለሞናኮም የዝውውር ጥያቄ አቅርበው ውድቅ ተደርጎባቸዋል።




ሼፊልዶች ባሳለፍነው ሳምንት £20M የለጠፉበትን ጆን ፍሌክን ለመሸጥ ፍላጎት አሳይተዋል አርሰናል ልጁን ለማስፈረም ፍላጎት ያለው ክለብ ሆኗል።




በዩናይትድ እና በቸልሲ በጥብቅ ሲፈለግ የነበረው ኡራጊያዊው አጥቂ ኤዲሰን ካቫኒ በመጨረሻም አትሌቲኮ ማድሪድን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል በተቀሩት የዝውውር ቀናት ወደ አትሌቲኮ ማምራቱ እርግጥ ሆኗል።




ጁቬንቱስ ወጣቱን አማካይ ኢንዞ ባሬንቻን ዝውውር ለማጠናቀቅ ከጫፍ ደርሰዋል።




ማርኮስ ሮኾ ወደ ሀገሩ ክለብ ኢስቱዴንቴ በውሰት ውል ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል ዩናይትዶች ልጁን ለመሸጥ ቢፈልጉም እስካሁን ገዢ አደለሁም።





አርሰናሎች የፓብሎ ማሪን ዝውውር ዛሬ አልያም ነገ ይፋ ያደርጋሉ ተጨዋቹ የጤና ምርመራውን ዛሬ እንደሚያደርግ ለክለቡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ዘግበውታል።




የዩናይትድ ተጨዋቾች በቦርዱ የተተወ አይነት ስሜት እየተሰማቸው ነው ምክንያቱ ደሞ ቦርዱ ሉካኩን እና ሳንቼዝን እና ሄሬራን ሲለቅ ሌላ ተጨዋች አለመተካቱ ነው በተጨማሪም ሀላንድን በዚህ የዝውውር መስኮት አለማስፈረማቸው ነው።




ክሪስቲያን ኤሪክሰን ዛሬ ዝውውሩን ለመጨረስ ወደ ጣሊያን ያመራል ሜዲካሉን ዛሬ ካደረገ ቡሀላ በይፋ የኢንተር ሚላን ንብረት ይሆናል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...