Saturday, January 25, 2020

የዕለተ እሁድ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

                   አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ




የዩናይትድእና ስፖርቲንግ ባለስልጣናት በብሩኖ ጉዳይ ትላንት በስልክ ተወያይተዋልዛሬም ንግግሩ ይቀጥላል ዩናይትዶች ለመጨረሻ ጊዜ ላቀረቡት 55ሚ. እና 10ሚ. እየታየ ሚጨመር ጥያቄ ከስፖርቲንጎች መልስ እየጠበቁ ነው።




አርሰናል ፓብሎ ማሪን ለማስፈረም እየሰራ ያለው እስከሲዝኑ መጨረሻ በውሰት ክረምት ላይ ቋሚ የሚደረግበት እድል የተካተተበት ነው ተብሏል።



ኤምሪ ካን ጁቬንቱስን በመልቀቅ ቦሩሲያ ዶርትመንድን ለመቀላቀል ንግግር መጀመሩ ይፋ ተደርጓል።




ጄርሜንዴፎ በርንማውዝን በመልቀቅ ሬንጀርስን በአንድ አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ተደርጓል።



አርቢሌብዢኮች በተለያዩ ክለቦች ሲፈለግ የነበረውን ስፔናዊውን የ21 አመት አማካይ ዳኒ ኦልሞን ከዳይናሞ ዛግሬብ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።





ኢንተር ሚላን እና ናፖሊ በማቲዮ ፖሊታኖ ዝውውር ጉዳይ ከስምምነት ደረሱ ተጨዋቹ ወደ ናፖሊ ሚያመራው በውሰት ነው ሰኞ የጤና ምርመራ እንደሚያደርግ ታውቋል።




ኤሲ ሚላኖች የቤኔፊካውን ተጫዋች ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ 18 ወራት ለሚቆይ የውሰት ውል ለማስፈረም ይፈልጋል ቤኔፊካ በውሰት የሚሰጥ ከሆነ £50m የመግዛት አማራጭ ጋር ነው የሚፈልገው።




ፓውሎዲባላ  ጁቬንቱስን ለመልቀቅ ተቃርቧል ዲባላ ስሙ ከዩናይትድ እና ከቶተንሀም ጋር በስፋት እየተያያዘ ይገኛል።

2 comments:

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...