አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
የሀገር ውስጥ ዜናዎች
ዛሬ እና ነገ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚደረጉ ጨዋታዎች መርሃ ግብር
ቅዳሜ
ስሑል ሽረ ከ ጅማ አባ ጅፋር - 9:00ሰበታ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ - 9:00
ወላይታ ድቻ ከ መቐለ 70 አ. - 9:00
እሁድ
ወልቂጤ ከተማ ከ ድሬደዋ ከተማ - 9:00
አዳማ ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና - 9:00
ፋሲል ከተማ ከ ሲዳማ ቡና - 9:00
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ባህር ዳር ከተማ - 9:00
ወልዋሎ ዓ.ዩ. ከ ኢትዮጵያ ቡና - 9:00
ምንጭ -ሶከር ኢትዮጵያ
የውጭ ሀገር ዜናዎች
የቶተንሃሙ አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ኢንተር ሚላንን ለመቀላቀል በቀጣዩ ሳምንት ለህክምና ምርመራ ወደ ሚላን እንደሚያመራ ይጠበቃል።ዴንማርካዊው ኢንተርናሽናል በጣሊያኑ ክለብ ሳምንታዊ £320,000 ደሞዝ እንደሚከፈለውም ተነግሯል።
(Sky Sports)
ማንቸስተር ዩናይትድ በቀጣይ ሳምንት ከዎልቭስ ጋር በሚኖረው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ደጋፊዎች የግሌዘር ቤተሰቦችን እና ኢድ ውድ ዋርድን በመቃወም ጨዋታው ሳይጠናቀቅ ከስቴዲየሙ ለመውጣት አቅደዋል።
(Mirror)
ሱዋሬዝን በጉዳት ለወራት ያህል ያጣው ባርሴሎና ምናልባትም አስገራሚ በሆነ መልኩ ፈረንሳዊውን የቼልሲ አጥቂ ኦሊቪየር ዥሩ ሊያዘዋውር ይችላል።
(Independent, via Mail)
አርሰናል ፈረንሳዊውን የክንፍ አጥቂ ቶማስ ሌማር ለማዘዋወር በአዲስ መልኩ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ድርድር ጀምሯል።
(RMC Sport, via Talksport)
ቶተንሃም የኤሲ ሚናኑን ፖላንዳዊ አጥቂ ፒያቴክ ለማዘዋወር ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም።ስፐርስ ለተጨዋቹ ዝውውር £30ሚ. አቅርቦ የነበረ ሲሆን ምናልባትም በዝውውር መስኮቱ መዝጊያ ግን ሊሳካ የሚችልበት ዕድል አለ።
(Star)
ሮማ ቤልጄሚያዊውን የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ በአሁኑ ሰዓት ሪያል ሶሴዳድ የሚገኘውን የክንፍ አጥቂ አድናን ያኑዛይ ለማዘዋወር እየሰራ ይገኛል።
(Calciomercato)
ብራዚላዊው ጋብሬል ማርቲኔሊ በሪያል ማድሪድ መፈለጉን ተከትሎ አርሰናል የተጨዋቹን ደሞዝ ሶስት እጥፍ በማሳደግ ሳምንታዊ £30,000 ሊያደርግለት አቅዷል።
(Mail)
ቶተንሃም ኬንያዊውን አማካይ ቪክቶር ዋኒያማ የሚገዛው እምብዛም ባለማግኘቱ ተጨዋቹን ከ£7ሚ. በታች ለመሸጥ ወስኗል።
(Standard)
ሊቨርፑል በባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ በጥብቅ የሚፈልገውን የቤኔፊካውን ፖርቱጋላዊ ታዳጊ ራፋኤል ብሪቶ ለማዘዋወር የተጨዋቹን የውል ማፍረሻ £38ሚ. ለመክፈል ተሰናድቷል።
(Record via Star)
No comments:
Post a Comment