አቅራቢ- አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
የቼልሲው አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ከክለቡ አመራሮች ጋር በግብ ጠባቂው ኬፓ አሪዛባላጋ ቆይታ ዙሪያ አለመግባባታቸውን ሚረር አስነብቧል።
(Mirror)
እንግሊዛዊው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋች ሄሴ ሊንጋርድ ከክለቡ የሚለቅ ከሆነ አትሌቲኮ ማድሪድ ወይም ሮማ ማረፊያው እንደሚሆን ይጠበቃል።
(ESPN)
በሊቨርፑል ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ በጥብቅ የሚፈለገው ቲም ወርነር "ወደ ተገቢው ክለብ ለመዘዋወር" እንደሚፈልግ ተናግሯል።ጀርመናዊው አጥቂ በዘንድሮው አመት በሁሉም የውድድር አይነቶች ለራ.ቢ ሌብዚኽ 25 ግቦችን አስቆጥሯል።
(Kicker - via Evening Standard)
ዌልሳዊው የሪያል ማድሪድ አጥቂ ጋሬዝ ቤል ሎስብላንኮዎቹን ሲለቅ ከፕሪሚየር ሊግ ይልቅ ወደ ሜጀር ሊግ ሶከር አሊያም ወደ ቻይና ሱፐር ሊግ ሊጓዝ የሚችልበት ዕድል ሰፊ ነው።
(Star)
አርሰናል እና ኤቨርተን በጥር ወሩ የዝውውር መስኮት የሊሉን ተከላካይ ጋብሬል ለማዘዋወር ሞክረው ሳይሳካ ቀርቷል።
(Le10Sport - in French)
ሰሞኑን ከአሰልጣኙ ቶማስ ቱሀል ጋር የተጋጨው የፓሪሰን ዤርመኑ አጥቂ ኪልያን ምባፔ ወኪል ፈረንሳዊው ተጨዋች ከክለቡ እንደማይለቅ ተናግሯል።ሆኖም የ21 አመቱ ኮከብ ስም በስፋት ከሪያል ማድሪድ ጋር በመያያዝ ላይ ይገኛል።
(Mundo Deportivo - in Spanish)
የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ሌጀንድ ሪያን ጊግስ ቀያይ ሰይጣኖቹ ፖርቱጋላዊውን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ማዘዋወራቸው መልካም እንደሆነ ተናግሯል።
(Sun)
ሊቨርፑል ለሆላንዳዊው ተከላካይ ቫርጅል ቫን ዳይክ እና ብራዚላዊ ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር አዲስ ኮንትራት አቅርቦላቸዋል።ተጨዋቾቹ በሊቨርፑል ቤት ቁልፍ ሚና እንዳላቸው ይታወቃል።
(Independent)
ኢንተር ሚላን አልጄሪያዊውን አጥቂ ኢስላም ስሌማኒ ከሌስተር ሲቲ ለማዘዋወር ተቃርቧል።አንቶኒዮ ኮንቴ ቡድኑን ለማጠናከር በርካታ ተጨዋቾችን በማስፈረም ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።
(Calciomercato - in Italian)
No comments:
Post a Comment