Tuesday, February 4, 2020

የዕለተ ማክሰኞ ምሽት ስፖርታዊ ዜናዎች


አቅራቢ  - ኢብራሒም ሙሐመድ




M.E.Nዛሬከሰአት ባወጣው መረጃ ከሆነ ፖል ፖግባ በክረመቱ የዝውውር መስኮት ከዩናይትድ መልቀቁ አይቀሬ እንደሆነ አስነብቧል።




በቸልሲቦርድእና በፍራንክ ላምፓርድ መካከል በስፔናዊው ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ ጉዳይ አለመግባባታቸው ታውቋል ላምፓርድ ተጨዋቹ እንዲሸጥ ይፈልጋል።




ባሳለፍነውሳምንትክሊያን ምባፔ እና አሰልጣኙ ተቀይሮ ሲወጣ መጋጨታቸው ይታወሳል ሆኖም አንዳንድ ጋዜጦች ልጁን ከሊቨርፑል እና ከማድሪድ ጋር ስሙን ሲያያዙ ቆይተዋል አሁን ላይ ግን ወኪሉ እንደተናገረው ከሆነ ምባፔ ከክለቡ እንደማይለቅ ተናገረ።




ዌልሳዊውየማድሪድአጥቂ ጋሪዝ ቤል ከማድሪድ ሲለቅ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከማምራት ይልቅ ወደ አሜሪካው ሜጀር ሊግ ሶከር ወይም ወደ ቻይና ሊጓዝ እንደሚልግ ተሰምቷል።




በጉዳትእየተቸገረየሚገኘው ኡስማን ዴምቤሌ በልምምድ ላይ ሳለ በድጋሚ ጉዳት አስተናግዷል  የጉዳቱ መጠን ባይታወቅም ጉዳቱ ግን በድጋሚ የጡንቻ መሳሳብ እንደሆነ ተነግሯል።




በተደጋጋሚከባርሴሎናጋር ስሙ እየተነሳ የሚገኘው ብራዚላዊው ኮከብ ዊሊያን ኮንትራቱ በዚህ አመት ይጠናቀቃል ሆኖም ዊሊያን ወደ ባርሴሎና ከማምራት ይልቅ በቸልሲ በተጨማሪ አዲስ ኮንትራት ለመፈረም ፍላጎት አለው።




በጉዳትለረጅምጊዜያት የራቀው ፖግባ እና በፈረንጆቹ አዲስ አመት ዋዜማ ላይ ጉዳት ያስተናገደው ስኮት ማክቶሚናይ ለስታንፎርዱ ብሪጅ ጨዋታ እንደሚደርሱ ሶልሻየር አረጋግጧል።



ጄራርድ ፒኬ እሁድ እለት ሌቫንቴን ሲያሸንፉ ቢጫ ካርድ ተመልክቶ ነበር ይህንንም ተከትሎ በቀጣይ ባርሴዎና ሪያል ቤትስን ሲገጥም በቅጣት ማይኖር ይሆናል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...