Tuesday, February 4, 2020

የዕለተ ረቡዕ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)



ዛሬ ክርስቲያኖ ሮናልዶ 35ተኛ አመቱን ደፍኗል።እስቲ ስለዚህ ፖርቱጋላዊ አንድ ሁለት እንበል ……

ከእያንዳንዱ ስኬታማ ሰው ዛሬ ጀርባ በርካታ ከባድ እና አታካች ትናንቶች አልፈዋል።

አስተዳደጉ በፈተናዎች የተሞላ ነበር።ምግብ ከበርገር ቤት ለምኖ ከጓደኞቹ ጋር የተመገበባቸው ቀናት እልፍ ነበሩ።በአስራዎቹ አጋማሽ ሳለም ከባድ የልብ ህመም አጋጥሞት 'ከዚህ በኋላ እግር ኳስን እርም በል' ቢባልም በእናቱ አጋዥነት ከቀዶ ጥገና በኋላ በርትቶ በመስራት አሁን ያለበት ደረጃ ደርሷል።ታዳጊ ሳለ ለጓደኞቹ 'አንድ ቀን የዓለማችን ምርጡ ተጨዋች እሆናለሁ' ሲላቸው አፊዘውበታል ፥ አሁን በዚህ ሀሳብ የሚስማሙ ሚሊየኖች ናቸው።
ይህ አሁን በሰውነቱ ቅርጽ ብዙዎች የሚደመሙበት ሰው በታዳጊነቱ ጓደኞቹ በቀጫጫነቱ የሚሳለቁበት ሰው ነበር።

አሁን ይህ ሰው በግሉም ፣ ከክለብ ጋር እንዲሁም ከሀገሩ ጋር ስሙን በወርቅ ብዕር ጽፏል።የአምስት ባሎንዶሮች እንዲሁም የእልፍ አዕላፍ ስኬቶች ባለቤት ነው።አለም ላይ እግርህ እስኪኳትን ብትዞር 'ክርስቲያኖ ሮናልዶ' የሚለው ስም የማይታወቅበት ሀገር ልታገኝ አትችልም።

ዛሬ ሮናልዶ 35ተኛ አመቱን ያከብራል።ይህ ከሜዳ ውጪ በሰብዓዊነቱ እጅጉን የሚሞገሰው ፖርቱጋላዊ እግር ኳስን ሊሰናበት ጥቂት አመታት ብቻ እንደቀሩት ስናስብ ልባችንን ሀዘን ይሞላዋል።

መልካም ልደት ፥ ክርስቲያኖ!



የዝውውር ዜናዎች



ፈረንሳዊው የማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ ፖል ፖግባ ለቡድን አጋሮቹ አሁንም ቀያይ ሰይጣኖቹን መልቀቅ እንደሚፈልግ እና በጥር ወሩ የዝውውር መስኮት እንደሚሆንም ነግሯቸዋል።
(Manchester Evening News)





ጁቬንትስ ጀርመናዊውን የማንቸስተር ሲቲ የክንፍ አጥቂ ለሮይ ሳኔ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር ዕቅድ አለው።የ24 አመቱ  ተጨዋች በባየርን ሙኒክም ይፈለጋል።
(Calcio Mercato, via Inside Futbol)





የቼልሲ ማኔጅመንት ለፍራንክ ላምፓርድ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት £150ሚ. ለተጨዋቾች ዝውውር የሚበጅትለት ሲሆን ዋነኛው የላምፓርድ ዕቅድ ደግሞ የሊዮኑ ፈረንሳዊ አጥቂ ሞሳ ዴምቤሌ ነው።
(Evening Standard)





በዘንድሮው አመት የመሀል ተከላካይ ክፍሉ የሳሳው ማንቸስተር ሲቲ ሁለት ተከላካዮችን ለማስፈረም አቅዷል።በጆን ስቶንስ አቋሚ ደስተኛ ያልሆነው ፔፕ ጋርዲዮላ ዋነኛ ለማጠናከር የሚፈልገው ስፍራ ተከላካይ መስመሩን ነው።
(Times, subscription required)





የዌልሳዊው የሪያል ማድሪድ ኮከብ ጋሬዝ ቤል ወኪል ለ30 አመቱ ተጨዋች በጥር ወር የዝውውር መስኮት ከቶተንሃም ምንም አይነት የዝውውር ጥያቄ እንዳልቀረበ ተናግሯል።
(Talksport)





በተደጋጋሚ ከባርሴሎናጋር ስሙ እየተነሳ የሚገኘው ብራዚላዊው ኮከብ ዊሊያን ኮንትራቱ በዚህ አመት ይጠናቀቃል ሆኖም ዊሊያን ወደ ባርሴሎና ከማምራት ይልቅ በቸልሲ በተጨማሪ አዲስ ኮንትራት ለመፈረም ፍላጎት አለው።






በጉዳትለረጅምጊዜያት የራቀው ፖግባ እና በፈረንጆቹ አዲስ አመት ዋዜማ ላይ ጉዳት ያስተናገደው ስኮት ማክቶሚናይ ለስታንፎርዱ ብሪጅ ጨዋታ እንደሚደርሱ ሶልሻየር አረጋግጧል።





ጄራርድ ፒኬ እሁድ እለት ሌቫንቴን ሲያሸንፉ ቢጫ ካርድ ተመልክቶ ነበር ይህንንም ተከትሎ በቀጣይ ባርሴሎና ሪያል ቤትስን ሲገጥም በቅጣት ማይኖር ይሆናል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...