Wednesday, February 5, 2020

የዕለተ ሐሙስ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅርቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ





እንግሊዛዊው ኮከብ ሀሪ ኬን ወደ ሜዳ የመመለሻው ጊዜ ከታሰበበት ጊዜ እንደሚዘገይ ተረጋግጧል ኬን ለ2020 የአውሮፓ ዋንጫ የመድረስ እድሉ ሰፊ ሲሆን ለቶተንሀም ግን በዚህ አመት ግልጋሎት ላይሰጥ ይችላል።





ማርኮ ሪዩስ ዶርትመንዶች ከፒኤስጂ ጋር ላለባቸው የቻምፒየንስ ሊግ አንደኛ ዙር ጨዋታ አይደርስም ዶርትመንድ ማክሰኞ እለት በብሬመን ሲሸነፍ ጉዳት ያስተናገደው ሮይስ እስከ አራት ሳምንት ከሜዳ ይርቃል።




ለረጅም ጊዜ በጉዳት ምክንያት የራቀው ወጣቱ የቸልሲ አማካይ ሩበን ሎፍተስቺክ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተረጋግጧል ባሳለፍነው ሳምንትም ከB ቡድኑ ጋር ልምምድ እና ቼልሲ ከብሬድፎርድ B ቡድን ጋር ባደረገው ጨዋታ ተሰልፏል።




አትሌቲኮ ማድሪዶች ከቶተንሀም ከለቀቁ ቡሀላ ያለ ስራ የተቀመጡትን ማውሪሲዮ ፖቸቲንሆን ዳግም ወደ ስፔን ለመመለስ ፍላጎት አላቸው ከዲያጎ ሲሞኒ ጋር ኮንትራት ቢኖራቸውም የሲሞኒን ኮንትራት ክረምት ላይ በማቋረጥ ፖቸቲትሆን መቅጠር ይፈልጋሉ።




ሪያል ማድሪዶች የፈረንሳዊውን ኮከብ ኪሊያን ምባፔ የመሸጫ ዋጋ እስኪቀንስ እንደሚታገሱት እና ልጁን 2021 ላይ £150m ብቻ ከፍለው እንደሚያስፈርመት ተማምነዋል።





ጣሊያናዊው የቸልሲ አማካይ ጀርጊንሆ ከናፖሊ ወደ ቼልሲ ያመጡትን ማውሪዚዮ ሳሪን በድጋሚ አብሯቸው ለመስራት ወደ ጁቬንቱስ ለመዘዋወር እንደሚፈልግ ተሰምቷል።




ጀርመናዊውየሲቲየመስመርተጨዋች ሊሮይ ሳኔ በክረምቱ የዝውውር በጥብቅ ወደ ሚፈልገው ክለብ ባየርን ሙኒክ መዘዋወር እንደሚፈልግ ለጓደኞቹ ነግሮዋቸዋል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...