አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
የ2020/2021 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ይፋ ሆኗል ቀኑም ነሀሴ2 በእለተ ቅዳሜ እንደሚጀመር ይፋ ሲደረግ ነሀሴ 26 ደሞ የዝውውር መስኮት እንደሚጠናቀቅ ይፋ ተደርጓል።
ባርሴሎናዎች የጌታፌውን አጥቂ አንጀል ሮድሪጌዝን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል ባርሳዎች የኡስማን ዴምቤሌን ተደጋጋሚ ጉዳት ተከትሎ ተጨዋቹን ማስፈረም ፈልገዋል።
ማንችስተር ሲቲዎች በሊሮይ ሳኔ ዝውውር ላይ ተስፋ ቆርጠዋል ተጨዋቹ አዲስ ወኪል መያዙ ይፋ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ሳኔም ወኪሉን የቀየረው ክረምት ላይ የባየርን ሙኒኩን ዝውውሩን ስላላጠናቀቀለት ነበር ።
አንድሬያ ርሞሌንኮ በክረምት ዌስትሀምን ለመልቀቅ ተቃርቧል ተጨዋቹ ተደጋጋሚ ጉዳት እና እድሜ ተጨምሮበት እንዲሁም ሞይስ ዌስትሀምን በወጣት ተጨዋቾች ለመገንባት ማሰቡን ተከትሎ ልጁ ሊለቅ ነው።
የዶርትመንዱ ሊቀመንበር ማይክል ዞርክ በጥር ላይ ስሙ በተደጋጋሚ ከቸልሲ እና ከዩናይትድ ጋር ሲያያዝ ስለነበረው ጄደን ሳንቾ ተጠይቀው ጥር ላይ ምንም አይነት ጥያቄ እንዳልቀረበላቸው ይፋ አድርገዋል ።
ማንችስተር ሲቲዎች በክረምቱ ሶስት ተጨዋቾች ለማስፈረም ሚፈልጓቸውን ተጨዋቾች ይፋ ሲያደርጉ ሮቢን ኔቬስን ከወልቭስ ካሊዱ ኩሊባሊን ከናፖሊ ኤርሊንግ ሀላንድን ከዶርትመንድ መሆናቸው ታውቋል።
የአርሰናሉአሰልጣኝ ማይክል አርቴታ ከ2020 የአውሮፓ ዋንጫ በፊት ሶስት ተጨዋቾችን እንዲያስፈርሙላቸው እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
ወልቭሶች ለአዳማ ትራኦሬ ሪከርድ የሆነ የግዢ ጥያቄ ሚቀርብላቸው ከሆነ ለመሸጥ ዝግጁ ሆነዋል።
No comments:
Post a Comment