Friday, February 7, 2020

የዕለተ አርብ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)



ማንቸስተር ዩናይትድ ለፖል ፖግባ ከዚህ በፊት ከመደበው ገንዘብ ላይ £30ሚ. መቀነሱ ታውቋል።በኦልድ ትራፎርድ ደስተኛ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ የተነገረለት ፈረንሳዊ ኢንተርናሽናል አሁን የመ'ሸጫ ዋጋው ወደ £150ሚ. ዝቅ ብሏል።
(Sun)





አዲሱ የአርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ስኳዱን ለማጠናከር በቅርቡ የአሌክሳንደር ላካዜት ፣ ሜሱት ኦዚል እና ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ ጉዳይን መስመር ማስያዝ ይፈልጋል።
(Sun)





ባርሴሎና በቀጣዩ የዝውውር መስኮት የዎልቭሱን አጥቂ አማዳ ትራኦሬ ለማዘዋወር ይፈልጋል።ትራኦሬ ላማሲያ ውስጥ ማደጉ ይታወሳል።
(Mail)





አርጀንቲናዊው የኢንተር ሚላን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ከባርሴሎና ይልቅ ማንቸስተር ዩናይትድን አሊያም ማንቸስተር ሲቲን መቀላቀል ይፈልጋል።
(Star)





ፍራንክ ላምፓርድ በኬፓ አሪዛባልጋ ደስተኛ ባለመሆኑ ካሜሮናዊውን የአያክስ ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና ለማዘዋወር ይፈልጋል።
(Goal.com)



ስሙ ከፓሪሰን ዤርመን ጋር በስፋት ሲያያዝ የሰነበተው ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ ታዳጊ ቪኒሺየስ ጁኒየር በሳንቲያጎ በርናቢዮ መቆየት እንደሚፈልግ ተናግሯል።የ19 አመቱ ብራዚላዊ 2018 ላይ ነበር ሎስብላንኮዎቹን የተቀላቀለው።
(Goal)





በአመቱ መጨረሻ በሊቨርፑል ያለው ውል የሚጠናቀቀው አዳም ላላና ከቀድሞው አሰልጣኙ ብሬንደን ሮጀርስ ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ተዘግቧል።ይህም የሚሆነው ደግሞ እንግሊዛዊው አማካይ ወደ ሌስተር ሲቲ ከተዘዋወረ ነው።
ላላናን ከሌስተር በተጨማሪ ቶተንሃም ፣ አርሰናል እና ዌስት ሀም ይፈልጉታል።
(The Telegraph)





የ2020/2021 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ይፋ ሆኗል ቀኑም ነሀሴ2 በእለተ ቅዳሜ እንደሚጀመር ይፋ ሲደረግ ነሀሴ 26 ደሞ የዝውውር መስኮት እንደሚጠናቀቅ ይፋ ተደርጓል።




ባርሴሎናዎች የጌታፌውን አጥቂ አንጀል ሮድሪጌዝን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል ባርሳዎች የኡስማን ዴምቤሌን ተደጋጋሚ ጉዳት ተከትሎ ተጨዋቹን ማስፈረም ፈልገዋል።




ማንችስተር ሲቲዎች በሊሮይ ሳኔ ዝውውር ላይ ተስፋ ቆርጠዋል ተጨዋቹ አዲስ ወኪል መያዙ ይፋ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ሳኔም ወኪሉን የቀየረው ክረምት ላይ የባየርን ሙኒኩን ዝውውሩን ስላላጠናቀቀለት ነበር ።







No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...