አቅራቢ - ኢብራሒም ሙሐመድ
አርሰናሎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቱርካዊውን አማካይ ኡርኩን ኮኩን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው ባሳለፍነው ሳምንት መልማዮችን ወደ ሆላንድ በመላክ ልጁን መመልከታቸው ተሰምቷል።
በጉዳት ምክንያት በቶተንሀሙ ጨዋታ ላይ ተቀይሮ የወጣው ራሂም ስተርሊንግ ከጉዳቱ ባለማገገሙ ከእሁዱ የኢትሀዱ የዌስትሀም ጨዋታ ውጭ መሆኑን ፔፕ ይፋ አድርጓል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የጥር ወር ኮከቦችን ይፋ አድርጓል በኮከብ አሰልጣኝነት የርገን ክሎፕ በኮከብ ተጨዋችነት ኩን አጉዌሮ እንዲሁም በምርጥ ጎል የብራይተኑ አሊሬዛ ጃሀንባካሽ ሆነው ተመርጠዋል።
ሪያል ማድሪድ እና ባርሴሎና በ24 አመቱ የወልቭስ የመስመር አጥቂ አዳማ ትራኦሬ ዝውውር ላይ ተፋጠዋል ወልቭሶች ከልጁ እስከ £90m ይፈልጋሉ።
ዩናይትዶች በክረምቱ አጥቂ ለማስፈረም ወደ ገበያ እንደሚወጡ እውን ሆኗል ዩናይትዶችም ዋና ኢላማ ያረጉት ላውታሮ ማርቲኔዝ ላይ ትኩረት አድርገዋል ኢንተር ሚላኖች ከተጨዋቹ እስከ £94m ይፈልጋሉ።
ቡድኑን በአዲስ መልክ ለመገንባት እቅድ ያለው የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሶስት ቋሚ ተጨዋቾችን ለሽያጭ አቅርበዋል ተጨዋቾቹም ኦዚል ላካዜቲ ኦባምያንግ ናቸው።
ጁቬንቱሶች ከትናንት ጀምሮ ከባርሴሎና ጋር ሊለያይ ነው የተባለውን ሊዮኔል ሜሲ ለማስፈረም ይፈልጋሉ። ሜሲን ለማስፈረም ብዙ ገንዘብ ቢያስፈልግም ጁቬዎች ግን ያወጣውን አውጥተው ሜሲን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።
ቶተንሀሞች የፊት መስመር ተጨዋቹን ትሮይ ፓሮትን ኮንትራት አራዝመዋል በአዲሱ ውል መሰረት ትሮይ ፓሮት እስከ 2023 በቶተንሀም ይቆያል።
No comments:
Post a Comment