Saturday, February 8, 2020

የዕለተ ቅዳሜ ስፖርታዊ ዜናዎች

           አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

የሀገር ውስጥ ዜናዎች
የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ በዚህ ሳምንት ሲቀጥል የተለያዩ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።የ13ተኛውን ሳምንት ሙሉ ፕሮግራም እነሆ :

ቅዳሜ
መቐለ 70 አ. ከ ፋሲል ከነማ - 9:00

እሁድ
ሀዋሳ ከተማ ከ ጅማ አባ ጅፋር - 9:00
ወልዋሎ ዓ.ዩ. ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ - 9:00
ድሬደዋ ከተማ ከ ስሑል ሽረ - 9:00
ባህር ዳር ከተማ ከ ሰበታ ከተማ - 9:00

ሰኞ
ሲዳማ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ - 9:00

ማክሰኞ
ሀዲያ ሆሳዕና ከ ወላይታ ድቻ - 9:00

ሐሙስ
ኢትዮጵያ ቡና ከ ወልቂጤ ከተማ

ምንጭ  - ሶከር ኢትዮጵያ




የውጭ ስፖርታዊ ዜናዎች



በበርካታ ሀያላን ክለቦች የሚፈለገው ሴኔጋላዊው የናፖሊ ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ በአመቱ መጨረሻ በተለይ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ የመሄድ ዕድሉ ከፍተኛ ነው።
(Star)





ባርሴሎና በውሰት ለባየር ሙኒክ ሰጥቶት የነበረውን ብራዚላዊውን አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ በአመቱ መጨረሻ መሸጥ ይፈልጋል።የዝውውር ዋጋውም £67ሚ. እንደሚሆን ተጠቅሷል።
(Mundo Deportivo - in Spanish)






ቼልሲ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት አርጀንቲናዊውን የኢንተር ሚላን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ እና የሊዮኑን ፈረንሳዊ አጥቂ ሞሳ ዴምቤሌ ለማዘዋወር ይሰራል።
(Evening Standard)





ባርሴሎና የቀድሞውን ተጨዋቹን አዳማ ትራኦሬን ከዎልቭስ ለማዘዋወር ፍላጎት ያለው ቢሆንም ሪያል ማድሪድ ሳንካ እንዳይሆንበት ይሰጋል።
(Mail)






ቦሩሲያ ዶርትመንድ እንግሊዛዊውን አጥቂ ጄደን ሳንቾ ከዩሮ 2020 በፊት መሸጥ አይፈልግም።ምክንያቱ ደግሞ የ19 አመቱ ተጨዋች ከውድድሩ በኋላ ዋጋው ከፍ ይላል በሚል ግምት ነው።
(90min)





ሊቨርፑል በአመቱ መጨረሻ ኮንትራቱ ለሚያበቃው እንግሊዛዊው አማካይ አዳም ላላና አዲስ ኮንትራት አላቀረበለትም።በዚህም ይህ አመት ሲያልቅ ወደ ፈለገበት ክለብ በነጻ የሚጓዝ ይሆናል።
(Liverpool Echo)





ቼልሲ የእንግሊዛዊውን የ18 አመት አማካይ ቲኖ አንጆሪን እና የሆናላንዳዊውን የ17 አመት ታዳጊ ተከላካይ ላን ማትሰን ውል ለማራዘም በመስራት ላይ ነው።
(Mail)





ጁቬንትስ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር በጥብቅ ከሚፈልጋቸው ተጨዋቾች መሀከል የቼልሲው ጣሊያናዊ የግራ መስመር ተከላካይ ኤመርሰን ፓልሜሪ አንዱ ነው።
(Inside Futbol)

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...