አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)
ትናንት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተደረገ ጨዋታ ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ፈታኙን ዎልቭስ በቫን ዳይክ እና ፈርሚንሆ ጎሎች ማሸነፍ ችሏል።በዚህም ሊቨርፑል ለተከታታይ 40 የሊግ ጨዋታዎች አልተሸነፈም።ማንቸስተር ዩናይትድ የቀድሞው ተጨዋቹን አርጀንቲናዊውን ኮከብ ካርሎስ ቴቬዝ ለጥቂት ጊዜ ሳይጠበቅ ሊያዘዋውረው አቅዷል።ቴቬዝ አሁን 35ተኛ አመቱ ላይ ሲገኝ በሀገሩ ክለብ ቦካ ጁኒየርስ በመጫወት ላይ ይገኛል።
(Tuttosport)
ቶተንሃም ዴንማርካዊውን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ለኢንተር ሚላን በ£20ሚ. ለመሸጥ በመርህ ደረጃ ተስማምቷል።ኤሪክሰን በተለይ ከጆዜ ሞሪንሆ ጋር እምብዛም አለመስማማቱ ከክለቡ እንዲለቅ ምክንያት ሳይሆነው እንዳልቀረ ይገመታል።
(Sempreinter.com)
ቼልሲ በድጋሚ ፈረንሳዊውን አጥቂ ሞሳ ዴምቤሌ ከሊዮን ለማዘዋወር ጥረት ማድረግ ጀምሯል።ሰማያዊዎቹ የ23 አመቱ አጥቂ ከዚህ በፊት ለማዘዋወር ሞክረው ባይሳካላቸውም አሁን የዝውውር ሂሳቡን ጨምረው ተጨዋቹን ስታንፎርድ ብሪጅ ለማክተም ወጥነው በመስራት ላይ ናቸው።
(Sun)
ማንቸስተር ዩናይትድ በተከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ኡራጋዊውን አጥቂ ኤዲንሰን ካቫኒ ከፓሪሰን ዤርመን ለማዘዋወር በመስራት ላይ ይገኛል።
(Telegraph)
ጋቦናዊው የአርሰናል አጥቂ ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ የካታላኑን ክለብ ባርሴሎና ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል ሲል የካታላኑ ጋዜጣ ሙንዶ ዲፖርቲቮ አስነብቧል።
(Mundo Deportivo - in Spanish)
ብሩኖ ፈርናንዴዝ ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ሊያደርገው የነበረው ዝውውር ያለ መስማማት ተጠናቋል።ምክንያቱ ደግሞ ክለቡ ስፖርቲንግ ሊዝበን የጠየቀውን £68ሚ. ማን ዩናይትድ ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው።
(Mail)
ሊቨርፑል ስፔናዊውን አማካይ ኢስኮ ከሪያል ማድሪድ ለማዘዋወር ፍላጎት አለው።ሎስብላንኮዎቹ ለተጨዋቹ £59ሚ. እንዲቀርብላቸው ይፈልጋሉ።
(El Desmarque - in Spanish)
ኢንተር ሚላን የናፖሊውን አጥቂ ፈርናንዶ ሊዮሬንቴ ለማዘዋወር ጥያቄ አቅርቧል።አንቶኒዮ ኮንቴ በዋናነት ሲፈልገው የነበረው የቼልሲውን ኦሊቪየር ዥሩ የነበረ ቢሆንም ባለመሳካቱ ፊቱን ወደ ሊዮሬንቴ አዙሯል።
( Sky Sports )
ቶተንሃም የሪያል ሶሴዳዱን ብራዚላዊ አጥቂ ዊልያን ሆዜ ለማዘዋወር እየሰራ ሲሆን የዝውውር ገንዘቡን በጥቂቱ ካሳደገ ተጨዋቹን የማግኘት ዕድሉ ሰፊ ነው።
( ESPN )
No comments:
Post a Comment