አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ከቶተንሀም በጥር አልያም በክረምት ሊለቅ እንደሚችል እየተነገረ የሚገኘውን ዳኒ ሮዝን ለማስፈረም ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ፍላጎት እንዳላቸው ተሰምቷል
ሌስተሮችየሳውዛንብተኑን ተከላካይ ጃኒክ ቬስትሬጋርድን ለማስፈረም እስከ £15m ለማውጣት ዝግጁ ሆነዋል በቀጣይ ሳምንት ዝውውሩ ሳይዘጋ ልጁን ለማምጣት እየሰሩ ነው
የጀደን ሳንቾ በብዙ ክለብ መፈለግ እና በክረምቱ ክለቡን መልቀቁ አይቀሬ መሆኑን ተከትሎ ዶርትመንዶች እሱን ለመተካት አይናቸውን ወደ ብራዚል ክለብ ኮከቦች ጥለዋል የግሬሜሮን ኤቨርተን እና የሳኦፖሎውን አንቶኒን ሳንቾን ለመተካት እጩ አርገዋቸዋል
ዌስትሀምዩናይትዶች የቀድሞውን ተጨዋቻቸውን ዲምትሪ ፓየትን መመለስ ይፈልጋሉ ነገር ግን ዝውውሩ የመሳካቱ እድል እጅግ የጠበበ መሆኑ ተሰምቷል
ማንችስተርዩናይትድ እና ባርሴሎና አርጀንቲናዊውን ኮከብ ላውታሮ ማሬቲኔዝን ለማስፈረም £100m ለማውጣት ፍቃደኛ ሆነዋል
ሲቪያዎችየሬንጀርሱን አጥቂ አልፍሪዶ ሞላሬስን በጥር የዝውውር መስኮት የማስፈረም ፍላጎት አላቸው
ኢንተርሚላኖች ዩናይትዶች ያቀረቡትን የማቲያስ ቬሲኖን የውሰት ዝውውር ጥያቄ ውድቅ አድርገውባቸዋል
ዌስትሀሞችበዚህ የዝውውር መስኮት የበርንማውዙን ሪያን ፍሬዘርን ማስፈረም ይፈልጋሉ ተጨዋቹ በዚህ የውድድር አመት ኮንትራቱን ይጨርሳል
አርሰናሎችዩክሬናዊውን ተከላካም ማትቪየንኮን ለማስፈረም ከሻካታር ዶኔስኮች ጋር ንግግር እንደጀመሩ የተጨዋቹ ወኪል ይፋ አድርጓል
ከትናንትምሽቱ የበርንሌ ሽንፈት ቡሀላ በርካታ ጫና እየደረሰበት የሚገኘው ሶልሻየር ከክለቡ ቦርድ ሙሉ ድጋፍ እንዳለው ስካይ ስፖርት አረጋግጫለው ብሏል
No comments:
Post a Comment