Thursday, January 23, 2020

የዕለተ ሐሙስ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

                   አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


ቶተንሃም የሪያል ሶሴዳዱን ብራዚላዊ አጥቂ ዊልያን ጆዜ ለማዘዋወር ድርድር ጀምሯል።የ28 አመቱ አጥቁ ለንግግር ወደ ለንደን ማምራቱም ታውቋል።ቶተንሃም አጥቂውን ሀሪ ኬንን በጉዳት ለአራት ወራት እንዳጣ ይታወቃል።
(AS)





ቼልሲ ኡራጋዊውን አጥቂ ኤዲንሰን ካቫኒ እስከ አመቱ መጨረሻ በውሰት ለመውሰድ ለፓሪሰን ዤርመን ጥያቄ አቅርቧል።ካቫኒ በበርካታ ክለቦች የሚፈለግ ሲሆን ወላጅ አባቱ አትሌቲኮ ማድሪድን ልጁ እንደሚቀላቀል ተናግሮ ነበር።
(Times - subscription required)





ፓሪሰን ዤርመን ፈረንሳዊውን ተከላካይ ላይቪን ኩርዛዋ ለአርሰናል ለመሸጥ €5ሚ. ጠይቋል።የ27 አመቱ ተከላካይ በፓርክ ደ ፕሪንስ ያለው ኮንትራት በአመቱ መጨረሻ ይጠናቀቃል።
(Telegraph)





ሪያል ማድሪድ ዌልሳዊውን አጥቂ ጋሬዝ ቤል ወደ ቀድሞው ክለቡ ቶተንሃም ለመመለስ በቂ ገንዘብ ከቀረበለት ፈቃደኛ ነው።
(Telegraph)






ባየርን ሙኒክ ፌሊፔ ኩቲንሆን በቋሚነት የማዘዋወር ዕድሉን መጠቀም አልፈለገም።ባየርን ሙኒክ ብራዚላዊውን አማካይ ከባርሴሎና በውሰት ሲወስድ ከፈለገ በቋሚነት ማዘዋወር እንደሚችል የሚጠቅስ ውሉ የነበረው ቢሆንም አሁን ግን ተጨዋቹን ማዘዋወር አይሻም።
 (Bild, via Mirror)





ስድስት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች እንግሊዛዊውን የቶተንሃም የግራ መስመር ተከላካይ ዳኒ ሮዝ ለማዘዋወር ጥያቄ አቅርበዋል።ሮዝ በተከፈተው የጥር ወር የዝውውር መስኮት ስፐርስን ሊለቅ እንደሚችል ይጠበቃል።
(Sky Sports)





በማንቸስተር ሲቲ በጥብቅ የሚፈለገው ዩክሬናዊውን የሻካታር ዶኔስክ ተከላካይ ሚኮላ ማትቪዬንኮ ከአርሰናል ጋር ድርድር መጀመሩን ወኪሉ ይፋ አድርጓል።
(Football London)





የአርሰናሉ የ18 አመት አጥቂ ጋብሬል ማርቲኔሊ በአመቱ መጨረሻ ውሉ ተሻሽሎ ደሞዙ አሁን ካለው ሶስት እጥፍ እንዲሆን ይፈልጋል።ማርቲኔሊ በሪያል ማድሪድ ይፈለጋል።
(Mail)





ባርሴሎና ጋቦናዊውን የአርሰናል አጥቂ ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ ለማዘዋወር በተደጋጋሚ ሞክሮ ባለመሳካቱ የቫሌንሲያውን  ስፔናዊ አጥቂ ሮድሪጎ ሞሬኖ በውሰት ለመውሰድ ከጫፍ ደርሷል።
(Sport)

1 comment:

  1. አረ የማንችስተር ዪናይትድ ምንም የለም ንገሩን

    ReplyDelete

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...