ማርከስ ራሽፎርድን በጉዳት ለሳምንታት ሚያጡት ዩናይትዶች ፊታቸውን ወደ ፖላንዳዊው የኤሲሚላን አጥቂ ፒያቴክ ማዞራቸውን የጣሊያን ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ
በክለቡ ባየርን ሙኒክ እንደማይፈለግ የተነገረውን ቦአቴንግን አርሰናሎች በዚህ የዝውውር መስኮት በውሰት ለማስፈረም ፍላጎታቸው ጨምሯል
ባሳለፍነው ሳምንት ከፒኤስጂ መልቀቅ እንደሚፈልግ ይፋ ያደረገውን ኤዲሰን ካቫኒን ለማስፈረም በርካታ ክለቦች ቢፈልጉም ቸልሲዎች ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ተቃርበዋል ለተጨዋቹ ቸልሲዎች የአንድ አመት ከግማሽ አመት ኮንትራት እና ዳጎስ ያለ ክፍያ አቅርበውለታል
የዴቪድ ቤካሙ ክለብ ኢንተር ሚያሚ የማንችስተር ሲቲውን አጥቂ ኩን አጉዌሮን በ2021 ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ ማስፈረም እንደሚፈልግ ታውቋል
ባየርን ሙኒክ የሪያል ማድሪዱን ቀኝ መስመር ተመላላሽ አልቫሮ ኦርዲዮዞላ በግማሽ አመት የውሰት ውል ዛሬ አስፈርመውታል
ሼፍልድ ዩናይትዶች በአርሰናል የሚፈለገውን ጆን ፍሌክ ላይ £20m ዋጋ ለጥፈውበታል
ባርሴሎናዎች የሱዋሬዝ መጎዳትን ተከትሎ አጥቂዎችን እየፈለገ ይገኛል የኢንተር ሚላኑን ላውታሮ ማርቲኔዝ የመጀመሪያ ምርጫቸው አርገውታል ኢንተር ለተጨዋቹ የጠየቁትን £110m ለመክፈል ፍቃደኛ ሆነዋል
በርንማውዞች የቀድሞውን የቸልሲ አጥቂ በርናንድ ትራኦሬን ከሊዮን ለማስፈረም ወደ £35m በማውጣት ልጁን ለማስረም ይፈልጋሉ
ሊቨርፑሎች በክለቡ የመሰለፍ እድል እየተሰጠው የማይገኘውን ዤርዳን ሻኪሪን በክረምቱ የዝውውር መስኮት ለመሸጥ ፍቃደኛ መሆናቸው ተረጋግጧል ለልጁም እስከ £25m ይፈልጋሉ ነገር ግን በዚህ የዝውውር መስኮት ልጁን የመሸጥ ፍላጎት የላቸውም
ማንችስተር ሲቲ እና ፒኤስጂ አዲሱ ፔርሎ እየተባለ የሚጠራውን የብሬሺያ አማካይ ሳንድሮ ቶናሊን ለማስፈረም በሚደረገው ፉክክር ውስጥ ገብተዋል ተጨዋቹ እስከ £40m ያወጣል
ክሪስቲያን ኤሪክሰን በይፋ ትናንትና ለቶተንሀሞች የልቀቁኝ ደብዳቤ አስገብቷል
No comments:
Post a Comment