Sunday, November 29, 2020

የዕለተ እሁድ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

ትናንት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተደረጉ ጨዋታዎች የተመዘገቡ ውጤቶች


ብራይተን 1-1 ሊቨርፑል

ማንቸስተር ሲቲ 5-0 በርንሌይ

ኤቨርተን 0-1 ሊድስ ዩናይትድ

ዌስት ብሮም 1-0 ሼፍልድ ዩናይትድ





አርሰናል በክለቡ ሪከርድ ዋጋ ያስፈረመውን ኮትዲቯራዊውን የመስመር አጥቂ ኒኮላስ ፔፔ ለመሸጥ ይፈልጋል።ከተለያዩ ክለቦችም ጥያቄ  እየጠበቀ ነው።

(Daily Star Sunday)






ብራዚላዊው አማካይ ፈርናንዲንሆ አዲስ ኮንትራት ስላልቀረበለት በአመቱ መጨረሻ ማንቸስተር ሲቲ እንደሚለቅ ይጠበቃል።

(Sunday Mirror)






ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ሪያል ማድሪድን ዳግም በጋላክቲኮስ የመገንባት ዓላማ ያላቸው ሲሆን በቅድሚያ 2021 ላይ ምባፔን 2022 ላይ ደግሞ ኤርሊንግ ሀላንድን ለማዘዋወር ከወዲሁ ዕቅድ አውጥተው እየሰሩ ነው።

(AS)






የባርሴሎናው ተከላካይ ዤራርድ ፒኪዌ ሜሲ በባርሴሎና ይቆያል ብሎ ተስፋ እንደሚያደርግ ተናግሯል።

(ESPN)






የኢንተር ሚላኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጁሴፔ ማሮታ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ዴንማርካዊው አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ከክለቡ እንደሚለቅ አረጋግጠዋል።

(Sky Sports)






የብራዚላዊው አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ ስም በስፋት ከዩቬንትስ ጋር ቢያያዝም ከባርሴሎና እንደማይለቅ ወኪሉ ይፋ አድርጓል።

(Mundo Deportivo - in Spanish)






አርጀንቲናዊው አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ ኢንተር ሚላንን መልቀቅ ይፈልጋል።ወኪሉ የሆነው ሆርጌ ሜንዴዝም አዲስ ክለብ እየፈለገ ይገኛል።ማንቸስተር ሲቲ ፣ ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ደግሞ የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።

(Marca)






 

Tuesday, November 24, 2020

የዕለተ ማክሰኞ ስፖርታዊ ዜናዎች

አዘጋጅ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች በዚህ ሳምንት የሚደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለት ስምንት ጨዋታዎች ይደረጋሉ 

 

ክራስኖዳር ከ ሲቪያ (2:55) 

ሬንስ ከ ቼልሲ (2:55) 

ቦሩሲያ ዶርትመንድ ከ ክለብ ብሩዥ (5:00) 

ላዚዮ ከ ዜኒት ፒተርስበርግ (5:00) 

ዳይናሞ ኪዬቭ ከ ባርሴሎና (5:00) 

ዩቬንትስ ከ ፍሬንካቭሮቭ (5:00) 

ማን ዩናይትድ ከ ኢስታንቡል ባሳክሄር (5:00) 

ፓሪ ሴንት ዤርመን ከ ሌብዚኽ (5:00)





በዘንድሮው ሲዚን ደካማ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው እና አዲስ ኮንትራት የፈረመው ፔፕ ጓርዲዮላ ፥ አዲስ ለመስራት ያሰበውን ቡድን ለማጠናከር ፥ የአስቶን ቪላውን እንግሊዛዊ አማካይ ጃክ ግሪሊሽ ለማዘዋወር ይፈልጋል። 

(Independent) 

 

 

 

 

 

የሊዮኔል ሜሲ እህል ውሃ በካምፕ ኑ እያበቃለት ይመስላል።ከአዲሱ አሰልጣኝ ሮናልድ ኪውመን ጋር እምብዛም ያልተጣጣመው ሜሲ ቀጣይ ማረፊያው ማንቸስተር ሲቲ እንደሚሆን እየተነገረ ነው። 

(Times - subscription only) 

 

 

 

 

 

በማን ዩናይትድ ተጠባባቂ ግብ ጠባቂ የሆነው ዲን ሄንደርሰን ከክለቡ መልቀቅ እንደሚፈልግ ሲነገር የቆየ ቢሆንም ኦሌ ጉናር ሶልሻየር ተጨዋቹ በኦልድ ትራፎርድ ይቆያል ብሏል። 

 (Sky Sports) 

 

 

 

 

 

ፍራንክ ላምፓርድ ፈረንሳዊው አጥቂ ኢሊቪየር ዢሩ ለቼልሲ ቁልፍ ተጨዋች መሆኑን ተናገረ።ዢሩ ከስታንፎርድ ብሪጅ እንደሚለቅ ሲነገር ቆይቷል። 

(Mirror) 

 

 

 

 

 

ምንም እንኳን የስፔናዊው አማካይ ኢስኮ ስም በብዛት ከማን ሲቲ እና አርሰናል ጋር ቢያያዝም ፥ ሪያል ማድሪድ እስካሁን ከየትኛውም ክለብ ይፋዊ ጥያቄ አይቀረበለትም። 

(AS) 

 

 

 

 

 

ቦሩሲያ ዶርትመንድ ዴንማርካዊውን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ከኢንተር ሚላን ማዘዋወር ይፈልጋል።ዶርትመንድ ከዚህ በፊት ቶተንሃም እያለም ኤሪክሰንን ይፈልገው ነበር። 

(Tuttermercatoweb - in Italian) 

 

 

 

 

 

ከሊድስ ጋር በነበረው ጨዋታ በቀይ ካርድ የተሰናበተው ኒኮላስ ፔፔ ላሳየው ያልተገባ ባሕሪ ይቅርታ ጠይቋል። 

(Sun)

 

Saturday, November 21, 2020

የዕለተ ቅዳሜ ስፖርታዊ ዜናዎች


 በዚዳን ስር በርካታ ጨዋታዎችን በተጠባባቂ ወንበር ላይ እያሳለፈ የሚገኘው ስፔናዊው ኮከብ ኢስኮ በጥር የዝውውር መስኮት ሪያል ማድሪድን መልቀቅ እንደሚፈልግ ማርካ አስነብቧል። ተጨዋቹ በተለያዩ የፕሪሚየር ሊግ እና የሴሪያው ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል። 





ጁቬንቱሶች የመሀል ሜዳ ክፍላቸውን ለማጠናከር አሁንም የተለያዩ ተጨዋቾችን እየተመለከቱ ይገኛሉ።Tuttosport እንዳስነበበው ከሆነ ጁቬዎች የሳሱሎውን የ22 አመት ተጨዋች ማኑኤል ሉካቶሊን በጥር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ከአሁኑ ለሳሱሎ ጥያቄ ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸው ተሰምቷል። 




ጀርመናዊው የጁቬንቱስ አማካይ ሳሚ ከዲራ በዚህ አመት ከኮንትራት ነፃ ሲሆን ወደ ሜጀር ሊግ ሶከር አልያም ወደ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ለማምራት መዘጋጀቱን የጀርመኑ ቢልድ አስነብቧል። 




በክረምቱ በብዛት ስሙ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ሲነሳ ቆይቶ በመጨረሻም እዛው በቦሩሲያ ዶርትመንድ የቆየው ጃደን ሳንቾ በቀጣዩ 2021 የክረምት የዝውውር መስኮት ዶርትመንድን መልቀቅ እንደሚፈልግ Todofichajes አስነብቧል። 




ካርሎ አንቾሎቲ ከቀድሞ ልጆቻቸው ጋር በድጋሚ ለመስራት ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው ሚረር አስነብቧል። አንቾሎቲ አሁን ላይ ሳሚ ካዲራን እና ኢስኮን በጥር የዝውውር መስኮት ወደ ኤቨርተን በማምጣት ቡድናቸውን ለማጠናከር ይፈልጋሉ። 




ሰርጂዮ ራሞስን ለማስፈረም ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ፍላጎት አሳይተዋል።እንደ 90min ዘገባ ከሆነ ሁለቱ የማንችስተር ከተማ ክለቦች አንዲሁም ሊቨርፑል እና ሶስቱ የለንደን ክለቦች ራሞስን ለማስፈረም ፍላጎት ያሳዩት ክለቦች ናቸው። 




አዲስ አጥቂ ማምጣት የማንችስተር ዩናይትድ የክረምት የዝውውር መስኮት ቀዳሚ አላማ ነው። ነገር ግን በጥር የዝውውር መስኮት የመሐል ተከላካይና የቀኝ ክንፍ አጥቂ ማስፈረም ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።






 ቅድመ ጨዋታ ትንታኔ | ቶተንሃም ከ ማን ሲቲ


በተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፡ ነገ ከቀኑ 8:30 በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ቶተንሃም ማንቸስተር ሲቲን ያስተናግዳል።

ይህን ጨዋታ ይበልጥ ተጠባቂ የሚያደርገው ደግሞ በሁለቱ ባላንጣ አሰልጣኞች ሆዜ ሞሪንሆ እና ፔፕ ጓርዲዮላ መሀከል የሚደረግ መሆኑ ነው።ከዚህ በፊት በኤልክላሲኮ እና በማንቸስተር ደርቢ በተቃራኒ የተገናኙት ሁለቱ የዘመናዊ እግር ኳስ ጠበብት አሰልጣኞች ፡ ዳግም በሌሎች ክለቦችም የሚገናኙ ይሆናል።


ሆዜ ፔፕ ጋርዲዮላ የመራቸውን ክለቦች በተቃራኒ ገጥመው 10 ጊዜ ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን ፡ በዚህም የጓርዲዮላን ያህል ያሸነፉት አሰልጣኝ የለም።ፔፕም በበኩሉ ከማኑዌል ፔሌግሬኒ ቀጥሎ የሆዜ ሞሪንሆን ክለቦች ነው በተደጋጋሚ ያሸነፈው።



የቡድን ዜናዎች


ስኬታማ ያልሆነ ጊዜን እያሳለፈ ያለው ማን ሲቲ በኢንተርናሽናል ብሬክ ናታን አኬን እና ናትናኤል ክላይን ላይ ጉዳት አስተናግደዋል።


አኬ የነገው ጨዋታ በጉልበት ጉዳት ምክንያት የሚያልፈው ሲሆን ስተርሊንግ ግን ያጋጠመው ቀለል ያለ ጉንፋን በመሆኑ ወደ ሰሜን ለንደን ይጓዛል።


በጡንቻ መሸማቀቅ ጉዳት ላይ የሰነበተው የማን ሲቲ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሰርጂዮ አጉዌይሮ ነገ ይመለሳል።


አጉዌይሮ ስፐርስ ላይ 11 ግብ ማስቆጠር ችሏል።


ማትት ዶሐርቲ ኮሮና ቫይረስ ስለተገኘበት ከስፐርስ ስብስብ ውጪ ሆኗል።


ኤሪክ ላሜላ ወደ ነገው ጨዋታ የመመለስ ዕድል ያለው ሲሆን ታንጉይ ንዶምቤሌ ግን ሙሉ ለሙሉ ከጉዳቱ አገግሞ ለነገው ጨዋታ ብቁ ነው።


በነገው ጨዋታ በዚህ ሲዝን በሁሉም የውድድር አይነቶች በ14 ጨዋታ 23 ግብ ላይ በቀጥታ የተሳተፈው ሀሪ ኬን ይጠበቃል።


 ግምታዊ አሰላለፍ

|ቶተንሃም|

ሎሪስ ፡ ኦሪየር ፡ ኤልደርዊልድ ፡ ዳየር ፡ ሪጊውለን ፡ ሲሶኮ ፡ ሆጅበርግ ፡ ቤል ሌ ሶልሶ ፡ ሰን እና ኬይን


|ማን ሲቲ|

ኤደርሰን ፡ ዎከር ፡ ዲያዝ ፡ ላፖርት ፡ ካንሴሎ ፡ ደ ብሮይነ ፡ ሮድሪ ፡ ጉንዶሓን ፡ ቶተስ ፡ ሄሱስ እና ፎደን

Friday, November 20, 2020

ሞሪንሆ ከ ጓርዲዮላ

አዘጋጅ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)

 ቅድመ ጨዋታ ትንታኔ | ቶተንሃም ከ ማን ሲቲ


በተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፡ ነገ ከቀኑ 8:30 በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ቶተንሃም ማንቸስተር ሲቲን ያስተናግዳል።

ይህን ጨዋታ ይበልጥ ተጠባቂ የሚያደርገው ደግሞ በሁለቱ ባላንጣ አሰልጣኞች ሆዜ ሞሪንሆ እና ፔፕ ጓርዲዮላ መሀከል የሚደረግ መሆኑ ነው።ከዚህ በፊት በኤልክላሲኮ እና በማንቸስተር ደርቢ በተቃራኒ የተገናኙት ሁለቱ የዘመናዊ እግር ኳስ ጠበብት አሰልጣኞች ፡ ዳግም በሌሎች ክለቦችም የሚገናኙ ይሆናል።


ሆዜ ፔፕ ጋርዲዮላ የመራቸውን ክለቦች በተቃራኒ ገጥመው 10 ጊዜ ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን ፡ በዚህም የጓርዲዮላን ያህል ያሸነፉት አሰልጣኝ የለም።ፔፕም በበኩሉ ከማኑዌል ፔሌግሬኒ ቀጥሎ የሆዜ ሞሪንሆን ክለቦች ነው በተደጋጋሚ ያሸነፈው።



የቡድን ዜናዎች


ስኬታማ ያልሆነ ጊዜን እያሳለፈ ያለው ማን ሲቲ በኢንተርናሽናል ብሬክ ናታን አኬን እና ናትናኤል ክላይን ላይ ጉዳት አስተናግደዋል።


አኬ የነገው ጨዋታ በጉልበት ጉዳት ምክንያት የሚያልፈው ሲሆን ስተርሊንግ ግን ያጋጠመው ቀለል ያለ ጉንፋን በመሆኑ ወደ ሰሜን ለንደን ይጓዛል።


በጡንቻ መሸማቀቅ ጉዳት ላይ የሰነበተው የማን ሲቲ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሰርጂዮ አጉዌይሮ ነገ ይመለሳል።


አጉዌይሮ ስፐርስ ላይ 11 ግብ ማስቆጠር ችሏል።


ማትት ዶሐርቲ ኮሮና ቫይረስ ስለተገኘበት ከስፐርስ ስብስብ ውጪ ሆኗል።


ኤሪክ ላሜላ ወደ ነገው ጨዋታ የመመለስ ዕድል ያለው ሲሆን ታንጉይ ንዶምቤሌ ግን ሙሉ ለሙሉ ከጉዳቱ አገግሞ ለነገው ጨዋታ ብቁ ነው።


በነገው ጨዋታ በዚህ ሲዝን በሁሉም የውድድር አይነቶች በ14 ጨዋታ 23 ግብ ላይ በቀጥታ የተሳተፈው ሀሪ ኬን ይጠበቃል።


 ግምታዊ አሰላለፍ

|ቶተንሃም|

ሎሪስ ፡ ኦሪየር ፡ ኤልደርዊልድ ፡ ዳየር ፡ ሪጊውለን ፡ ሲሶኮ ፡ ሆጅበርግ ፡ ቤል ሌ ሶልሶ ፡ ሰን እና ኬይን


|ማን ሲቲ|

ኤደርሰን ፡ ዎከር ፡ ዲያዝ ፡ ላፖርት ፡ ካንሴሎ ፡ ደ ብሮይነ ፡ ሮድሪ ፡ ጉንዶሓን ፡ ቶተስ ፡ ሄሱስ እና ፎደን

የዕለተ አርብ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች


 ሪያል ማድሪድ እና ኢንተር ሚላን የኔዘርላንዳዊው አማካይ ጆርጂንሆ ቫይናልደም ፈላጊ  ቢሆኑም ሊቨርፑል ግብ ተጨዋቹን በአንፊልድ ለማቆየት ይፈልጋል።

(Mundo Deportivo - in Spanish)






ስፔናዊው የ34 ዓመት ተከላካይ ሰርጂዮ ራሞስ በሪያል ማድሪድ ያለውን ውል አለማራዘሙን ተከትሎ በርካታ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች እየፈለጉት ነው።

(90min)






ሪያል ማድሪድ ሰርጂዮ ራሞስ በክለቡ ቢቆይም ባይቆይም ኦስትሪያዊውን ተከላካይ ዴቪድ አላባ ከባየርን ሙኒክ ማዘዋወር ይፈልጋል።

(Marca)






ኤቨርተን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ዌልሳዊውን የመስመር አጥቂ ዳኔል ጄምስ ለማዘዋወር አቅዷል።

(Football Insider)






የዩቬንትሱ አማካይ ሳሚ ኬዲራ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለመጓዝ ፍላጎት ያለው ሲሆን ኤቨርተን እና ማንቸስተር ዩናይትድ ደግሞ ፈላጊዎቹ ናቸው።

(Sun)






ኤርሊንግ ሀላንድ ከቦሩሲያ ዶርትመንድ ጋር ዋንጫዎቹ ለማሳካት እንጂ ክለቡን ከመልቀቅ ዕቅድ እንደሌለው አባቱ አሳውቋል።

(Sport1, via Goal)





ፔፕ ጓርዲዮላ ለተጨማሪ አመታት በኤቲሀድ ለመቆየት መስማማቱን ተከትሎ ፡ ማን ሲቱ አርጀንቲናዊውን ምትሀተኛ ሊዮኔል ሜሲ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት ለማዘዋወር ለፔፕ ቃል ገብቶለታል። 

(Mirror) 

 

 

 

 

 

ማንቸስተር ዩናይትድ ፣ ፓሪሰን ዤርመን እና ሪያል ማድሪድ ፈረንሳዊውን የሬንስ አማካይ ኤድዋርዶ ካራቪንጋ ለማዘዋወር ፉክክር ውስጥ ገብተዋል። 

(Marca - in Spanish) 

 

 

 

 

 

ቨርጅል ቫን ዳይክ የጉልበት ቀዶ ጥገና ካደረገ በኋላ ቀለል ያሉ ልምምዶችን መስራት ጀምሯል።በዚህ ሲዝን ወደ ሜዳ ሊመለስም ይችላል። 

(Mail)

Thursday, November 19, 2020

የዕለተ ሐሙስ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

                        አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ


 ሆላንዳዊው የሊቨርፑል ኮከብ ዌይናልደም በሊቨርፑል የቀረበለትን ኮንትራት ማይፈርም ከሆነ ባርሴሎና እና ኢንተር ሚላን ልጁን በአመቱ መጨረሻ በነፃ ለማስፈረም ካሁኑ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን Calcio Mercato ትናንት ማምሻውን አስነብቧል። 




ማንችስተር ሲቲ እና ባየርን ሙኒክ በቦሩሲያ ሞንቼግላድባው አማካይ ዴኒስ ዛካሪያ ላይ ፍላጎት እንዳላቸው Calcio Mercato አስነብቧል። የ23 አመቱን አማካይ በጥር ለመውሰድ ከባየርን የበለጠ ማንችስተር ሲቲዎች ፍላጎት አላቸው። 




ባርሴሎናዎች ያለባቸውን የተከላካይ እና የመስመር አጥቂ ችግር ለመቅረፍ በጥር የዝውውር መስኮት ሁለት ትላልቅ ዝውውሮችን ለመፈፀም ዝግጁ መሆናቸውን Daily Mail አስነብቧል። ባርሴሎናዎች በጥር የመጀመሪያ ፍላጎታቸው የሊዮኑን ሜምፊስ ዴፓይ ሲሆን ሌላኛው ደሞ የማንችስተር ሲቲው ኤሪክ ጋርሲያ ናቸው። 





የፍራንክ ላምፓርዱ ቸልሲ አይናቸውን የቦሩሲያ ዶርትመንዱ እንግሊዛዊው አማካይ ጁዲ ቤሊንግሀም ላይ ጥለዋል። ቡድናቸውን በወጣት ተጨዋቾች ላይ ለመገንባት ፍላጎት ያላቸው ቸልሲዎች ቤሊንግሀምን የካንቴ የረጅም ጊዜ ተተኪ ለማድረግ አንደሚፈልጉ Eurosport አስነብቧል።በተጨማሪም ቸልሲዎች የዌስትሀሙን ዴክላን ራይስንም ይፈልጉታል። 




የፈረንሳዩ ክለብ ሴንቲቲየን አልጄሪያዊውን የሌስተር ሲቲ አጥቂ ኢስላም ሲሊማኒን በጥር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። አልጄሪያዊው የ32 አመት አጥቂ በዘንድሮ ሲዝን ለሌስተር በፕሪሚየር ሊጉ አንድ ጊዜ ብቻ ነው ተሰልፎ መጫወት የቻለው። 





ከትናንት ጀምሮ የተለያዩ የእንግሊዝ እና የጣሊያን ሚዲያዎች አርሰናል እና ኢንተር ሚላን ኤሪክሰን እና ዣካን ለመቀያየር ፍላጎት እንዳላቸው ሲዘግቡ ነበር። ነገር ግን አንደ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ ከሆነ ክርስቲያን ኤሪክሰን በድጋሚ ወደ እንግሊዝ መመለስ አይፈልግም። በጣሊያን ደስተኛ ባይሆንም በኢንተር ግን መቆየት እንደሚፈልግ እርግጥ ነው ይላል መረጃው።




ፖል ፖግባ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ምንም ችግር የለበትም። በወራት ውስጥ ዩናይትድ ለፖግባ አዲስ ኮንትራት ያቀርባል ፥ አዲስ የተፈጠረ ነገር የለም ሲል ታማኙ ዲማርዚዮ ተናግሯል።

Tuesday, November 17, 2020

የዕለተ ረቡዕ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

                አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ


 ቶተንሀም እና ኤቨርተን በናፖሊው አጥቂ አርካዜክ ሚሊክ ዝውውር ላይ መፋጠታቸውን The Sun አስነብቧል። ሁለቱም ክለቦች ፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ልጁን በጥር ለመውሰድ ከአሁኑ ከወኪሉ ጋር ንግግር ለማድረግ ዝግጁ ሆነዋል። ኢንተር ሚላንም የተጨዋቹ ፈላጊ ነው። 





ማንችስተር ሲቲዎች የ32 አመቱን ሰርጂዮ አጉዌሮን ለመተካት የተለያዩ አጥቂዎችን እየተመለከቱ ይገኛሉ።እንደ 90min.com ዘገባ ከሆነ ሲቲዎች አሁን ላይ የኢንተር ሚላኑን ማርቲኔዝ አልያም የቦሩሲያ ዶርትመንዱን ኤርሊንግ ሀላንድን የሚፈልጉት የአጥቂ ዝርዝር ውስጥ አስገብተዋል።በተጨማሪም ሲቲዎች የሂሚኔዝ ፈላጊ ሆነዋል። 




ማንችስተር ዩናይትዶች በክለባቸው ውስጥ ማይፈልጓቸውን ማርከስ ሮሆ ፣ ፊል ጆንስ ፣ሜንሳህን እና ሮሜሮ በጥር የዝውውር መስኮት ክለቡን እንዲለቁ ተነግሮዋቸዋ። እንደ M.E.N ዘገባ ከሆነ ተጨዋቾቹ ላይ እስካሁን ዋጋ ባይለጠፍባቸውም ዩናይትዶች ግን ተጨዋቾችን በቋሚ ዝውውር ብቻ ነው መልቀቅ  ሚፈልጉት። 




ሊቨርፑሎች ለሆላንዳዊው አማካይ ጂዮርጂኒዮ ዋይናልደም የተሻሻለ አዲስ ኮንትራት አቅርበውለታል። ተጨዋቹ በአንፊልድ ኮንትራቱ 2021 ክረምት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን ሊቨርፑሎች ለዋይናልደም የሶስት አመት ኮንትራት አቅርበውለታል። እንደ Calciomercato ዘገባ ከሆነም ሊቨርፑሎች ድርድሩን አሁንም እየገፉበት ይገኛሉ። 





ቸልሲዎች የመሀል ሜዳቸውን ለማጠናከር እንግሊዛዊውን የዌስትሀም አማካይ ዴክላን ራይስን በጥር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ይፈልጋሉ። ዝውውሩንም ለማጠናቀቅ ይረዳቸው ዘንድ ኒጎሎ ካንቴን ወደ ኢንተር ሚላን አልያም ፒኤስጂ በጥር ለመሸኘት ዝግጁ መሆናቸውን Express Sport አስነብቧል። 





ኤሲ ሚላኖች የአጥቂ ስፍራቸውን ለማጠናከር የተለያዩ ተጨዋቾችን እየተመለከቱ ይገኛሉ። Corriere dello Sport ዛሬ አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት ኤሲ ሚላኖች በጥር የዝውውር መስኮት ክሮሺያዊውን የሪያል ማድሪድ አጥቂ ሉካ ዮቪችን በውሰት ለማስፈረም ይፈልጋሉ። 





ዌስትሀም ዩናይትዶች የሪያል ማድሪዱን የመስመር አጥቂ ማሪያኖ ዲያዝን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ Defensa Central አስነብቧል።የ27 አመቱ ኮከብ በ2018 ከሊዮን ማድሪድን ተቀላቅሎ በማድሪድ ቤት የተጠበቀውን ያክል ጥሩ ሚባል ጊዜ ማሳለፍ ተስኖታል። ይህን ተከትሎ  ዌልትሀሞች ልጁን ለማስፈረም ይፈልጋሉ። 




ናፖሊዎች አዲሶቹ የቸልሲ የግራ መስመር ተከላካይ የኤመርሰን ፓልሜራ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል። ተጨዋቹ ለረጅም ጊዜ በኢንተር ሚላን ይፈለግ የነበረ ቢሆንም የጋቱሶው ናፖሊ የኤመርሰን ፈላጊ ሆኖ ብቅ ብሏል።

Monday, November 16, 2020

የዕለተ ማክሰኞ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች

 አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ



ኢንተር ሚላኖች በቀጣይ ክረምት ላውታሮ ማርቲኔዝን ወደ ባርሴሎና ሚሸኙት ከሆነ የሱን ምትክ የቶሪኖውን ኮከብ አንድሬያ ቤሎቲን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ካልቺዮ መርካቶ አስነብቧል። በተጨማሪም ኢንተር ሚላኖች በጥር የዝውውር መስኮት የቸልሲውን ኦሊቨር ዡሩድን ለመውሰድ ፍላጎት አሳይተዋል። 





ከሼፊልድ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ከተመለሰ በኋላ የመሰለፍ እድል እያገኘ የማይገኘው ኮከቡ ግብ ጠባቂ ዲን ሄንደርሰን በጥር የዝውውር መስኮት ዩናይትድን በውሰት ለመልቀቅ ዝግጁ ነው። ከፈላጊ ክለቦቹ ውስጥ የሆኑት ሴልቲኮች ልጁን በረጅም ጊዜ የውሰት ውል ማስፈረም እንደሚፈልጉ 90Min አስነብቧል። 





የወልቭሱ አጥቂ ራዎል ሂሚኔዝ በቀጣይ ክረምት ሰርጂዮ አጉዌሮን በመተካት ወደ ማንችስተር ሲቲ የማምራት እድል እንዳለው Don Balon አስነብቧል። የተጨዋቹ የመሸጫ ዋጋ የተጋነነ አለመሆኑን ተከትሎ የፔፕ ሲቲ ልጁን በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉ ተማምነዋል። 






የፈረንሳዩ ሀብታም ክለብ ፓሪሰን ጀርሜን በጥር የዝውውር መስኮት ስፔናዊውን ተከላካይ ሰርጂዮ ራሞስን ለመውሰድ ፍላጎት አሳይተዋል። ተጨዋቹ በዚህ አመት መጨረሻ በይፋ ከሪያል ማድሪድ ጋር ለመለያየት መቃረቡን ተከትሎ ፒኤስጂዎች በጥር እስከ £20m በመክፈል ልጁን ለመውሰድ ተዘጋጅተዋል። 




አትሌቲኮ ማድሪድ አዲሱ የካኖግሉ ፈላጊ ሆኖ ብቅ ብሏል። በኤሲ ሚላን ቤት የመጨረሻው የኮንትራት ማብቂያ አመት ላይ የሚገኘውን ካኖግሉን ለማስፈረም አትሌቲዎች አሁን ላይ ፍላጎት ማሳየታቸውን Mundo Deportivo አስነብቧል።ተጨዋቹ ከአትሌቲኮ በተጨማሪ በማንችስተር ዩናይትድ እና ባርሴሎናም ይፈለጋል። 





የአንቾሎቲው ኤቨርተን አዲሱ የስፔናዊ ኮከብ ፋቢያን ሩይዝ ፈላጊ ክለብ ሆነው መተዋል። ተጨዋቹ ከዚህ በፊት በሪያል ማድሪድ ፣ ባርሴሎና  እና አትሌቲኮ ቢፈለግም አሁን ላይ ኤቨርተኖች የ24 አመቱን አማካይ ለማስፈረም ከሁሉም ክለቦች በላይ ፍላጎት እንዳለውTodofichajes አስነብቧል። 






ጁቬንቱሶች የወልቭሱን የመስመር ተጨዋች ፔድሮ ኔቶን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ቱቶ ስፖርት አስነብቧል።ጁቬዎች ከተጨዋቹ ወኪል ጆርጌ ሜንዴዝ ጋር በተደጋጋሚ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ለተጨዋቹ ከፍ ያለ የዝውውር ሂሳብ ማዘጋጀታቸው ታውቋል። 

.

Sunday, November 15, 2020

የዕለተ ሰኞ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

 


ኤቨርተኖች ሌላ ተጨዋች ከሪያል ማድሪድ ለመውሰድ ፍላጎት አሳይተዋል። በክረምት ሀሜስ ሮድሪጌዝን በመውሰድ ጥሩ ግንኙነት ያላቸው ኤቨርተኖች አሁን ላይ ደግሞ በዚዳን ስር ማይፈለገውን ስፔናዊ ኮከብ ኢስኮን ለመውሰድ ይፈልጋሉ። ኤቨርተኖች ለተጨዋቹ እስከ £18m ለመክፈል ፍላጎት አላቸው። 




ኤሲ ሚላኖች ጣሊያናዊውን ኮከብ ጂአሉጂ ዶናሮማን ኮንትራት ለማራዘም ከጫፍ ደርሰዋል።እንደ Calcio Mercato ዘገባ ከሆነ ሚላኖች ለተጨዋቹ አመታዊ ከፍተኛ የተባለ €8m ለመክፈል ፍቃደኛ ሆነዋል።በቀጣይ ሳምንታት ዶናሮማ ለረጅም አመታት በሳንሴሮ የሚያቆየውን አዲስ ስምምነት ይፈራረማል። 





ጋርዲዮላ ያለበትን የፈጠራ ችግር ለመቅረፍ አሁን ላይ ሙሉ ትኩረቱን እንግሊዛዊው የአስቶንቪላ ኮከብ ጃክ ግሪሊሽ ላይ አድርጓል። ተጨዋቹ በተደጋጋሚ ወደ ዩናይትድ ይሄዳል ተብሎ ቢጠበቅም አሁን ላይ ግን ፔፕ ተጨዋቹን ለማስፈረም ዋነኛ ኢላማው አድርጓል። 





ኤቨርተን እና ሊቨርፑል በቶሪኖ ተከላካይ በግሌሰን ላይ ተፋጠዋል። እንደ ሊቨርፑል ከተማ ጋዜጣ Liverpool Echo ዘገባ ከሆነ ሁለቱም ክለቦች ልጁን ለመውሰድ ትልቅ ፍላጎት አሳይተዋል።የተጨዋቹም ማረፊያ በቀጣይ ሳምንታት እንደሚታወቅ ሌሎች የጣሊያን ጋዜጦች አስነብበዋል። 






ባርሴሎናዎች በጥር የዝውውር መስኮት ተከላካይ በውሰት ለማምጣት ይፈልጋሉ። አሁን ላይ ዋነኛ ትኩረታቸው በዚህ አመት ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው የማንችስተር ሲቲው ጋርሲያ ሲሆን ተጨዋቹን በጥር በውሰት ከመውሰድ ይልቅ በክረምት በነፃ ማግኘት ይፈልጋሉ። ይህን ተከትሎ ለግማሽ ሲዝን የሚሆን ተከላካይ ፍለጋ ወተዋል። እንደ SPORT ዘገባ ከሆነ ባርሳዎች ሩዲገርን ወይም ሙስጣፊን በውሰት ለመውሰድ ይፈልጋሉ። 





ጁቬንቱስ እና ፓሪሰን ጀርመን በስፔናዊው ኮከብ ተከላካይ ሰርጂዮ ራሞስ ላይ ትልቅ ፍላጎት አሳይተዋል። ተጨዋቹ ኮንትራቱን የማያራዝምበት እድሉ ሰፊ መሆኑን ተከትሎ ከአሁኑ ክለቦቹ ከተጨዋቹ ወኪል ጋር ግንኙነት ለማድረግ መዘጋጀታቸውን La Cuatro አስነብቧል። 






ክሪስታል ፓላሶች በቸልሲ ቤት ቤን ቺልዌል ከመጣ በኋላ የቋሚነት ቦታን ያጣው ስፔናዊው ማርከስ አሎንሶን በክረምት ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል። አንደ Daily Mail ዘገባ ከሆነ ፓላሶች የግራ መስመር ተከላካያቸው ፓትሪክ ቫንሆልት በክረምት እንደሚለቅ መረጋገጡን ተከትሎ ስፔናዊውን የ29 አመት ኮከብ ወደ ፓላስ ለመውሰድ ዝግጁ ሆነዋል። 





የስቴቨን ጄራርዱ ሬንጀርስ የሻምፒዮን ሺፑ ክለብ ኖርዊች ሲቲ አማካይ የሆነውን ኬኒ ማክሊንን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ The Sun አስነብቧል። ተጨዋቹ በክረምቱ የዝውውር መስኮት በርካታ ክለቦች ቢፈልጉትም ልጁ በኖርዊች ቆይቷል።ሬንጀርስም በጥር ልጁን ለመውሰድ ዝግጁ ናቸው።

Saturday, November 14, 2020

የዕለተ እሁድ ረፋድ ስፖርታዊ ዜናዎች


 ፖቸቲኖ ቅርቡ ለሆኑ ሰዎች እንደተናገረው ከሆነ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝነትን ስራ ይፈልገዋል። ነገር ግን ብቸኛ አማራጮቹ ዩናይትዶች እንዳልሆኑ አሳውቋል። ፖቸቲኖ ቀጣዩ የዩናይትድ አሰልጣኝ ለመሆን ብቸኛው የውድዋርድ እጩ አይደለም። 





ሪያል ማድሪዶች በክረምት ወደ ቶተንሀም የላኩትን ዌልሳዊውን ጋሪዝ ቤልን በድጋሚ ወደ ቤርናባው መመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው AS አስነብቧል። የተጨዋቹ ኮንትራት በ2022 በማድሪድ ቤት የሚጠናቀቅ ሲሆን ማድሪዶች እዛው ቶተንሀም እንዲቀር ፍላጎት አላቸው። ቶተንሀሞችም የቤልን ዝውውር ቋሚ ማድረግ ይፈልጋሉ። 






በተከላካይ ጉዳት እየታመሱ የሚገኙት ሊቨርፑሎች በጥር የዝውውር መስኮት አንድ ተከላካይ ለማስፈረም ወደ ገበያ ለመውጣት ተገደዋል። እንደ The Mirror ዘገባ ከሆነ ሊቨርፑሎች የመጀመሪያ ምርጫቸው የሻልክ04 ኦዛን ካባክ ነው።በተጨማሪም የሱ ዝውውር ማይሳካ ከሆነ የሌብዢኩን ኮከብ ዳዮት ኦፓምካኖን ለማስፈረም ይፈልጋሉ። 






ኮንትራት በ2021 ክረምት የሚጠናቀቀውን ጀርመናዊ የባየርን ሙኒክ ተከላካይ ቦአቴንግን በነፃ ለማስፈረም ሶስቱ የእንግሊዝ ክለብ የሆኑት ቶተንሀም፣ ቸልሲ እና አርሰናል ተፋጠዋል።ተጨዋቹ በሙኒክ በይፋ ኮንትራቱ እንደማይታደስለት የተነገረው ሲሆን ከጥር በኋላ ከፈለገው ቡድን ጋር ቅድመ ስምምነት መፈፀም ይችላል። 






 ከሰሞኑ በስፋት ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ሲያያዝ የቆየው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጁቬንቱስ እንደሚቆይ ታውቋል። የተጨዋቹ ኮንትራት በ2022 ሚጠናቀቅ ሲሆን ተጨዋቹ ወደ ሌላ ክለብ ከማምራት ይልቅ በቱሪን በመቆየት ተጨማሪ ስኬቶችን ከጁቬ ጋር ማጣጣም እንደሚፈልግ AS አስነብቧል። 





ሰርጂዮ ራሞስ እና ሪያል ማድሪድ ለመለያየት ተቃርቧል።ራሞስ በማድሪድ ጫማውን መስቀል እንደሚፈልግ እና ረጅም ኮንትራት እንዲቀርብለት ሲፈልግ በተቃራኒው ማድሪዶች ለተጨዋቹ ከሁለት አመት የበለጠ ኮንትራት ማቅረብ አይፈልጉም። ይህን ተከትሎ ተጨዋቹ በይፋ ማድሪድን መልቀቅ እንደሚፈልግ በቀጣይ ሳምንት ይፋ እንደሚያደርግ ማርካ አስነብቧል። 






ቤልጄማዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የመስመር አጥቂ አድናን ያኑዛይ በሁለት የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል። ከዩናይትድ ከለቀቀ በኋላ በስፔን ጥሩ የሚባል ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘውን ያኑዛይን ለመውሰድ ሳውዝሀምፕተን እና ብራይተን ፍላጎት አሳይተዋል። ክለቡ ሪያል ሶሴዳድ ልጁን የመልቀቅ ፍላጎት የላቸውም። 





ማንችስተር ዩናይትዶች ተከላካይ ለማስፈረም ወደ ገበያ ወተዋል። የጥር የዝውውር መስኮት ሲከፈት አንድ ተከላካይ ወደ ኦልትራፎርድ ለማምጣት ይፈልጋሉ የመጀመሪያ ምርጫቸው የሆነው የ21 አመቱ የብራጋ ተከላካይ ዴቪድ ካርሞ ሆኗል።እንደ ESPN ዘገባ ከሆነ ተጨዋቹ በጣሊያኖቹ ክለቦች ፊዮሬንቲና እና ሮማም ይፈለጋል። 






ቸልሲዎች ጣሊያናዊው የግራ መስመር ተከላካይ ኤመርሰን ፓልሜሪ ክለቡን እንዲለቅ ይፈልጋሉ። ተጨዋቹ በ2018 ከሮማ ያስፈረሙት ሲሆን አሁን ላይ በሱ ቦታ ተጨማሪ ተጨዋቾች ስላሉ ልጁን ላምፓርድ አይፈልገውም ይህን ተከትሎ ልጁ ወደ ፈለገበት ክለብ እንዲሄድ መውጫ በሩን ክፍት አድርገውለታል።

Sunday, November 8, 2020

የዕለተ እሁድ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

 


ሎዛ አበራ ከቢሪክሪካራ ጋር መለያየቷ እውን ሆኗል ! 


ያለፉትን አስራ አራት ወራት በማልታው ክለብ በስኬት የታጀበ ዓመትን ያሳለፈችው ሎዛ አበራ በክለቡ እንደማትቆይ ይፋ አድርጋለች ።


ሌዛ አበራ ቀጣይ ማረፊያው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሆኗል ፥ ወርሃዊ ደሞዟም ከነ  ጥቅማ ጥቅም 75ሺህ ብር ሆኗል።

 (Tikvah)





ብሔራዊ ቡድኑ ነገ ወደ ኒጀር ያቀናል !

የኮሮና ውጤት ሳይታወቅ ?

በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና በረዳቶቻቸው የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ

ቡድን በካፍ አካዳሚ ዝግጅቱን ላለፉት ስድስት ሳምንታት አድርጎ ለሚጠበቀው

የአፍሪካ ዋንጫ ማጣራያ ፍልሚያ ነገ ወደ ኒጀር- ኒያሚ እንደሚጓዝ ታውቋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ቀደም ብሎ በካፍ አካዳሚ ብሔራዊ ቡድኑ

የሚያደርገው የዝግጅት ጊዜ ለአስር ቀናት የተባለ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች

ለስድስት ሳምንት ሙሉውን የዝግጅት ጊዜ በካፍ አካዳሚ -በአዲስ አበባ

አድርጓል።

ቡድኑ አቋሙን የፈተሸውም ሶስት የወዳጅነት ጨዋታ የትም ሳይጓዝ በአዲስ

አበባ በተመሳሳይ ነው ። ከዚህ አንፃር አዲሱ ብሔራዊ ቡድኑን ትክክለኛ አቋሙ

ገና አልታወቀም ማለት ይቻላል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኒጀር አቻው የፊታችን አርብ ጨዋታውን የሚያደርግ

ሲሆን የቡድኑ አባላት ትላንት የኮሮና ምርመራ ማድረጋቸው ሲሰማ ውጤቱ

አልተገለፀም። ሆኖም ከዛሬው የኒጀር ጉዞ በፊት ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

እንደሚታወሰው ብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት ሲጀምር የመጀመሪያ የCovid-19 ምርመራ ካከናወኑ 36 የቡድኑ አባላት መካከል አምስት ተጨዋቾች በቫይረሱ

ተይዘው ማገገማቸው አይዘነጋም።

(Ethio Kick off)





ኖርዌያዊው ድንቅ ወጣት አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ በቦሩሲያ ዶርትመንድ የውል ማፍረሻ የተቆረጠ ሒሳብ እንደሌለው የክለቡ ቺፍ ኤክስኪውቲቭ ሀንስ ጆዋኺም ገልፀዋል። 

(Bild - in German) 

 

 

 

 

 

የዩቬንትሱ ቺፍ ፉትቦል ፋቢዮ ፓራቲቺ ከፈረንሳዊው የማን ዩናይትድ አማካይ ፖል ፖግባ ጋር መነጋገር ጀምረዋል።ፖግባ በቲያትር ኦፍ ድሪምስ ብዙም ደስተኛ አይደለም። 

(Mirror)





ባርሴሎና ጥር ላይ አምስት ተጨዋቾችን እንደሚለቅ ይጠበቃል።ከነዚህ ተጨዋቾች ውስጥ በማን ዩናይትድ የሚፈለገው ፈረንሳዊው የመስመር አጥቂ ኦስማን ዴምቤሌ ይገኝበታል። 

(Mundo Deportivo) 

 

 

 

 

 

ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ  ከበርካታ ጊዜያት በኋላ ወደ አሰልጣኝነት መመለሻቸው ጊዜ የተቃረበ ይመስላል።ቀጣይ ማረፊያቸውም ማን ዩናይትድ ሊሆን እንደሚችል ነው እየተጠበቀ ያለው።ፖቼቲንሆ ከባርሴሎና ሁለት ጊዜ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አድርገው ነበር። 

(Star)





ማንቸስተር ሲቲ ለእንግሊዛዊው የአጥቂ አማካይ ፊል ፎደን የውል ማራዘሚያ ሊያቀርብለት ነው።አዲሱ ውል የተጨዋቹን ደሞዝ ሶስት እጥፍ ያሳድጋል። 

(Star) 

 

 

 

 

 

ማን ዩናይትድ ሙሳ ዲያቢን ለማዘዋወር ያቀረበውን ጥያቄ ባየርን ሊቨርኩሰን ውስቅ አድርጎበታል። 

(Bild, via Inside Futbol) 

 

 

 

 

 

የዴቪድ ቤካም ክለብ የሆነው ፡ የሜጀር ሊግ ሶከሩ ክለብ ኢንተር ሚያሚ የሪያል ማድሪዱን ኮከብ ሰርጂዮ ራሞስ ለማዘዋወር እየሰራ ነው። 

(AS)

Wednesday, November 4, 2020

የ2020 ምርጥ አስር አጥቂዎች

  የ2020 ምርጥ 10 አጥቂዎች


ታዋቂው ጋዜጣ ፎር ፎር ቱ ፡ በ2020 የታዩ አስር አጥቂዎችን ዝርዝር በበርካታ መመዘኛዎች አስቀምጧል።እኛም እንደሚከተለው አስቀምጠነዋል


ውድ አንባቢያን ከስር የተቀመጡት የፊት መስመር አጥቂዎች ናቸው ።የመስመር አጥቂዎችን አይጨምርም።





10.ጄሚ ቫርዲ (ሌስተር ሲቲ)



9.ሊውዝ ሱዋሬዝ (አትሌቲኮ ማድሪድ)




8.ራሁል ሂሜኔዝ (ዎልቨርሀምተን ዎንደረርስ)




7.ካሪም ቤንዜማ (ሪያል ማድሪድ)




6.ኤርሊንግ ሀላንድ (ቦሩሲያ ዶርትመንድ)




5.ሰርሂዮ አጉዌይሮ (ማንቸስተር ስቲ)




4.ሮሜሮ ሉካኩ (ኢንተር ሚላን)




3.ክርስቲያኖ ሮናልድ (ዩቬንትስ)




2.ሀሪ ኬን (ቶተንሃም)




1.ሌዋንዶልስኪ (ባየርን ሙኒክ)

Tuesday, November 3, 2020

የወቅቱ የዓለማችን ምርጥ አምስት አማካዮች

                 አዘጋጅ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


 ቶፕ ሶከር ባወጣው መረጃ መሰረት ፥ የዓለማችን 2020 ምርጥ አምስት አማካዮች የሚከተሉት ናቸው።ከመጨረሻው እንጀምራለን




5.ብሩኖ ፈርናንዴዝ (ማን ዩናይትድ)

ባለፈው ዓመት ከስፖርቲንግ ሊዝበን ማን ዩናይትድን የተቀላቀለው ብሩኖ ፈርናንዴዝ ፥ ብዙዎች በቲያትር ኦፍ ድሪምስ እያሳየ ባለው አቋም ያሞግሱታል።

የ25 አመቱን ፖርቱጋላዊ አማካይ ለማን ዩናይትድ ቁልፍ ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን ለግብነት የበቁ ኳሶችንም አመቻችቶ አቀብሏል።በዚህም በአሁኑ ሰዓት የዓለማችን ምርጥ አምስተኛ አማካይ ተብሏል።






4.ካሴሚሮ (ሪያል ማድሪድ)

የ2019/20 የሪያል ማድሪድ የሊግ ስኬት ሲነሳ ካሴሚሮን መዘንጋት አይቻልም።ካሴሚሮ በተለይ ኳስን በማስጣል እና ለተከላካዮች ሽፋን በመስጠቱ ብዙዎች ያደንቁታል።






3.ሀኪም ዚያች (አያክስ/ቼልሲ)

አሁን በቼልሲ የሚገኘው ዚያች በ2020 ዓመት በተለይ ለቀድሞው ክለቡ አያክስ ባደረገው አስተዋፅኦ 3ተኛ ሆኗል።






2.ቲዬጎ አልካንታራ (ባየርን ሙኒክ/ሊቨርፑል)

ስፔናዊው አማካይ ባየርን ሙኒክ በአንድ አመት ሻምፒዮንስ ሊግን ጨምሮ ሶስት ዋንጫዎችን ሲያሳካ ቁልፉ ሰው ነበር።አሁን ደግሞ በሊቨርፑል ጥሩ ጅማሮ በማድረግ ላይ ነው።






1.ኬቨን ደ ብሮይነ (ማን ሲቲ)

ቤልጄሚያዊው ጥበበኛ የዓለማችን ምርጡ አማካይ ተብሏል ፥ በቶፕ ሶከር።በተለይ ድንቅ የግብ ዕድሎችን በመፍጠር እና ግቦችን በማስቆጠር እንዲሁም የተሳካ ኳስ አቀባይነቱ ብዙዎችን የሚያስደምም የተጨዋቹ ተሰጥኦ ነው።

የዕለተ ማክሰኞ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች

                      አቅራቢ - አብዱልቃድር በሽር (የሪሐና ልጅ)


 ኢንተር ሚላን ዴንማርካዊውን አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ከመሸጥ ይፈልጋል።£18ሚ. የዝውውር ዋጋው እንደሚሆን የተነገረውን ኤሪክሰን ኤሲ ሚላን ፣ ሮማ እና ላዚዮ ይፈልጉታል።

(Calciomercato - in Italian)







ብራዚላዊው ኢንተርናሽናል ኔይማር በፓሪሰን ዤርመን መቆየት እንደሚፈልግ ለአመራሮቹ ነግሯቸዋል።የ28 አመቱ አጥቂ እስከ 2022 የሚያቆይ ኮንትራት ያለው ሲሆን ከወዲሁ ንግግር ጀምሯል።

(Foot Mercato, via Sunday Mirror)






እንግሊዛዊው ተከላካይ ፊል ጆንስ በቀጣዩ የዝውውር መስኮት በውሰት ከማን ዩናይትድ ወደ በርንሌይ እንደሚጓዝ ዴይሊ ስታር አስነብቧል።

(Daily Star Sunday)






የሪያል ማድሪዱ ስፓኒያርድ ኢስኮ ከቀድሞው አሰልጣኙ ካርሎ አንቾሎቲ እና የቡድን አጋሩ ሀሜስ ሮድሪጌዝ ጋር በኤቨርተን ሊገናኝ ይችላል በቀጣዩ የዝውውር መስኮት።

(Sunday Mirror)






ቦሲኒያ ሄርዞጎቪኒያዊውን ተከላካይ አነል አህመድሆድዚኽ ለማዘዋወር ቼልሲ ለማልሞ £8ሚ. አቅርቧል።

(Expressen - in Swedish)






የቀድሞው ፈረንሳዊ የአርሰናል አጥቂ ሮበርት ፒሬዝ ኪልያን ምባፔ ወደ ሪያል ማድሪድ ቢጓዝ የእግር ኳስ ሕይወቱ የተሻለ እንደሚሆን መክሯል።

(Goal)






በአመቱ መጨረሻ በናፖሊ ያለው ውል የሚያበቃው ጄናሮ ጋቱሶ አዲስ ኮንትራት ሊፈራረም ነው።ጋቱሶ በዚህ አመት ጥሩ ቡድን ሰርቷል።

(Sky Italia - in Italian)






ዲዬጎ ሲሞኒ ለሊውዝ ሱዋሬዝ አጣማሪ የሚሆን አጥቂ እየፈለገ ሲሆን ዋነኛው ዕቅዱ ደግሚ የአታላንታው ዱቫን ዛፓታ ነው።

(Calciomercato - in Italian)







አሁን ክለብ አልባ የሆነው የቀድሞው የዩቬንትስ ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ እና ባየርን ሙኒክ አጥቂ ማሪዮ ማንዙኪች ከአስቶን ቪላ የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

(Birmingham Mail)

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...