Sunday, November 15, 2020

የዕለተ ሰኞ ማለዳ ስፖርታዊ ዜናዎች

 


ኤቨርተኖች ሌላ ተጨዋች ከሪያል ማድሪድ ለመውሰድ ፍላጎት አሳይተዋል። በክረምት ሀሜስ ሮድሪጌዝን በመውሰድ ጥሩ ግንኙነት ያላቸው ኤቨርተኖች አሁን ላይ ደግሞ በዚዳን ስር ማይፈለገውን ስፔናዊ ኮከብ ኢስኮን ለመውሰድ ይፈልጋሉ። ኤቨርተኖች ለተጨዋቹ እስከ £18m ለመክፈል ፍላጎት አላቸው። 




ኤሲ ሚላኖች ጣሊያናዊውን ኮከብ ጂአሉጂ ዶናሮማን ኮንትራት ለማራዘም ከጫፍ ደርሰዋል።እንደ Calcio Mercato ዘገባ ከሆነ ሚላኖች ለተጨዋቹ አመታዊ ከፍተኛ የተባለ €8m ለመክፈል ፍቃደኛ ሆነዋል።በቀጣይ ሳምንታት ዶናሮማ ለረጅም አመታት በሳንሴሮ የሚያቆየውን አዲስ ስምምነት ይፈራረማል። 





ጋርዲዮላ ያለበትን የፈጠራ ችግር ለመቅረፍ አሁን ላይ ሙሉ ትኩረቱን እንግሊዛዊው የአስቶንቪላ ኮከብ ጃክ ግሪሊሽ ላይ አድርጓል። ተጨዋቹ በተደጋጋሚ ወደ ዩናይትድ ይሄዳል ተብሎ ቢጠበቅም አሁን ላይ ግን ፔፕ ተጨዋቹን ለማስፈረም ዋነኛ ኢላማው አድርጓል። 





ኤቨርተን እና ሊቨርፑል በቶሪኖ ተከላካይ በግሌሰን ላይ ተፋጠዋል። እንደ ሊቨርፑል ከተማ ጋዜጣ Liverpool Echo ዘገባ ከሆነ ሁለቱም ክለቦች ልጁን ለመውሰድ ትልቅ ፍላጎት አሳይተዋል።የተጨዋቹም ማረፊያ በቀጣይ ሳምንታት እንደሚታወቅ ሌሎች የጣሊያን ጋዜጦች አስነብበዋል። 






ባርሴሎናዎች በጥር የዝውውር መስኮት ተከላካይ በውሰት ለማምጣት ይፈልጋሉ። አሁን ላይ ዋነኛ ትኩረታቸው በዚህ አመት ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው የማንችስተር ሲቲው ጋርሲያ ሲሆን ተጨዋቹን በጥር በውሰት ከመውሰድ ይልቅ በክረምት በነፃ ማግኘት ይፈልጋሉ። ይህን ተከትሎ ለግማሽ ሲዝን የሚሆን ተከላካይ ፍለጋ ወተዋል። እንደ SPORT ዘገባ ከሆነ ባርሳዎች ሩዲገርን ወይም ሙስጣፊን በውሰት ለመውሰድ ይፈልጋሉ። 





ጁቬንቱስ እና ፓሪሰን ጀርመን በስፔናዊው ኮከብ ተከላካይ ሰርጂዮ ራሞስ ላይ ትልቅ ፍላጎት አሳይተዋል። ተጨዋቹ ኮንትራቱን የማያራዝምበት እድሉ ሰፊ መሆኑን ተከትሎ ከአሁኑ ክለቦቹ ከተጨዋቹ ወኪል ጋር ግንኙነት ለማድረግ መዘጋጀታቸውን La Cuatro አስነብቧል። 






ክሪስታል ፓላሶች በቸልሲ ቤት ቤን ቺልዌል ከመጣ በኋላ የቋሚነት ቦታን ያጣው ስፔናዊው ማርከስ አሎንሶን በክረምት ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል። አንደ Daily Mail ዘገባ ከሆነ ፓላሶች የግራ መስመር ተከላካያቸው ፓትሪክ ቫንሆልት በክረምት እንደሚለቅ መረጋገጡን ተከትሎ ስፔናዊውን የ29 አመት ኮከብ ወደ ፓላስ ለመውሰድ ዝግጁ ሆነዋል። 





የስቴቨን ጄራርዱ ሬንጀርስ የሻምፒዮን ሺፑ ክለብ ኖርዊች ሲቲ አማካይ የሆነውን ኬኒ ማክሊንን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ The Sun አስነብቧል። ተጨዋቹ በክረምቱ የዝውውር መስኮት በርካታ ክለቦች ቢፈልጉትም ልጁ በኖርዊች ቆይቷል።ሬንጀርስም በጥር ልጁን ለመውሰድ ዝግጁ ናቸው።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...