ፖቸቲኖ ቅርቡ ለሆኑ ሰዎች እንደተናገረው ከሆነ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝነትን ስራ ይፈልገዋል። ነገር ግን ብቸኛ አማራጮቹ ዩናይትዶች እንዳልሆኑ አሳውቋል። ፖቸቲኖ ቀጣዩ የዩናይትድ አሰልጣኝ ለመሆን ብቸኛው የውድዋርድ እጩ አይደለም።
ሪያል ማድሪዶች በክረምት ወደ ቶተንሀም የላኩትን ዌልሳዊውን ጋሪዝ ቤልን በድጋሚ ወደ ቤርናባው መመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው AS አስነብቧል። የተጨዋቹ ኮንትራት በ2022 በማድሪድ ቤት የሚጠናቀቅ ሲሆን ማድሪዶች እዛው ቶተንሀም እንዲቀር ፍላጎት አላቸው። ቶተንሀሞችም የቤልን ዝውውር ቋሚ ማድረግ ይፈልጋሉ።
በተከላካይ ጉዳት እየታመሱ የሚገኙት ሊቨርፑሎች በጥር የዝውውር መስኮት አንድ ተከላካይ ለማስፈረም ወደ ገበያ ለመውጣት ተገደዋል። እንደ The Mirror ዘገባ ከሆነ ሊቨርፑሎች የመጀመሪያ ምርጫቸው የሻልክ04 ኦዛን ካባክ ነው።በተጨማሪም የሱ ዝውውር ማይሳካ ከሆነ የሌብዢኩን ኮከብ ዳዮት ኦፓምካኖን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።
ኮንትራት በ2021 ክረምት የሚጠናቀቀውን ጀርመናዊ የባየርን ሙኒክ ተከላካይ ቦአቴንግን በነፃ ለማስፈረም ሶስቱ የእንግሊዝ ክለብ የሆኑት ቶተንሀም፣ ቸልሲ እና አርሰናል ተፋጠዋል።ተጨዋቹ በሙኒክ በይፋ ኮንትራቱ እንደማይታደስለት የተነገረው ሲሆን ከጥር በኋላ ከፈለገው ቡድን ጋር ቅድመ ስምምነት መፈፀም ይችላል።
ከሰሞኑ በስፋት ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ሲያያዝ የቆየው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጁቬንቱስ እንደሚቆይ ታውቋል። የተጨዋቹ ኮንትራት በ2022 ሚጠናቀቅ ሲሆን ተጨዋቹ ወደ ሌላ ክለብ ከማምራት ይልቅ በቱሪን በመቆየት ተጨማሪ ስኬቶችን ከጁቬ ጋር ማጣጣም እንደሚፈልግ AS አስነብቧል።
ሰርጂዮ ራሞስ እና ሪያል ማድሪድ ለመለያየት ተቃርቧል።ራሞስ በማድሪድ ጫማውን መስቀል እንደሚፈልግ እና ረጅም ኮንትራት እንዲቀርብለት ሲፈልግ በተቃራኒው ማድሪዶች ለተጨዋቹ ከሁለት አመት የበለጠ ኮንትራት ማቅረብ አይፈልጉም። ይህን ተከትሎ ተጨዋቹ በይፋ ማድሪድን መልቀቅ እንደሚፈልግ በቀጣይ ሳምንት ይፋ እንደሚያደርግ ማርካ አስነብቧል።
ቤልጄማዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የመስመር አጥቂ አድናን ያኑዛይ በሁለት የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል። ከዩናይትድ ከለቀቀ በኋላ በስፔን ጥሩ የሚባል ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘውን ያኑዛይን ለመውሰድ ሳውዝሀምፕተን እና ብራይተን ፍላጎት አሳይተዋል። ክለቡ ሪያል ሶሴዳድ ልጁን የመልቀቅ ፍላጎት የላቸውም።
ማንችስተር ዩናይትዶች ተከላካይ ለማስፈረም ወደ ገበያ ወተዋል። የጥር የዝውውር መስኮት ሲከፈት አንድ ተከላካይ ወደ ኦልትራፎርድ ለማምጣት ይፈልጋሉ የመጀመሪያ ምርጫቸው የሆነው የ21 አመቱ የብራጋ ተከላካይ ዴቪድ ካርሞ ሆኗል።እንደ ESPN ዘገባ ከሆነ ተጨዋቹ በጣሊያኖቹ ክለቦች ፊዮሬንቲና እና ሮማም ይፈለጋል።
ቸልሲዎች ጣሊያናዊው የግራ መስመር ተከላካይ ኤመርሰን ፓልሜሪ ክለቡን እንዲለቅ ይፈልጋሉ። ተጨዋቹ በ2018 ከሮማ ያስፈረሙት ሲሆን አሁን ላይ በሱ ቦታ ተጨማሪ ተጨዋቾች ስላሉ ልጁን ላምፓርድ አይፈልገውም ይህን ተከትሎ ልጁ ወደ ፈለገበት ክለብ እንዲሄድ መውጫ በሩን ክፍት አድርገውለታል።
No comments:
Post a Comment