አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ኢንተር ሚላኖች በቀጣይ ክረምት ላውታሮ ማርቲኔዝን ወደ ባርሴሎና ሚሸኙት ከሆነ የሱን ምትክ የቶሪኖውን ኮከብ አንድሬያ ቤሎቲን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ካልቺዮ መርካቶ አስነብቧል። በተጨማሪም ኢንተር ሚላኖች በጥር የዝውውር መስኮት የቸልሲውን ኦሊቨር ዡሩድን ለመውሰድ ፍላጎት አሳይተዋል።
ከሼፊልድ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ከተመለሰ በኋላ የመሰለፍ እድል እያገኘ የማይገኘው ኮከቡ ግብ ጠባቂ ዲን ሄንደርሰን በጥር የዝውውር መስኮት ዩናይትድን በውሰት ለመልቀቅ ዝግጁ ነው። ከፈላጊ ክለቦቹ ውስጥ የሆኑት ሴልቲኮች ልጁን በረጅም ጊዜ የውሰት ውል ማስፈረም እንደሚፈልጉ 90Min አስነብቧል።
የወልቭሱ አጥቂ ራዎል ሂሚኔዝ በቀጣይ ክረምት ሰርጂዮ አጉዌሮን በመተካት ወደ ማንችስተር ሲቲ የማምራት እድል እንዳለው Don Balon አስነብቧል። የተጨዋቹ የመሸጫ ዋጋ የተጋነነ አለመሆኑን ተከትሎ የፔፕ ሲቲ ልጁን በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉ ተማምነዋል።
የፈረንሳዩ ሀብታም ክለብ ፓሪሰን ጀርሜን በጥር የዝውውር መስኮት ስፔናዊውን ተከላካይ ሰርጂዮ ራሞስን ለመውሰድ ፍላጎት አሳይተዋል። ተጨዋቹ በዚህ አመት መጨረሻ በይፋ ከሪያል ማድሪድ ጋር ለመለያየት መቃረቡን ተከትሎ ፒኤስጂዎች በጥር እስከ £20m በመክፈል ልጁን ለመውሰድ ተዘጋጅተዋል።
አትሌቲኮ ማድሪድ አዲሱ የካኖግሉ ፈላጊ ሆኖ ብቅ ብሏል። በኤሲ ሚላን ቤት የመጨረሻው የኮንትራት ማብቂያ አመት ላይ የሚገኘውን ካኖግሉን ለማስፈረም አትሌቲዎች አሁን ላይ ፍላጎት ማሳየታቸውን Mundo Deportivo አስነብቧል።ተጨዋቹ ከአትሌቲኮ በተጨማሪ በማንችስተር ዩናይትድ እና ባርሴሎናም ይፈለጋል።
የአንቾሎቲው ኤቨርተን አዲሱ የስፔናዊ ኮከብ ፋቢያን ሩይዝ ፈላጊ ክለብ ሆነው መተዋል። ተጨዋቹ ከዚህ በፊት በሪያል ማድሪድ ፣ ባርሴሎና እና አትሌቲኮ ቢፈለግም አሁን ላይ ኤቨርተኖች የ24 አመቱን አማካይ ለማስፈረም ከሁሉም ክለቦች በላይ ፍላጎት እንዳለውTodofichajes አስነብቧል።
ጁቬንቱሶች የወልቭሱን የመስመር ተጨዋች ፔድሮ ኔቶን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ቱቶ ስፖርት አስነብቧል።ጁቬዎች ከተጨዋቹ ወኪል ጆርጌ ሜንዴዝ ጋር በተደጋጋሚ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ለተጨዋቹ ከፍ ያለ የዝውውር ሂሳብ ማዘጋጀታቸው ታውቋል።
.
No comments:
Post a Comment