አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ቶተንሀም እና ኤቨርተን በናፖሊው አጥቂ አርካዜክ ሚሊክ ዝውውር ላይ መፋጠታቸውን The Sun አስነብቧል። ሁለቱም ክለቦች ፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ልጁን በጥር ለመውሰድ ከአሁኑ ከወኪሉ ጋር ንግግር ለማድረግ ዝግጁ ሆነዋል። ኢንተር ሚላንም የተጨዋቹ ፈላጊ ነው።
ማንችስተር ሲቲዎች የ32 አመቱን ሰርጂዮ አጉዌሮን ለመተካት የተለያዩ አጥቂዎችን እየተመለከቱ ይገኛሉ።እንደ 90min.com ዘገባ ከሆነ ሲቲዎች አሁን ላይ የኢንተር ሚላኑን ማርቲኔዝ አልያም የቦሩሲያ ዶርትመንዱን ኤርሊንግ ሀላንድን የሚፈልጉት የአጥቂ ዝርዝር ውስጥ አስገብተዋል።በተጨማሪም ሲቲዎች የሂሚኔዝ ፈላጊ ሆነዋል።
ማንችስተር ዩናይትዶች በክለባቸው ውስጥ ማይፈልጓቸውን ማርከስ ሮሆ ፣ ፊል ጆንስ ፣ሜንሳህን እና ሮሜሮ በጥር የዝውውር መስኮት ክለቡን እንዲለቁ ተነግሮዋቸዋ። እንደ M.E.N ዘገባ ከሆነ ተጨዋቾቹ ላይ እስካሁን ዋጋ ባይለጠፍባቸውም ዩናይትዶች ግን ተጨዋቾችን በቋሚ ዝውውር ብቻ ነው መልቀቅ ሚፈልጉት።
ሊቨርፑሎች ለሆላንዳዊው አማካይ ጂዮርጂኒዮ ዋይናልደም የተሻሻለ አዲስ ኮንትራት አቅርበውለታል። ተጨዋቹ በአንፊልድ ኮንትራቱ 2021 ክረምት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን ሊቨርፑሎች ለዋይናልደም የሶስት አመት ኮንትራት አቅርበውለታል። እንደ Calciomercato ዘገባ ከሆነም ሊቨርፑሎች ድርድሩን አሁንም እየገፉበት ይገኛሉ።
ቸልሲዎች የመሀል ሜዳቸውን ለማጠናከር እንግሊዛዊውን የዌስትሀም አማካይ ዴክላን ራይስን በጥር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ይፈልጋሉ። ዝውውሩንም ለማጠናቀቅ ይረዳቸው ዘንድ ኒጎሎ ካንቴን ወደ ኢንተር ሚላን አልያም ፒኤስጂ በጥር ለመሸኘት ዝግጁ መሆናቸውን Express Sport አስነብቧል።
ኤሲ ሚላኖች የአጥቂ ስፍራቸውን ለማጠናከር የተለያዩ ተጨዋቾችን እየተመለከቱ ይገኛሉ። Corriere dello Sport ዛሬ አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት ኤሲ ሚላኖች በጥር የዝውውር መስኮት ክሮሺያዊውን የሪያል ማድሪድ አጥቂ ሉካ ዮቪችን በውሰት ለማስፈረም ይፈልጋሉ።
ዌስትሀም ዩናይትዶች የሪያል ማድሪዱን የመስመር አጥቂ ማሪያኖ ዲያዝን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ Defensa Central አስነብቧል።የ27 አመቱ ኮከብ በ2018 ከሊዮን ማድሪድን ተቀላቅሎ በማድሪድ ቤት የተጠበቀውን ያክል ጥሩ ሚባል ጊዜ ማሳለፍ ተስኖታል። ይህን ተከትሎ ዌልትሀሞች ልጁን ለማስፈረም ይፈልጋሉ።
ናፖሊዎች አዲሶቹ የቸልሲ የግራ መስመር ተከላካይ የኤመርሰን ፓልሜራ ፈላጊ ሆነው ብቅ ብለዋል። ተጨዋቹ ለረጅም ጊዜ በኢንተር ሚላን ይፈለግ የነበረ ቢሆንም የጋቱሶው ናፖሊ የኤመርሰን ፈላጊ ሆኖ ብቅ ብሏል።
No comments:
Post a Comment