አዘጋጅ - ኢብራሒም ሙሐመድ
ሆላንዳዊው የሊቨርፑል ኮከብ ዌይናልደም በሊቨርፑል የቀረበለትን ኮንትራት ማይፈርም ከሆነ ባርሴሎና እና ኢንተር ሚላን ልጁን በአመቱ መጨረሻ በነፃ ለማስፈረም ካሁኑ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን Calcio Mercato ትናንት ማምሻውን አስነብቧል።
ማንችስተር ሲቲ እና ባየርን ሙኒክ በቦሩሲያ ሞንቼግላድባው አማካይ ዴኒስ ዛካሪያ ላይ ፍላጎት እንዳላቸው Calcio Mercato አስነብቧል። የ23 አመቱን አማካይ በጥር ለመውሰድ ከባየርን የበለጠ ማንችስተር ሲቲዎች ፍላጎት አላቸው።
ባርሴሎናዎች ያለባቸውን የተከላካይ እና የመስመር አጥቂ ችግር ለመቅረፍ በጥር የዝውውር መስኮት ሁለት ትላልቅ ዝውውሮችን ለመፈፀም ዝግጁ መሆናቸውን Daily Mail አስነብቧል። ባርሴሎናዎች በጥር የመጀመሪያ ፍላጎታቸው የሊዮኑን ሜምፊስ ዴፓይ ሲሆን ሌላኛው ደሞ የማንችስተር ሲቲው ኤሪክ ጋርሲያ ናቸው።
የፍራንክ ላምፓርዱ ቸልሲ አይናቸውን የቦሩሲያ ዶርትመንዱ እንግሊዛዊው አማካይ ጁዲ ቤሊንግሀም ላይ ጥለዋል። ቡድናቸውን በወጣት ተጨዋቾች ላይ ለመገንባት ፍላጎት ያላቸው ቸልሲዎች ቤሊንግሀምን የካንቴ የረጅም ጊዜ ተተኪ ለማድረግ አንደሚፈልጉ Eurosport አስነብቧል።በተጨማሪም ቸልሲዎች የዌስትሀሙን ዴክላን ራይስንም ይፈልጉታል።
የፈረንሳዩ ክለብ ሴንቲቲየን አልጄሪያዊውን የሌስተር ሲቲ አጥቂ ኢስላም ሲሊማኒን በጥር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። አልጄሪያዊው የ32 አመት አጥቂ በዘንድሮ ሲዝን ለሌስተር በፕሪሚየር ሊጉ አንድ ጊዜ ብቻ ነው ተሰልፎ መጫወት የቻለው።
ከትናንት ጀምሮ የተለያዩ የእንግሊዝ እና የጣሊያን ሚዲያዎች አርሰናል እና ኢንተር ሚላን ኤሪክሰን እና ዣካን ለመቀያየር ፍላጎት እንዳላቸው ሲዘግቡ ነበር። ነገር ግን አንደ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ ከሆነ ክርስቲያን ኤሪክሰን በድጋሚ ወደ እንግሊዝ መመለስ አይፈልግም። በጣሊያን ደስተኛ ባይሆንም በኢንተር ግን መቆየት እንደሚፈልግ እርግጥ ነው ይላል መረጃው።
ፖል ፖግባ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ምንም ችግር የለበትም። በወራት ውስጥ ዩናይትድ ለፖግባ አዲስ ኮንትራት ያቀርባል ፥ አዲስ የተፈጠረ ነገር የለም ሲል ታማኙ ዲማርዚዮ ተናግሯል።
No comments:
Post a Comment