Saturday, November 21, 2020

የዕለተ ቅዳሜ ስፖርታዊ ዜናዎች


 በዚዳን ስር በርካታ ጨዋታዎችን በተጠባባቂ ወንበር ላይ እያሳለፈ የሚገኘው ስፔናዊው ኮከብ ኢስኮ በጥር የዝውውር መስኮት ሪያል ማድሪድን መልቀቅ እንደሚፈልግ ማርካ አስነብቧል። ተጨዋቹ በተለያዩ የፕሪሚየር ሊግ እና የሴሪያው ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል። 





ጁቬንቱሶች የመሀል ሜዳ ክፍላቸውን ለማጠናከር አሁንም የተለያዩ ተጨዋቾችን እየተመለከቱ ይገኛሉ።Tuttosport እንዳስነበበው ከሆነ ጁቬዎች የሳሱሎውን የ22 አመት ተጨዋች ማኑኤል ሉካቶሊን በጥር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ከአሁኑ ለሳሱሎ ጥያቄ ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸው ተሰምቷል። 




ጀርመናዊው የጁቬንቱስ አማካይ ሳሚ ከዲራ በዚህ አመት ከኮንትራት ነፃ ሲሆን ወደ ሜጀር ሊግ ሶከር አልያም ወደ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ለማምራት መዘጋጀቱን የጀርመኑ ቢልድ አስነብቧል። 




በክረምቱ በብዛት ስሙ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ሲነሳ ቆይቶ በመጨረሻም እዛው በቦሩሲያ ዶርትመንድ የቆየው ጃደን ሳንቾ በቀጣዩ 2021 የክረምት የዝውውር መስኮት ዶርትመንድን መልቀቅ እንደሚፈልግ Todofichajes አስነብቧል። 




ካርሎ አንቾሎቲ ከቀድሞ ልጆቻቸው ጋር በድጋሚ ለመስራት ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው ሚረር አስነብቧል። አንቾሎቲ አሁን ላይ ሳሚ ካዲራን እና ኢስኮን በጥር የዝውውር መስኮት ወደ ኤቨርተን በማምጣት ቡድናቸውን ለማጠናከር ይፈልጋሉ። 




ሰርጂዮ ራሞስን ለማስፈረም ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ፍላጎት አሳይተዋል።እንደ 90min ዘገባ ከሆነ ሁለቱ የማንችስተር ከተማ ክለቦች አንዲሁም ሊቨርፑል እና ሶስቱ የለንደን ክለቦች ራሞስን ለማስፈረም ፍላጎት ያሳዩት ክለቦች ናቸው። 




አዲስ አጥቂ ማምጣት የማንችስተር ዩናይትድ የክረምት የዝውውር መስኮት ቀዳሚ አላማ ነው። ነገር ግን በጥር የዝውውር መስኮት የመሐል ተከላካይና የቀኝ ክንፍ አጥቂ ማስፈረም ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።






 ቅድመ ጨዋታ ትንታኔ | ቶተንሃም ከ ማን ሲቲ


በተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፡ ነገ ከቀኑ 8:30 በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ቶተንሃም ማንቸስተር ሲቲን ያስተናግዳል።

ይህን ጨዋታ ይበልጥ ተጠባቂ የሚያደርገው ደግሞ በሁለቱ ባላንጣ አሰልጣኞች ሆዜ ሞሪንሆ እና ፔፕ ጓርዲዮላ መሀከል የሚደረግ መሆኑ ነው።ከዚህ በፊት በኤልክላሲኮ እና በማንቸስተር ደርቢ በተቃራኒ የተገናኙት ሁለቱ የዘመናዊ እግር ኳስ ጠበብት አሰልጣኞች ፡ ዳግም በሌሎች ክለቦችም የሚገናኙ ይሆናል።


ሆዜ ፔፕ ጋርዲዮላ የመራቸውን ክለቦች በተቃራኒ ገጥመው 10 ጊዜ ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን ፡ በዚህም የጓርዲዮላን ያህል ያሸነፉት አሰልጣኝ የለም።ፔፕም በበኩሉ ከማኑዌል ፔሌግሬኒ ቀጥሎ የሆዜ ሞሪንሆን ክለቦች ነው በተደጋጋሚ ያሸነፈው።



የቡድን ዜናዎች


ስኬታማ ያልሆነ ጊዜን እያሳለፈ ያለው ማን ሲቲ በኢንተርናሽናል ብሬክ ናታን አኬን እና ናትናኤል ክላይን ላይ ጉዳት አስተናግደዋል።


አኬ የነገው ጨዋታ በጉልበት ጉዳት ምክንያት የሚያልፈው ሲሆን ስተርሊንግ ግን ያጋጠመው ቀለል ያለ ጉንፋን በመሆኑ ወደ ሰሜን ለንደን ይጓዛል።


በጡንቻ መሸማቀቅ ጉዳት ላይ የሰነበተው የማን ሲቲ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሰርጂዮ አጉዌይሮ ነገ ይመለሳል።


አጉዌይሮ ስፐርስ ላይ 11 ግብ ማስቆጠር ችሏል።


ማትት ዶሐርቲ ኮሮና ቫይረስ ስለተገኘበት ከስፐርስ ስብስብ ውጪ ሆኗል።


ኤሪክ ላሜላ ወደ ነገው ጨዋታ የመመለስ ዕድል ያለው ሲሆን ታንጉይ ንዶምቤሌ ግን ሙሉ ለሙሉ ከጉዳቱ አገግሞ ለነገው ጨዋታ ብቁ ነው።


በነገው ጨዋታ በዚህ ሲዝን በሁሉም የውድድር አይነቶች በ14 ጨዋታ 23 ግብ ላይ በቀጥታ የተሳተፈው ሀሪ ኬን ይጠበቃል።


 ግምታዊ አሰላለፍ

|ቶተንሃም|

ሎሪስ ፡ ኦሪየር ፡ ኤልደርዊልድ ፡ ዳየር ፡ ሪጊውለን ፡ ሲሶኮ ፡ ሆጅበርግ ፡ ቤል ሌ ሶልሶ ፡ ሰን እና ኬይን


|ማን ሲቲ|

ኤደርሰን ፡ ዎከር ፡ ዲያዝ ፡ ላፖርት ፡ ካንሴሎ ፡ ደ ብሮይነ ፡ ሮድሪ ፡ ጉንዶሓን ፡ ቶተስ ፡ ሄሱስ እና ፎደን

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...