ቅድመ ጨዋታ ትንታኔ | ቶተንሃም ከ ማን ሲቲ
በተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፡ ነገ ከቀኑ 8:30 በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ቶተንሃም ማንቸስተር ሲቲን ያስተናግዳል።
ይህን ጨዋታ ይበልጥ ተጠባቂ የሚያደርገው ደግሞ በሁለቱ ባላንጣ አሰልጣኞች ሆዜ ሞሪንሆ እና ፔፕ ጓርዲዮላ መሀከል የሚደረግ መሆኑ ነው።ከዚህ በፊት በኤልክላሲኮ እና በማንቸስተር ደርቢ በተቃራኒ የተገናኙት ሁለቱ የዘመናዊ እግር ኳስ ጠበብት አሰልጣኞች ፡ ዳግም በሌሎች ክለቦችም የሚገናኙ ይሆናል።
ሆዜ ፔፕ ጋርዲዮላ የመራቸውን ክለቦች በተቃራኒ ገጥመው 10 ጊዜ ማሸነፍ የቻሉ ሲሆን ፡ በዚህም የጓርዲዮላን ያህል ያሸነፉት አሰልጣኝ የለም።ፔፕም በበኩሉ ከማኑዌል ፔሌግሬኒ ቀጥሎ የሆዜ ሞሪንሆን ክለቦች ነው በተደጋጋሚ ያሸነፈው።
የቡድን ዜናዎች
ስኬታማ ያልሆነ ጊዜን እያሳለፈ ያለው ማን ሲቲ በኢንተርናሽናል ብሬክ ናታን አኬን እና ናትናኤል ክላይን ላይ ጉዳት አስተናግደዋል።
አኬ የነገው ጨዋታ በጉልበት ጉዳት ምክንያት የሚያልፈው ሲሆን ስተርሊንግ ግን ያጋጠመው ቀለል ያለ ጉንፋን በመሆኑ ወደ ሰሜን ለንደን ይጓዛል።
በጡንቻ መሸማቀቅ ጉዳት ላይ የሰነበተው የማን ሲቲ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሰርጂዮ አጉዌይሮ ነገ ይመለሳል።
አጉዌይሮ ስፐርስ ላይ 11 ግብ ማስቆጠር ችሏል።
ማትት ዶሐርቲ ኮሮና ቫይረስ ስለተገኘበት ከስፐርስ ስብስብ ውጪ ሆኗል።
ኤሪክ ላሜላ ወደ ነገው ጨዋታ የመመለስ ዕድል ያለው ሲሆን ታንጉይ ንዶምቤሌ ግን ሙሉ ለሙሉ ከጉዳቱ አገግሞ ለነገው ጨዋታ ብቁ ነው።
በነገው ጨዋታ በዚህ ሲዝን በሁሉም የውድድር አይነቶች በ14 ጨዋታ 23 ግብ ላይ በቀጥታ የተሳተፈው ሀሪ ኬን ይጠበቃል።
ግምታዊ አሰላለፍ
|ቶተንሃም|
ሎሪስ ፡ ኦሪየር ፡ ኤልደርዊልድ ፡ ዳየር ፡ ሪጊውለን ፡ ሲሶኮ ፡ ሆጅበርግ ፡ ቤል ሌ ሶልሶ ፡ ሰን እና ኬይን
|ማን ሲቲ|
ኤደርሰን ፡ ዎከር ፡ ዲያዝ ፡ ላፖርት ፡ ካንሴሎ ፡ ደ ብሮይነ ፡ ሮድሪ ፡ ጉንዶሓን ፡ ቶተስ ፡ ሄሱስ እና ፎደን
No comments:
Post a Comment