ትናንት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተደረጉ ጨዋታዎች የተመዘገቡ ውጤቶች
ብራይተን 1-1 ሊቨርፑል
ማንቸስተር ሲቲ 5-0 በርንሌይ
ኤቨርተን 0-1 ሊድስ ዩናይትድ
ዌስት ብሮም 1-0 ሼፍልድ ዩናይትድ
አርሰናል በክለቡ ሪከርድ ዋጋ ያስፈረመውን ኮትዲቯራዊውን የመስመር አጥቂ ኒኮላስ ፔፔ ለመሸጥ ይፈልጋል።ከተለያዩ ክለቦችም ጥያቄ እየጠበቀ ነው።
(Daily Star Sunday)
ብራዚላዊው አማካይ ፈርናንዲንሆ አዲስ ኮንትራት ስላልቀረበለት በአመቱ መጨረሻ ማንቸስተር ሲቲ እንደሚለቅ ይጠበቃል።
(Sunday Mirror)
ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ሪያል ማድሪድን ዳግም በጋላክቲኮስ የመገንባት ዓላማ ያላቸው ሲሆን በቅድሚያ 2021 ላይ ምባፔን 2022 ላይ ደግሞ ኤርሊንግ ሀላንድን ለማዘዋወር ከወዲሁ ዕቅድ አውጥተው እየሰሩ ነው።
(AS)
የባርሴሎናው ተከላካይ ዤራርድ ፒኪዌ ሜሲ በባርሴሎና ይቆያል ብሎ ተስፋ እንደሚያደርግ ተናግሯል።
(ESPN)
የኢንተር ሚላኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጁሴፔ ማሮታ በጥር ወር የዝውውር መስኮት ዴንማርካዊው አማካይ ክርስቲያን ኤሪክሰን ከክለቡ እንደሚለቅ አረጋግጠዋል።
(Sky Sports)
የብራዚላዊው አማካይ ፌሊፔ ኩቲንሆ ስም በስፋት ከዩቬንትስ ጋር ቢያያዝም ከባርሴሎና እንደማይለቅ ወኪሉ ይፋ አድርጓል።
(Mundo Deportivo - in Spanish)
አርጀንቲናዊው አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ ኢንተር ሚላንን መልቀቅ ይፈልጋል።ወኪሉ የሆነው ሆርጌ ሜንዴዝም አዲስ ክለብ እየፈለገ ይገኛል።ማንቸስተር ሲቲ ፣ ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ደግሞ የተጨዋቹ ፈላጊዎች ናቸው።
(Marca)
No comments:
Post a Comment