አዘጋጅ - ኢብራሂም ሙሐመድ
ኢንተር ሚላኖች በቀጣይ ክረምት አርጀንቲናዊውን አጥቂያቸውን ላውታሮ ማርቲኔዝን ሚሸኙ ከሆነ በሱ ምትክ ሜክሲኮዋዊውን የወልቭስ አጥቂ ራዎል ሂሚኔዝን ማምጣት እንደሚፈልጉ CalcioMercatoWeb ሲያስነብብ ተጨዋቹ ከኢንተር ሚላን በተጨማሪም ጁቬንቱስም ሂሚኔዝን ማስፈረም ይፈልጋሉ።
አርሰናሎች በጥር የዝውውር መስኮት ተጨማሪ ተከላካይ ወደ ኢምሬት ለማምጣት ካሁኑ ስራዎችን ጀምረዋል። እንደ TodoFichajes ዘገባ ከሆነ አርሰናሎች ከአርቢ ሌብዢኩ የ21 አመት ኮከብ ኢብራሂም ኮናቴ ጋ ስማቸው እየተያያዘ ነው። ተጨዋቹንም ለማስፈረም ካሁኑ ከተጨዋቹ ወኪሎች ጋር ንግግር መጀመራቸው ታውቋል።
ሴልቲኮች በዚህ አመት መጨረሻ ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን የክርስቲያል ፓላስ ኮከብ ጀምስ ማካርቲን በረጅም ጊዜ ኮንትራት በጥር የዝውውር መስኮት ማስፈረም እንደሚፈልጉ Team Talk አስነብቧል። ተጨዋቹ በፓላስ ኮንትራት ማራዘም እንደማይፈልግ ሲናገር ልጁን ከሴልቲክ በተጨማሪ የእንግሊዞቹ አስቶንቪላ እና በርንሌ ማስፈረም ይፈልጋሉ።
ሁለቱ የለንደን ክለቦች የሆኑት ቸልሲ እና ዌስትሀም ዩናይትድ በ18 አመቱ የአርቢ ሌብዢኩ ተከላካይ ማትሂው ቦንድስዌል ላይ ትልቅ ልጁን የመውሰድ ፍላጎት ማሳየታቸውን Telegraph አስነብቧል። ተጨዋቹ በዚህ ሰአት FC Dordrecht በውሰት እየተጫወቸ ይገኛል።
ጁቬንቱሶች እስፔናዊውን የ29 አመት የአትሌቲኮ ማድሪድ ተከላካይ ስቴፋን ሳቪችን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው Calcio Mercato አስነብቧል። ተጨዋቹ በአትሌቲኮ ቤት ኮንትራቱ በ2022 የሚጠናቀቅ ሲሆን ተጨማሪ ኮንትራት ለመፈረም ፍላጎት የሌለው ሲሆን አትሌቲዎችም ተጨዋቹን ለመሸጥ ዝግጁ ናቸው።
ማንችስተር ዩናይትዶች የቪያሪያሉን ስፔናዊ ተከላካይ ፓው ቶሬስን ለማስፈረም ዝግጁ ሆነዋል። ተጨዋቹንም ለማስፈረም ሲሉ ማንችስተሮች ሊንደሎፍን ሮሆን ቤይሊን ጆንስን በመሸጥ ቶሬስን ለማምጣት እንደሚፈልጉ TEAMtalk አስነብቧል።በተጨማሪም ዩናይትዶች የሌብዢኩን ኡፓምካኖንም ወደ ኦልትራፎርድ ማምጣት ይፈልጋሉ።
ኒውካስትል ዩናይትዶች የቸልሲውን ወጣት ተከላካይ ፊካዮ ቶሞሪን በውሰት ለማስፈረም አንደሚፈልጉ እና ለቸልሲ በይፋ ጥያቄ ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውን Northern Echo አስነብቧል።የ22 አመቱ ተከላካይ በዌስትሀምም ይፈለጋል ማረፊያው ግን ኒውካስትል መሆኑ አይቀሬ ነው።
ዴንማርካዊው ክርስቲያን ኤሪክሰን በጥር የዝውውር መስኮት ኢንተር ሚላንን መልቀቁ እውን እየሆነ መምጣቱን የጣሊያኑ ጋዜጣ Calciomercato አስነብቧል። ተጨዋቹ በቀድሞ ክለቡ ቶተንሀም አርሰናል ሪያል ማድሪድ ፒኤስጂ አሁን ላይ በጥብቅ ይፈለጋል።
No comments:
Post a Comment