ኤሲ ሚላኖች በትላልቅ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሚፈለገውን የማርሴውን የ21 አመቱን ቦባካር ካማራን በጥር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ዝግጁ መሆናቸውን Calciomercato አስነብቧል።የማርሴው ኮከብ ግን አሁን ላይ ማርሴን ስለመልቀቅ እንደማያስብ የፈረንሳዩ L'Equipe አስነብቧል።
በተከላካይ መስመር ተጨዋቾቻቸው ብዙም ደስተኛ ያልሆኑት የኤቨርተኑ አሰልጣኝ አንቾሎቲ በጥር የዝውውር መስኮት ሌላ ተከላካይ ለማስፈረም ወደ ገበያ እንደሚወጡ The Sun አስነብቧል።እንደ Mundo Deportivo ዘገባ ከሆነ ኤቨርተኖች የመጀመሪያ ምርጫቸው በባርሴሎና ቤት ቦታ ያጣው ፈረንሳዊው ሳሙኤል ኡምቲቲ ነው።
የአያክስ የግራ መስመር ተከላካይ ኒኮላስ ታግሊፊኮ በጥር የዝውውር መስኮት ወደ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች መዘዋወር እንደሚፈልግ Daily Mail አስነብቧል።ተጨዋቹ በአያክስ አዲስ ኮንትራት የቀረበለት ሲሆን ልጁ ግን ወደ ፕሪሚየር ሊግ መምጣትን መርጧል። ተጨዋቹ በሌስተር ሲቲ እና በማንችስተር ሲቲ በጥብቅ ይፈለጋል።
ጁቬንቱሶች ከቸልሲ ሁለት ተጨዋቾችን ለማስፈረም ፍላጎት አላቸው። አንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ ከሆነ አሮጊቶቹ አጥቂውን ኦሊቨር ዡሩድን እና ኤመርሰን ፓልሜራን ነው ከብሪጅ ለማስኮብለል ፍላጎት ያሳዩት።
ባርሴሎናዎች በጥር የዝውውር መስኮት ተከላካይ ለማስፈረም ወደ ገበያ ይወጣሉ።የመጀመሪያ ምርጫቸው የማንችስተር ሲቲው ኤሪክ ጋርሺያ ሲሆን ሲቲዎች በጥር ማይለቁት ከሆነ የቸልሲውን ተከላካይ አንቶኒዮ ሩዲገርን ማስፈረም እንደሚፈልጉ Mundo Deportivo አስነብቧል።
ሬንሶች የፈረንሳዊውን ወጣት አማካይ ኤድዋርዶ ካማቪንጋን የመሸጫ ዋጋ ወደ €50m ቀንሰውታል የተጨዋቹ ኮንትራት በ2022 የሚጠናቀቅ ሲሆን ልጁ ኮንትራት ከማደስ ይልቅ ወደ ሌላ ክለብ ለመሄድ ስለሚፈልግ ሬንሶች ተጨዋቹን ዋጋውን አውርደው ለመሸጥ ዝግጁ መሆናቸውን AS አስነብቧል።ተጨዋቹ በፒኤስጂ ፣ በሪ.ማድሪድ እና ጁቬንቱስ ይፈለጋል።
ማንችስተር ዩናይትድ እና ቸልሲ በስዊዘርላንዳዊው የቦሩሲያ ሞንቼግላድባ አማካይ ዴኑስ ዛካሪያ ዝውውር ላይ መፋጠጣቸውን Daily Star አስነብቧል። ተጨዋቹንም ለመውሰድ ሁለቱም ክለቦች ለተጨዋቹ ወኪል ጥያቄ አቅርበዋል።ነገር ግን እስካሁን ሁለቱም ክለቦች ይፋዊ ጥያቄ ለጀርመኑ ክለብ ቦ.ሞንቼግላድባ አላቀረቡም።
ኒውካስትል ዩናይትድ እና ሳውዝሀምፕተን በማንችስተር ዩናይትዱ የግራ መስመር ተከላካይ ብራንደን ዊሊያምስ ላይ ፍላጎት አሳይተዋል። የ20 አመቱ ኮከብ የቴሌስ ማንችስተር መምጣትን ተከትሎ በተደጋጋሚ ከጨዋታ ውጭ እየሆነ ስለሚገኝ ተጨማሪ የመጫወቻ ጊዜ ለማግኘት ዩናይትድን መልቀቅ ይፈልጋል።ይህንንም ተከትሎ ሁለቱ ክለቦች ልጁን በጥር በውሰት ለመውሰድ ፍላጎት ማሳየታቸውን The Chronicle አስነብቧል።
No comments:
Post a Comment