ሁለቱ የሴሪያ ክለቦች የሆኑት ጁቬንቱስ እና ኢንተር ሚላን የፒኤስጂውን አርጀንቲናዊውን ኮከብ አንሄል ዲማሪያን በክረምት ለማስፈረም ፉክክር ውስጥ መግባታቸውን Calcio Mercato አስነብቧል። ፒኤስጂዎች እስካሁን ለተጨዋቹ ኮንትራት ያላቀረበለት ሲሆን ልጁም በክረምት ክለቡን ለመልቀቅ መዘጋጀቱ ታውቋል።
አርጀንቲናዊው የጁቬንቱስ ኮከብ ፓብሎ ዲባላ በተለያዩ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ራዳር ውስጥ መግባቱን 90min አስነብቧል።በጁቬ ተጨማሪ ኮንትራት ያለው ዲባላ አሁን ላይ በፒርሎ ስር ደስተኛ እንዳልሆነ የተነገረ ሲሆን በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ማቅናቱ አይቀሬ ሆኗል።
አርሰናሎች የማንችስተር ሲቲውን እንግሊዛዊውን የመሀል ተከላካይ ጆን ስቶንስን ለማስፈረም አንደሚፈልጉ 90min ያስነበበ ሲሆን አርሰናሎች ልጁን በጥር ለማምጣት ይፈልጋሉ። ስቶንስ በማንችስተር ሲቲ እስከ 2022 ኮንትራት ያለው ሲሆን ማንችስተር ሲቲዎች የተጨዋቹን ኮንትራት ለማራዘም ፍላጎት የላቸውም።
ማንችስተር ዩናይትዶች በቀጣይ ክረምት ዝውውር አሮዋን ቢሳካን ሚፎካከር የቀኝ መስመር ተከላካይ አንደሚያስፈርሙ M.E.N አስነብቧል።ዩናይትዶች አሁን ላይ ዋነኛ ትኩረታቸው የአትሌቲኮ ማድሪዱ ኬራን ትሪፒየር ሲሆን የሱ ዝውውር ማይሳካ ግን የሪያል ማድሪዱን ቫስኩዌዝን ለማምጣት እቅድ አላቸው።
ኤሲ ሚላኖች በጥር የዝውውር መስኮት ተጨማሪ ተከላካይ ለማስፈረም ወደ ገበያው እትደሚወጡ አሰልጣኙ ይፋ ሲያደርጉ በጥርም የዝውውር መስኮት የመጀመሪያ እቅዳቸው የቶተንሀሙ ዳቪድሰን ሳንቼዝ መሆኑ The Sun ያስነበበ ሲሆን ሚላኖች ልጁን በውሰት አልያም በቋሚ ዝውውር ልጁን ለመውሰድ ዝግጁ ናቸው።
በዚህ አመት ኮንትራቱ ከአርሰናል ጋር የሚጠናቀቀው ጀርመናዊው አማካይ ሜሱት ኦዚል በቀጣይ አመት ወደ ትልቅ ክለብ ለማምራት ዝግጁ እንደሆነ The Mirror ያስነበበ ሲሆን ወደ የትኛው ሊግ ማምራት እንደሚፈልግ ግን እስካሁን አልታወቀም።
በጁቬንቱስ ቦታ እንደሌለው የተነገረው እና በዚህ አመት ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው ሳሚ ከዲራ በጥር የዝውውር መስኮት የተለያዩ የቻምፒዮንስ ሺፕ ክለቦች ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።ተጨዋቹ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች መሄድ ቢፈልግም ዋትፎርድ ፣በርንማውዝ እና ኖርዊች ተጨዋቹን ለመውሰድ ፍላጎት አላቸው።
ቸልሲዎች እንግሊዛዊውን ካሉም ሁድሰን ኦዶይን እንደማይለቁት ይፋ አድርገዋል። ለተጨዋቹ ኮንትራት ቢያቀርቡለትም ለመፈረም ፍላጎት አቷ። ነገር ግን ልጁን ቸልሲዎች አሳልፈው ለመስጠት አይፈልጉም ፤ ኦዶይ በሙኒክ በጥብቅ ይፈለጋል።
No comments:
Post a Comment