ቶተንሀሞች የ22 አመቱን የስቱትጋርት የመስመር ተጨዋች ኒኮ ጎንዛሌዝን ለማስፈረም ትልቅ ፍላጎት ማሳየታቸውን AS አስነብቧል።ተጨዋቹ በጁቬንቱስም ይፈለጋል። ከስቱትጋርት ጋር እስከ 2024 የሚያቆይ ኮንትራት አለው።
ባየርን ሌቨርኩሰን እና ጋላታሳራይ በስትራስቡርጉ የመስመር ተከላካይ ኬኒ ላላ ላይ ፍላጎት እንዳሳዩ Le10Sport አስነብቧል። ተጨዋቹ ኮንትራቱ በዚህ አመት መጨረሻ ይጠናቀቃል። ይሄን ተከትሎ ሁለቱም ክለቦች ልጁን በነፃ ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
ማርክሮካ በጥር የዝውውር መስኮት ከባየርን ሙኒክ መልቀቅ እንደማይፈልግ እና በባየርን ለቦታው እንደሚፋለም AS አስነብቧል። ተጨዋቹ በቫሌንሲያ በጥብቅ ይፈለጋል። ሮካ በዚህ ሲዝን በቡንደስሊጋው አምስት ጨዋታ ብቻ ነው ማድረግ የቻለው።
ማንችስተር ሲቲዎች በኤሲ ሚላን እና ጁቬንቱስ በጥብቅ የሚፈለገውን የሳሱሎ የመሀል ተጨዋች ማኑኤል ሉካቶሊን ለማስፈረም እንቅስቃሴ እንደጀመሩ ዴይሊ ሜይል አስነብቧል። ሲቲዎች ለተጨዋቹ እስከ £30m ለመክፈል ፍላጎት አላቸው።
በዚህ አመት መጨረሻ ኮንትራቱ ከማንችስተር ሲቲ ጋር የሚጠናቀቀውን ሰርጂዮ አጉዌሮን በአመቱ መጨረሻ በነፃ ለማስፈረም ከፈላጊዎቹ ክለቦች ቀድመው ልጁን ለመውሰድ ባርሴሎናዎች እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ዘሰን አስነብቧል።
ባየርን ሙኒኮች የመሀል ሜዳ ክፍላቸውን ለማጠናከር የተለያዩ ተጨዋቾችን እየተመለከቱ ይገኛሉ። እንደ ቢልድ ስፖርት ዘገባ ከሆነ ሙኒኮች የቦሩሲያ ሞንቼግላድባውን አማካይ ፍሎሪን ኒዩሀስን ለማስፈረም ለሞንቼግላድባ £40m ለማቅረብ መዘጋጀታቸው ታውቋል።
አርቢሌብዢኮች በበርካታ ክለቦች ሲፈለግ የነበረውን ወጣቱን የአርሰናል ተጨዋች ፎላሪ ባሎጉን በነፃ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር ከስምምነት መድረሱን Football Insider አስነብቧል።ተጨዋቹ ኮንትራቱ በዚህ አመት መጨረሻ ይጠናቀቃል። አዲስ ኮንትራት ከአርሰናል ቢቀርብለትም ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።
የዎልቭሱ አሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪንቶ ሳንቼዝ የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ሁለቱን የቸልሲ አጥቂ ኦሊቨር ዡሩድ እና የሊቨርፑሉን ዲቮክ ኦሪጊን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ዘ ሚረር አስነብቧል።
ማንችስተር ዩናይትዶች በጥር የዝውውር መስኮት ጄሲ ሊንጋርድን ወራጅ ቀጠና ላሉ ክለቦች ለመስጠት እንደማይፈልጉ M.E.N አስነብቧል። ተጨዋቹ በሼፊልድ ዩናይትድ በጥብቅ ይፈለጋል።
ቶተንሀሞች ብራዚላዊውን የሪያል ማድሪድ የመሀል ተከላካይ ኤደር ሚሊታኦን ለማስፈረም ንግግር መጀመራቸውን ዴይሊ ሜይል አስነብቧል። በዚዳን ስር የመሰለፍ እድል የተነፈገው ሚሊታኦ የበርናባው መውጫ በር ላይ ይገኛል። ቶተንሀሞች ለተጨዋቹ እስከ £30m ለመክፈል ፍላጎት አላቸው።
No comments:
Post a Comment