Wednesday, January 13, 2021

የዕለተ ረቡዕ ስፖርታዊ ዜናዎች

አዘጋጅ - ኢብራሂም ሙሐመድ 



ሪያል ማድሪዶች በቀጣዩ ክረምት የዝውውር መስኮት ፈረንሳዊውን የፒኤስጂ ኮከብ ክሊያን ምባፔን ለማስፈረም ሲሉ ወደ ስድስት የሚጠጉ ተጨዋቾችን ወደ ገበያ እንደሚያወጡ AS claim አስነብቧል።እንደዘገባው ከሆነ ማድሪዶች ቤል፣ ኢስኮ፣ ሴባዮስ፣ ዮቪች፣ ዲያዝ እና ማርሴሎን እስከ £90m በመሸጥ በምትኩ ምባፔን በ£135m ለማስፈረም ነው የፈለጉት። 





አትሌቲኮ ማድሪዶች የሄርታ በርሊኑን የ21 አመት የመስመር ተጨዋች ማቲያል ጭሁናን ለማስፈረም ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው  Sky Germany አስነብቧል። ተጨዋቹን ጁቬንቱስ እና ኢንተር ሚላን ቢፈልጉትም አትሌቲዎች ግን ገፍተው መተው ንግግር ጀምረዋል። 





አርሰናል እና ኤቨርተን ፈረንሳዊውን የ32 አመት አማካይ ስቴቨን ንዞንዚን ለመውሰድ ፍላጎት ማሳየታቸውን ዴይሊ ሜይል አስነብቧል። ተጨዋቹ በዚህ አመት በውሰት በፈረንሳዩ ሬንስ ክለብ የሚገኝ ሲሆን በቆይታውም ደስተኛ አይደለም። ይህን ተከትሎ ሁለቱ ክለቦች ልጁን ለመውሰድ ትልቅ ፍላጎት አሳይተዋል። 





ታማኙ ጋዜጠኛ ፋቢሪዚዮ ሮማኖ በበርካታ ክለቦች የሚፈለገው ፈረንሳዊው የሌብዢክ ተከላካይ ዳዮት ኦፖምካኖ በጥር የዝውውር መስኮት ወደ የትኛውም ክለብ እንደማያመራ ከክለቡ ሰዎች ይፋ እንደተደረገ አስነብቧል።ተጨዋቹን በጥር ለማስፈረም ዩናይትድ እና ቸልሲ ቢፈልጉም ሌብዢኮች ግን በጥር ሊለቁት አይፈልጉም። 






የቸልሲው ባለ ሀብት ሮማን አብራሞቪች ላምፓርድን ለማሰናበት አሁን ላይ ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌለው Team Talk አስነብቧል። እንደ መረጃው ከሆነ ባለ ሀብቱ የቀድሞውን የቸልሲ አሰልጣኝ አብርሀም ግራንት የአሰልጣኝ ቡድኑ ውስጥ በማካተት እንዲረዳው እንደሚፈልጉ እና እንደሚያመጡት ተሰምቷል። 





አርሰናል እና የጀርመናዊው የፒኤስጂ የመስመር አጥቂ ጁሊያን ዲያክስለር ሰዎች በክረምት በነፃ ወደ ኢምሬት ለማምጣት ንግግር መጀመራቸውን ዘሰን አስነብቧል። ተጨዋቹ ከፒኤስጂ ጋር ያለው ኮንትራት በዚህ አመት መጨረሻ ይጠናቀቃል። 





ብራዚላዊው የፒኤስጂ ኮከብ ኔይማር ጁኒየር በክለቡ ለተጨማሪ አመታት ለመቆየት እንደተስማማ እና በቀጣይ ሳምንታት አዲስ ኮንትራት እንደሚፈርም Mundo Deportivo አስነብቧል።ተጨዋቹ በፒኤስጂ ያለው ኮንትራት 2022 ይጠናቀቃል። 





ቫሌንሲያዎች ለቶተንሀሙ እንግሊዛዊ አማካይ ሀሪ ዊንክስ ለሁለተኛ ጊዜ የውሰት ጥያቄ Guillem Balague ማቅረባቸውን ተናግሯል። ቶተንሀሞች እስካሁን መልስ አልሰጡም ፤ ጆዜ ልጁን ለማቆየት ብዙም ፍላጎት ባይኖራቸውም በቀላሉ ይለቁታል ተብሎ አይጠበቅም። 





አርሰናሎች የሻካታር ዶኔስኩን የ21 አመት ኮከብ ማኖር ሶሎሞንን ለማስፈረም ትልቅ ፍላጎት እንዳሳዩ Guardian አስነብቧል። ተጨዋቹ በዚህ ሲዝን ለሻካታር ዶኔስክ 17 ጨዋታዎችን አድርጎ አምስት ጎሎችን አስቆጥሯል። 





በዚህ አመት መጨረሻ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን አርጀንቲናዊ አጥቂ ሰርጂዮ አጉዌሮን በነፃ ለማስፈረም ሁለቱ የላሊጋ ክለቦች ባርሴሎና እና የቀድሞ ክለቡ አትሌቲኮ ማድሪድ ፍላጎት አሳይተዋል።የ32 አመቱን አጥቂ ፒኤስጂዎችም ይፈልጉታል።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...