Friday, January 1, 2021

የዕለተ ዓርብ ከሰዓት ስፖርታዊ ዜናዎች


 

ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ ክለብ አልባ ሆኖ የቀረው ጃክ ዊልሼር ከተለያዩ የሜጀር ሊግ ሶከር ክለቦች የእናስፈርምህ ጥያቄ እንደቀረበለት The Times አስነብቧል። ተጨዋቹ አሁን ላይ ከቻምፒዮን ሺፑ ክለብ በርንማውዝ ጋር ልምምድ እየሰራ ይገኛል። 





ጁቬንቱሶች በጥር የዝውውር መስኮት ሁለት ዝውውሮችን ለመፈፀም እንቅስቃሴ እንደጀመሩ Goal.com አስነብቧል። ጁቬዎች ትናንት ማምሻውን አንደተሰማው ከሆነ ወጣቱን የጄኑዋውን አማካይ ኒኮሎ ሮቬላን ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ታውቋል። 






ብራይተኖች ግብ ጠባቂያቸው ማት ሪያን ለመልቀቅ መወሰኑን ተከትሎ የማንችስተር ዩናይትዱን አራተኛ ግብ ጠባቂ የሆነውን እና በክለቡ እንደማይፈለግ የተነገረውን ሰርጂዮ ሮሜሮን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው Daily Mail አስነብቧል።ሮሜሮ በቫሌንሲያም እየተፈለገ ይገኛል። 





ቶተንሀሞች ኮንትራቱ ወደ ማብቂያው የደረሰው እና በሀገሩ ክለብ ፒኤስጂ እየተፈለገ የሚገኘውን ሁጎ ሎሬስን ለማቆየት ፈተና እንደሆነባቸው ዴይሊ ሜይል አስነብቧል። ይሄንን ተከትሎ ቶተንሀሞች እሱን ለመተካት የዩናይትዱን ሁለተኛ ግብ ጠባቂ ዲን ሄንደርሰንን ወይም የዌስትብሮሙን ግብ ጠባቂ ሳም ጆንስቶንስን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል። 






ማንችስተር ሲቲዎች የኩን አጉዌሮን ተተኪ ለማግኘት ወደ ገበያ ለመውጣት ዝግጁ ናቸው ።ዛሬ ጠዋት በወጡ መረጃዎች ሲቲዎች የቶተንሀሙን ሀሪ ኬንን ለማስፈረም ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው ስካይ ስፖርት አስነብቧል።ሲቲዎች ለአጥቂው እስከ £100m ለማውጣት ፍላጎት እንዳላቸውም ተነግሯል። 






ጀርመናዊው የጁቬንቱስ አማካይ ሳሚ ከዲራ የእግር ኳስ ሂወቱን በፕሪሚየር ሊግ ማጠናቀቅ አንደሚፈልግ ከተናገረ በኋላ ኤቨርተን እና ቶተንሀም ልጁን ለማስፈረም በይፋ ከወኪሉ ጋር ንግግር እንደጀመሩ Daily Mail አስነብቧል። ነገር ግን ከቶተንሀም ይልቅ ኤቨርተኖች ከዲራን የማግኘት እድል እንዳላቸው ተሰምቷል። 






አርሰናል እና ሊቨርፑል በብዙ ክለቦች የሚፈለገውን የሮማውን ተከላካይ ለማስፈረም ሮጀር ኢባኔዝን ለማስፈረም የሚደረገውን ዝውውር በይፋ መቀላቀላቸውን Calciomercato አስነብቧል።ተጨዋቹ በበርካታ ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል። 




ማንችስተር ዩናይትዶች የሲቪያውን ተከላካይ ጁሌስ ኩንዴን በቀጣይ የክረምት የዝውውር መስኮት ለማስፈረም እንደሚፈልጉ Mundo Deportivo አረጋግጧል። ተጨዋቹ በከተማ ተቀናቃኛቸው ማንችስተር ሲቲም የሚፈለግ ሲሆን ዩናይትዶች የተጠየቁትን በመክፈል ልጁን ለማስፈረም ይፈልጋሉ። 





ቸልሲዎች በድጋሚ የጃደን ሳንቾ ፈላጊ ሆነው መምጣታቸውን Que Golazo አስነብቧል። በክረምት የዝውውር መስኮት ልጁ ላይ ያላቸውን ፍላጎት ቢያነሱም አሁን ግን ሳንቾን ወደ ብሪጅ ለማምጣት ዝግጁ መሆናቸው ታውቋል። ሳንቾ በዩናይትድም በጥብቅ ይፈለጋል። 




ጀርመናዊው የፒኤስጂ የመስመር አጥቂ ጁሊያን ዲያክስለር በድጋሚ በሊድስ ዩናይትድ ራዳር ውስጥ መግባቱን Gazzetta dello Sport አስነብቧል። ሊድሶች በክረምት ልጁን ፈልገውት ቢሆንም ዝውውሩ ሳይሳካ ቀርቷል ይህን ተከትሎ ሊድሶች በጥር ዲያክስለርን ለማምጣት ፍላጎት እንዳላቸው ታውቋል። 





በዚህ አመት ኮንትራቱ የሚጠናቀቀውን የሌስተር ሲቲ የመስመር አጥቂ ዲማራይ ግራይን በአመቱ መጨረሻ በነፃ ለማስፈረም ቤኔፊካ እና ሮማ ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው ዘሰን አስነብቧል። ተጨዋቹ እስካሁን በሌስተር አዲስ ኮንትራት አልቀረበለትም።

No comments:

Post a Comment

"ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል

 "ቱሪን አሁንም በልቡ ውስጥ አለ" ራዮላ ፖግባ ወደ ዩቬንትስ ሊመለስ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ወኪል የሆነው ሚኖ ራዮላ ፤ አማካዩ በክረምት የዝውውር መስኮት ወደ ቱሪን ሊመለ...