በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ያለ ደጋፊ ደብዝዞ እየቀጠለ ባለው እግር ኳስ ፤ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አያሌ አዳዲስ ሁነቶችን እየታዘብን እንገናኛለን።
በዘንድሮም ሲዝን የባለፈው አመቱ ሻምፒዮን ሊቨርፑል በመሪ ሆኖ እየቀጠለ ሲሆን ማንቸስተር ዩናይትድ ደግሞ በሁለተኝነት እየተከተለ ይገኛል።ማንቸስተር ሲቲ ፣ ቶተንሀም ፣ ቼልሲ ፣ ሌስተር ሲቲ እና ኤቨርተንም ለሻምፒዮንነት ከአሁኑ መተንበይ ቢያዳግትም ጥሩ የውድድር ትራክ ላይ ያሉ ይመስላል።
ለዛሬ 16 ሳምንታትን ባስቆጠረው እና ሊጋመስ ሁለት ጨዋታ በቀረው ሊግ ላይ Goal .com ከOpta በወሰደው አሃዛዊ መረጃ የመረጣቸውን ምርጥ 11 እንድትመለከቱ ጋብዘናል።
ግብ ጠባቂ - ኤሚልያኖ ማርቲኔዝ (አስቶን ቪላ)
የቀኝ ተከላካይ - ሪስ ጄምስ (ቼልሲ)
የመሀል ተከላካይ - ከርት ዙማ (ቼልሲ)
የመሀል ተከላካይ - ፋቢንሆ (ሊቨርፑል)
የግራ ተከላካይ - አንድሪው ሮበርትሰን (ሊቨርፑል)
የተከላካይ አማካይ - ዬቬስ ቢሳውማ (ብራይተን)
የቀኝ አጥቂ - ሙሐመድ ሳላህ (ሊቨርፑል)
የአጥቂ አማካይ - ብሩኖ ፈርናንዴዝ (ማንቸስተር ዩናይትድ)
የአጥቂ አማካይ - ጃክ ግሪሊሽ (አስቶን ቪላ)
የግራ አጥቂ - ሰን ሂውንግ ሚን (ቶተንሀም)
አጥቂ - ሀሪ ኬን (ቶተንሀም)
No comments:
Post a Comment