እንደ አብዛኛዎቹ አፍሪካውያን ማኔ በድህነት ውስጥ ያደገ ነው።ይህ አሁን
በሚሊዮን ፓውንዶች በየአመቱ የሚያገኘው ሴኔጋላዊ ልጅነቱ እምብዛም
አስደሳች አልነበረም።ሆኖም አሁን ያ ጊዜ አልፎ ሀገሩን እና ያሳደገውን አካባቢ
በቻለው አቅም ሁሉ እየረዳ ነው።ማኔ ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቅ እንዲህ አለ ፡
"አስር ፌራሪ መኪና ፣ ሀያ የዳይመንድ ሰዓቶች ፣ ወይም ሁለት አውሮፕላን ለኔ
ምን ያደርግልኛል? እነዚህ ቁሶች ለእኔ እና ለተቀረው ዓለም ምን ያደርጋሉ?
"በልጅነቴ የረሀብ ጊዜያትን አሳልፌያለሁ።ከባባድ ጊዜያትን አልፌያለሁ ።እግር
ኳስን በባዶ እግሬ ነበር የምጫወተው ፥ በድህነት ምክንያት ትምህርት መማር
አልቻልኩም ፥ ብቻ ብዙ ብዙ።ነገር ግን አሁን ያ ሁሉ አልፎ ምስጋና ከእግር ኳስ
ይሁንና ከራሴ አልፌ ሕዝቤንም እረዳለሁ።
"በሀገሬ ትምህርት ቤቶችን ፣ ስቴዲየም ሰርቻለሁ።ልብስ ፣ ጫማ እና ምግብ
ደግሞ ከፍተኛ ድህነት ውስጥ ላሉት እሰጣለሁ።ኑሮዋቸውን እንዲያሻሽሉ
በተወለድኩበት መንደር ለሚገኙ ሰዎች ለየቤተሰቡ በወር 70 ዩሮ እሰጣለሁ።
"እናም እኔ ቅንጡ መኪናዎች ፣ ቅንጡ ቤት ፣ መዝናናት እና አውሮፕላን ምናምን
አልፈልግም።ከዚ ይልቅ በሕይወት አጋጣሚ ካገኘሁት ለሕዝቤ ባካፍክ
እመርጣለሁ።"
No comments:
Post a Comment