ሁለቱ የሰሜን ለንደን ክለቦች አርሰናል እና ቶተንሀም የኤሲ ሚላኑን አማካይ ፍራንክ ኬሴን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል።ተጨዋቹ በኤሲ ሚላን ያለው ኮንትራት በ2022 የሚጠናቀቅ ሲሆን ኤሲ ሚላኖች ከልጁ ዝውውር እስከ €45m ይፈልጋሉ። ነገር ግን ሁለቱም ክለቦች ይህን ለመክፈል ፍቃደኛ አለመሆናቸውን Calcio Mercato አስነብቧል።
ከቻይናው Shanghai SIPG ክለብ ጋር ኮንትራቱን እንደማያራዝም ይፋ ያደረገው ብራዚላዊው የ34 አሙቱ ሀልክ በተለያዩ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል። ተጨዋቹ ከኮንትራት ነፃ ሲሆን ስማቸው ያልተጠቀሰ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች እና የፖርቱጋሉ ፖርቶ የልጁ ፈላጊ እንደሆኑ ዘ ሰን አስነብቧል።
ከፖል ፖግባ ጋር ለመለያየት ከጫፍ የደረሱት ማንችስተር ዩናይትዶች በሱ ምትክ የተለያዩ ተጨዋቾችን ለማስፈረም እየተመለከቱ ሲገኝ የመጀመሪያ ምርጫቸው የኒሱ ኤድዋርዶ ካማቪጋ ሲሆን ከሱ በተጨማሪ የላዚዮ ሚሊንኮቪች ሳቪች እንዲሁም የዌስትሀም ዩናይትዱ ዴክላን ራይስ እንደሆኑ M.E.N አስነብቧል።
ቶተንሀም እና ኤቨርተን በሬንጀርሱ ኮከብ ጀምስ ታቬርነር ዝውውር ላይ ፉክክር ውስጥ መግባታቸውን ዴይሊ ሜይል አስነብቧል።ተጨዋቹ በዚህ ሲዝን ለሬንጀርስ 16ጎል እና 12 ለጎል የሚሆን ኳስ ሲያቀብል በዌስትሀም፣ በኒውካስትል እና በክርስቲያል ፓላስም ይፈለጋል።
ሜሱት ኦዚልን ለማስፈረም የአሜሪካኑ ዲሲ ዩናይትድ እና የቱርኩ ፊነርባቼ ተፋጠዋል። የተጨዋቹ ኮንትራት በዚህ አመት መጨረሻ ሚጠናቀቅ ሲሆን ክለቦቹ ግን ኦዚልን በጥር ለማስፈረም ተፋጠዋል። ተጨዋቹ ከቱርክ ይልቅ መዳረሻው አሜሪካ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ባርሴሎናዎች መልማዮቻቸውን ወደ ፖርቱጋል በመላክ የቤኒፊካውን ኡራጋዊ አጥቂ ዳርዊን ኑኔዝን እየተመለከቱ እንደሆነ SPORT አስነብቧል። የ21 አመቱን ኮከብ ወደ ካምፕኑ ለማምጣት ዝግጁ ሲሆኑ የተጨዋቹን ፊርማ ካገኙ በኋላ በቀጣዩ ክረምት የዝውውር መስኮት ማምጣት ነው ፍላጎታቸው።
ቶተንሀም እና ፒኤስጂ አርጀንቲናዊውን የጁቬንቱስ የመስመር አጥቂ ፓብሎ ዲባላን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ካልቺዮ መርካቶ አስነብቧል።በጁቬንቱስ ኮንትራቱ ያላራዘመው ዲባላ ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ ለቦርዱ መናገሩ የተሰማ ሲሆን ሁለቱ ክለቦች ልጁን ለመውሰድ አሁን ላይ ፍላጎት አላቸው።
ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ ሁለት የዝውውር መስኮቶች ቡድኑን በደንብ ማጠናከር ይፈልጋል።ዩናይትድ በቀኝ የተከላካይ መስመር ላይ አሮን ዋን ቢሳካን በጣም የሚፎካከር ተጨዋች ማምጣት ለቢሳካ እድገት ጠቃሚ እንደሆነ አምነዋል በሌላ በኩል ማጥቃቱን ለማጠናከር የማጥቃት ባህሪ ያለው ተጨዋች ተቀዳሚ ምርጫቸው ነው።
No comments:
Post a Comment