ማን ዩናይትድ ከዩቬንትስ ጋር ፖግባን በፓውሎ ዲባላ ሊቀያየር ነው።
ከትናንት በስቲያ የፖል ፖግባ ወኪል ሚኖ ራዮላ ፖግባ ከዩናይትድ በዚህ አመት እንደሚለቅ መናገሩ ይታወሳል።እናም ዛሬ The Athletic እንደዘገበው ዩናይትድ ፖግባን ወደ ዩቬንትስ በመሸኘት በምትኩ ፓውሎ ዲባላን ለማምጣት አቅዷል ።
በሌላ ዘገባ Calciomercato via Daily Mirror እንደዘገበው ፖግባ አሁን በማን ዩናይትድ የሚያገኘውን ሳምንታዊ £290,000 ደሞዝ ቀንሶም ቢሆን ነው ወደ ዩቬንትስ መጓዝ የሚፈልገው።ፖግባ 2016 ላይ ወደ ዩናይትድ ከመመለሱ በፊት በዩቬንትስ መጫወቱ ይታወሳል ።
No comments:
Post a Comment