አዘጋጅ - ኢብራሂም ሙሐመድ
ቸልሲዎች ኮንትራቱ 2022 የሚጠናቀቀውን የባየርን ሙኒኩን ዳቪድ አላባን በጥር ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ቢልድ እና ዘሰን አስነብበዋል። አላባ ከቸልሲ በተጨማሪ በባርሴሎና ፣ማንችስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ ይፈለጋል።
ትናንት ምሽት ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ውጭ የሆኑት ኢንተር ሚላኖች በጥር የዝውውር መስኮት ተጨዋቾችን ወደ ሚላን ማምጣት እንደማይፈልጉ Calciomercato አስነብቧል። በተጨማሪም ኢንተሮች በጥር የተወሰኑ ተጨዋቾችን እንደሚለቁ ይጠበቃል።
እንደ ካልቺዮ መርካቶ ዘገባ ከሆነ ሶስቱ የጣሊያን ሴሪያ ክለቦች ሳሱሎ አትላንታ እና ዩዲኔዚ የሬድስታር ቤልግሬዱን ወጣቱን አንድሬ ዱሪክን በጥር የዝውውር መስኮት ለማስፈረም ተፋጠዋል። የመሀል ተከላካይ የሆነው ዱሪክ በጥር የዝውውር መስኮት ክለቡን መልቀቅ ይፈልጋል።
ባርሴሎናዎች አዲስ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ለመቅጠር ፍላጎት አሳይተዋል። እንደ ስፔኑ Esport3 እንደ ጀርመኑ Bild ዘገባ ከሆነ ባርሴሎናዎች ዋነኛ ትኩረታቸው የቦሩሲያ ዶርትመንዱ ሚካኤል ዞርክ ነው ሰውዬውን በቀላሉ ለማግኘት ቢቸገሩም ግን ወደ ካምፕኑ ለማምጣት ፍላጎት አሳይተዋል።
የአርጀንቲናው ክለብ ቦካ ጁኒየርስ ከብራዚል ሁለት ተጨዋቾችን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል። እንደ TNT SPORT ዘገባ ከሆነ ቦካዎች የሳኦፖሎ የመስመር ተከላካይ የሆነውን ዳኒ አልቬስ እና የፍላሚንጎውን ጋቢጎልን ወደ አርጀንቲና ለማምጣት እንቅስቃሴ ጀምረዋል።
አርሰናል እና ዎልቭስ የቫሌንሲያውን አጥቂ ማክሲ ጎሜዝን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል። እንደ ዴይሊ ሜይል ዘገባ ከሆነ የ24 አመቱ አጥቂ በጥር ቫሌንሲያን እንደሚለቅ ይጠበቃል።ጎሜዝ በዚህ ሲዝን ለቫሌንሲያ በላሊጋው 10 ጨዋታ አድርጎ 3ጎል አስቆጥሯል።
ባየርን ሙኒኮች ሆላንዳዊውን የባርሴሎና አማካይ ፍራንክ ዲዮንግን ለማስፈረም እንደሚፈልጉ ሙንዶ ዲፖርቲቮ አስነብቧል። ባርሴሎናዎች ተጨዋቹን እንደማይለቁት ሲጠበቅ ሙኒኮች ግን ኮከቡን አማካይ ለመውሰድ ፍላጎት አሳይተዋል።
በፒኤስጁ ኮንትራቱ በ2022 የሚጠናቀቀው ፈረንሳዊው ኮከብ ክሊያን ምባቤ በፓሪስ ተጨማሪ ኮንትራት ለመፈረም በቅድሚያ የክለቡን ፕሮጀክት መመልከት እንደሚፈልግ ሌኪፕ አስነብቧል። ምባፔ በፓርክ ደ ፕሪንስ ለመቆየት የመጀመሪያው ጥያቄ የኔይማር ኮንትራት ማራዘም እንደሆነ ተነግሯል።
No comments:
Post a Comment